Get Mystery Box with random crypto!

.....ህማማት ..... አባ አይኮንኑኝ የጦም በመብላቴ እንቁላል በልቼ ብትቆይ ህይ | pökä arts ™

.....ህማማት
.....
አባ አይኮንኑኝ
የጦም በመብላቴ
እንቁላል በልቼ
ብትቆይ ህይወቴ
ሌሎቹን ሳያዩ
እኔን አይገዝቱ
ሰው እየቦጨቁ
በለተ ህማማቱ
ምን ነው ግን አባቴ
በኔ ላይ በረቱ???
ቀለል አርገው አይተው
አባቴ ይፍቱኛ
የጣለችው ዶሮ
ነበረች ጦመኛ
በህይወት ዘመኗ
ስትጭር ስትለቃቅም
ከጥሬ በስተቀር
አንዳች በልታ አታውቅም

ፀባዖት ሶልአኪያ