#ነው_እንዴ? ፡ ፡ ፡ በ እንጀራ ከሞላ ሌማቱ፤ ወጡም ካለ በየዓይነቱ፤ የቱን ልብላ ቢል እንጂ ሰው፤ ሳይጓጓ ነዉ የሚጎርሰው። ፡ ፡ ከጎደለ ግን መሀዱ፤ ኩርማን ሲቀር ከመሶቡ፤ ወጡም ባይጥም የተብላላው፤ ሰው ጣፍጦት ነው የሚበላው። ፡ ፡ ሞልቶ ተርፎ ንቆት ኖሮ፤ ችላ ያለው ተደርድሮ፤ ብላ ሲባል ትዝ ያላለው ተለምኖት ባለመዋል ፤ እፍኝ ሲቀር ከጎተራው ማለቁን ሲያይ ይጥመዋል። ፡ ፡ ሰሞኑን ... ከወትሮ ገነነ ፍቅርሽ በጣም ጣፈጥሺኝ ውዴ፤ ሊያልቅ ነው መሰለኝ ልንለያይ ነው እንዴ? #ሄኖክ_ብርሃኑ @yegetemkalat @poem_merry 2.3K viewsMerry G, 16:32