የእግዜር ታናሽ እህት ።።።።።።።።።።።።።። (ማዕዶት ያየህ) እንዳለመታደል፣ ሽቅብ እንደመውደቅ፣ወደ ሰማይ ገደል፣ ዘንበል ወደ እግዜር ጣት፣ በማግኘት ፍስሀ ፣ማጣትን ለማጣት፣ ሰው በመሆን እቶን፣ቀን ሌት ከመቀጣት፣ መሆን ያሰኘኛል ፣ የግዜር ታናሽ እህት የቀሚሱ አጣቢ፣ ከስሩ ተቀምጣ ፣ ተረት የሚነግራት፣የፍቅሩ ቃል ጠቢ። የአምላክ ተላላኪ፣ ብር ብዬ ሄጄ፣ብር ብዬ መምጣት፣ ማዕዱን መካፈል፣ፅዋውን መጠጣት። ሆዱን ለሚፈጀው፣ሰው አርጎ መስራቱ፣ ላይቀር በእንጨት መሳት፣ከገነት መውጣቱ፣ እኔም ከምፀፀት፣እሱም ከሚያዝንብኝ፣ በእስትንፋስ ቡራኬው፣ግብሩን ቢልክብኝ። 29/09/2014 ዓ.ም. @yegetemkalat @poem_merry 4.1K viewsMerry G, edited 17:32