Get Mystery Box with random crypto!

ዮሐንስ ጌታቸው

የቴሌግራም ቻናል አርማ phronema — ዮሐንስ ጌታቸው
የቴሌግራም ቻናል አርማ phronema — ዮሐንስ ጌታቸው
የሰርጥ አድራሻ: @phronema
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.77K
የሰርጥ መግለጫ

ርቱዕ ሐልዮ
ጥያቄና አስተያየት ካልዎት ይስጡ!
@tmhrte_tsdk_bot

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-30 21:55:21
312 views18:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 21:54:55 +++###ተክለ_ሃይማኖት_ሱራፊ#+++

ተክለ ሃይማኖት ጻድቁ አባታችን በምእመናን ልቡና ሃይማኖትን የተከለ፥ በምግባሩ ክንፍነት ወደ ላይ የበረረ ጻድቅ ነው። በጽድቁ ያለፈውን የሐዋርያት ዘመን ጎትቶ ወደ እርሱ ዘመን ያመጣ፥ ሐዋርያነትን በቅዱስ ጳውሎሳዊነት የተሳተፈ ሐዋርያ ነው። ልበ አምላክ ዳዊት ቀንና ሌሊት ሕጉን የሚያስብ ሰው በውኃ ዳር የተተከለች፡ በየጊዜው ፍሬዋን የምትሰጥ ተክልን ይመስላል እንዳለው ተክለ ሃይማኖት ጻድቁ አባታችን ይህቺን ተክል ይመስላል። የእምነት፣ የምግባርን የማይቋረጥ ፍሬን የሚያፈራ ጻድቅ ተክለ ሃይማኖት ነውና።

በአካለ ሥጋ በምድር እየታየ፡ በተመስጦ ሰማይን ስቦ ወደ ምድር ያወረደ፡ ከምድርም በርሮ በሰማይ ከሱራፊ ጋር በምስጋናም በማዕጠንትም የተሳተፈ፥ ክርስቲያን ሐሳቡን ወደ ሰማይ መውሰድ እንዳለበት በተግባር ያመለከተ ጻድቅ ይሏል ተክለ ሃይማኖት! ጥዕምት የኾነችውን የቅዱሳን መላእክትን ምስጋና የቀመሰ፥ ከቅዱስ ያሬድ በኋላ ያሬዳዊ አኗኗርን ቀምሶ የኖረ! በጽድቁ ጥላ ኃጥአንን የሚከልል ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት!

ቅዱስ ያሬድ "ሐረገ ወይን እንተ በምድር ሥረዊሃ ወበሰማይ አዕጹቂሃ ..." ብሎ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ዘምሯል። ተክለ ሃይማኖት ሕያው መቅደሱ ለክርስቶስ የኾነ ቤተ ክርስቲያን ነው። ሥሩ በምድር ማለትም ቃል ኪዳኑ፣ ጥበቃው፣ አርአያነቱ፤ ቅርንጫፉ በሰማይ ይሏል ባለሟልነቱ ክብሩ በሰማይ ነውና። ፀሐይ የማያጠወልገው፣ የለመለመ የሃይማኖት ተክል ነው። የሥሩን ሥር ክርስቶስን አድርጎ የበቀለ የወይን ሐረግ ነውና ቅርንጫፉ እስከ ሰማይ ይደርሳል።

ተክለ ሃይማኖትን ማየት የሕይወትን መርሕ ማግኘት ነው። የክርስትና ሕይወታችን የደረቀው የዚህ ዓለም ጠማማ ሐሳብ ተጭኖት ነው። ዓይነ ልቡናችንን ወደ ተክለ ሃይማኖት ካደረግን ከእርሱ በሚወጣው ብርሃን አማካኝነት ርቱዐዊነትን ገንዘብ እናደርጋለን። ነገረ ተክለ ሃይማኖትን ከተክለ ሃይማኖታዊ ሕይወት ውጭ ኾነን በአእምሯችን መዝገብ ብቻ ብንይዘው ምን ጥቅም አለው። ጻድቁን አባታችንን በተግባራዊ ሕይወታችን እንቅመሰው፥ በእርሱ የንጽሕናና የቅድስና ተክልነት ውስጥ ልቡናችንን እንትከል! እርሱ ከምድር ወደ ሰማይ ወጥቶ ከሱራፌል ጋር ማጠኑን በማሰብ ልቡናችንን ዲያቆኑ "በሰማይ የሀሉ ልበክሙ" ብሎ በሚያዘን መሠረት በሰማይ እናኑር።

የቅዱሳን ሞታቸው የከበረ የዕረፍታቸው ዕለት ነው። ዕረፍታቸው ወደ ጌታ ደስታ የሚገቡበት በር ነው። በዕረፍታቸውም በዚህ ዓለም ፍቅር ተይዘን በኃጢአት ጒድጓድ ውስጥ ወድቀን ያለነውን ያሳርፉናል። በዕረፍታቸው ውስጥ በረከትን ያድሉናል። የቅዱሳን የልደታቸው ዕለት ብቻ ሳይኾን የዕረፍታቸውም ዕለት ለእኛ የመንፈሳዊ ደስታችን ዕለት ነው። ዕያረፉም ከቀቢጸ ተስፋ የሚያሳርፉን ናቸው። እንግዲህ ክርስትና በተክለ ሃይማኖታዊ እምነትና ሥራ ሱራፊን የመኾን ሕይወት እንጂ ሌላ አይደለም። በረከታቸውን የልቡናችን ጥልቅ ትቅመሳት፡ አሜን።
305 views18:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 16:29:30 The Quickest in Answering - ፍጡነ ረድኤት በስሙ ለጸለየ ሰው ተራዳዒነቱ ፈጣን በመኾኑ የተሰየመለት ነው፡፡ ይህ ደግሞ የምልጃውን ፍጥነት የሚያመለክት ነው፡፡ ለዚህም ነው በእኛ ቤተ ክርስቲያን በመልክአ ጊዮርጊስ ላይ “ኦ ፍጡነ ረድኤት እምሩጽተ ነፋስ ወዐውሎ፡፡ ለዘይጼውአከ በተወክሎ፡፡ ጊዮርጊስ ቅረብ ለምሕረት ወለተሣህሎ፡፡ ተወከፍ ወትረ ጸሎትየ ወቃለ ጽራኅየ ኩሎ፡ እስመ ልበ አምላክ ርኅሩኅ በኀቤከ አሎ - ቅዱስ ጊዮርጊስ ሆይ አንተን በመታመን ለጠራህ ሁሉ ፈጥነህ ስትደርስለት ከዓውሎ ነፋስ ይልቅ በፋጠነ ሩጫ ነው እኮን፡፡ ጊዮርጊስ ሆይ! የዘወትር ጸሎቴንና የቃሌንም የልመና ጩኸት ትቀበል ዘንድ ለይቅርታና ለምሕረት ፈጥነህ ወደ እኔ ቅረብ፡፡” የሚሉን፡፡
ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰማዕታትን የሚያጸና ሰማዕት ነው፡፡ ጊርጊስ ዘእስክንድርያን ሲያጸናው እናገኛለንና፡፡ ቅዱስ ጊርጊስ እየጸለየ ሳለ እግዚአብሔር መልአክና ቅዱስ ጊዮርጊስ ዘልዳ ከሰማይ ወርደው እንዲበረታና እንዲጠነክር ነገሥታቱንም ድል እንዲነሣ ኃይል ሰጡት፡፡ የእስክንድርያው ጊርጊስ የልዳውን ቅዱስ ጊዮርጊስ “አንተ ማን ነህ? ብሎ ጠየቀው፡፡ የልዳው ቅዱስ ጊዮርጊስም “እኔ በፋርሱ ንጉሥ ዱድያኖስ ዘመነ ንግሥና በታይር ከተማ ሰማዕትነትን የተቀበልሁ የሚሊተሱ ጊዮርጊስ ነኝ፡፡ ዐፅሜ ወደ ልዳ በተወሰደና በስሜ ቤተ ክርስቲያን በታነጸልኝ በዓሥራ ሁለቱ ዓመት አባትህ አርሳንዮስ ወደ ልዳ መጥቶ ጌታችን መድኃኒታን ኢየሱስ ክርስቶስ ልጅ ይሰጠው ዘንድ በእኔ ስም ተማፀነ፡፡ እግዚአብሔርም አንተን የእስክንድርያውን ጊርጊስ ሰጠው፤ ተጋድሎህን ፈጽመህ ሰማዕት እስክትኾን ድረስ አልለይህምና አይዞህ ጽና ብሎት ከመልአኩ ጋር ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡” እንግዲህ ቅዱስ ጊዮርጊስ እኛንም በክርስትና ሕይወት ያጸናን ዘንድ ከጥልቅ ልቡናችን ልንለምነው ያስፈልገናል፡፡
464 views13:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 19:41:26 " ትሑት ነፍስ ምስጉን ናት። ጌታ ይወዳታልና። እመ አምላክ ከኹሉም የምትበልጥ ትሕት ናት፤ ስለዚህም በምድር ላይ የሰው ልጆች በሙሉ ያመሰግኗታል፥ ሰማያውያን ኃይላትም ያገለግሏታል። ጌታ የተመሰገነች እናቱን ለእኛ ጠባቂና ረዳት አድርጎ ሰጠን።" (St. Silouan the Athonite, Writings III.14) በእርግጥ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የትሕትና ትምህርት ቤት ናት። ለእርሷ ያለን ፍቅር የሚገለጠውም እርሷ የምትወደውን ትሕትና ገንዘብ ስናደርገው ነው። ትሕትናን ገንዘብ ለማድረግ በየዕለቱ እስካልተጋን ድረስ ደርሶ የሚገኝ ጸጋ አይደለም። በእመቤታችን ዕለት ከእርሷ ጋር መኾናችን አንዱ የሚረጋገጠው ትሕትና ያለን እንደ ኾነ ነው። በትዕቢት እየተቃጠልን ሺህ ጊዜ ለእመቤታችን ፍቅር አለን፤ ማርያም ማርያም ብንል ምን ጥቅም አለው? ዋናው ጉዳይ ለራሳችን በፈቃዳችን ጥመት ያለበስነውን ትዕቢት ክፉ መኾኑን አምነን በማውገዝ ወደ ትሕትና ወደ ለመድረስ እንትጋ እንጂ!
528 views16:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 17:53:43 ርቱዕ ሐልዮ
ጥያቄና አስተያየት ካልዎት ቦቱን በመጫን ይስጡ!
@tmhrte_tsdk_bot
259 views14:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 09:03:46 "ንግሥቲቱ የሚለው ቪዲዮ፥ ይህ የዚያ ክፍል ኹለት ነው"
536 views06:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 09:02:20
589 views06:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 13:26:14 የእመቤታችን ዕርገት

...
በአርመን ኦርቶዶክስ ዝማሬ ላይ በዕርገቷ ጊዜ እንዲህ ይዜማል፡- ዛሬ ሰማያውያን የመንፈስ ቅዱስን ማደርያ ወደ ሰማይ አመጡ። ወደ ሰማያዊቷ ኢየሩሳሌም ያስገቧት ዘንድ፤ እኛ ልንደርስበት በማይቻለን የሥላሴ ክብር በሚገለጥበት ማደርያ በዘለዓለማዊቷ ድንኳን ሰማያውያን ምሥጢር ትሳተፍ ዘንድ አመጧት። “ዛሬ ሰማያዊያን መላእክት የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ቅዱስ አካል ዐሣረጉ፣ በሰው ቋንቋ ሊነገር የማይቻለውን ሰማያዊ ዘለዓለማዊ ደስታ ትሳተፍ ዘንድ በመላእክት መካከል አስቀመጧት” በማለት በግሩም ዜማ የድንግሊቱን ዕርገት በማድነቅ ዝማሬ ያቀርባሉ፡፡ በዲያብሎስ ምክንያት ከዚህ ምሥጢር ርቀው በሕይወታቸው ፍሬ የታጣባቸው የዚህ ዓለም ኑሮን ብቻ የሚወዱ የአስተሳሰብ ድቀት ሰለሠለጠነባቸው ከድንግሊቱ የዕርገት ዜና ርቀዋል። ኢትዮጵያዊው ሊቅ ርቱዓ ሃይማኖትም የድንግሊቱን ዕርገት እንዲህ ይላል፡- አባ ብንያምም ለአንጥያኮስ ሲነግረው “የማርያም ሥጋ እንደጻድቃን ኹሉ በመቃብር አለ የሚል፤ ሥጋዋ በሰማይ እንዳለ ነፍሷም ከሥጋዋ እንደተዋሐደ የማያምን በነፍሷም በሥጋዋም ከሦስቱ ሰማያት በላይ በመንግሥተ ሰማይ እንዳለች ወደ ወደደችውም የምትጎበኝ በሰማይም በምድርም ሥልጣን እንዳላት በጸሎቷ የሚታመኑ ፈቃዷንም የሚያደርጉ እንደሚድኑ ይህን የማያምን ዕጣው በልጇ ስም ካልተጠመቁት ወገን ይኾናል። በጭቃ ከተሠሩ በውጭ ካሉ ቤቶች ይልቅ በወርቅ የተለበጠ የንጉሥ ቤት እንደሚበልጥ ኹሉ የድንግል ማርያም ክብርም ከኹሉም ፍጥረት ይበልጣል” አለ በማለት ሊቁ የአባ ብንያምን ቃል እንሥተው የእመቤታችን ትንሣኤና ዕርገት በክርስቲያኖች ዘንድ ሊታመን እንደሚገባ ገልጾልናል። የኢየሩሳሌሙም ጳጳስ ጢሞቲ የእመቤታችንን ዕረፍትና ዕርገት እንዲህ ገልጸዋል፡- “ድንግል እስካኹን ድረስ ሟች ያለመኾኗ ምክንያት በርሷ ውስጥ ያደረው ጌታ ወደ ማረጊያ ክልሎች ስለወሰዳት ነው” በማለት ሞት በሌለበት በዕረፍት ስፍራ ልጇ ያሣረጋት መኾኑን አስተምረዋል። ሌሎችም ሊቃውንት ቅዱስ ቄርሎስ ዘኢሩሳሌም፣ የብኅንሳው አባ ሕርያቆስ፣ ዮሐንስ ዘደማስቆ አብራርተው ስለ ዕርገቷ ገልጸዋል፡፡
629 views10:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 07:19:12
773 views04:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 22:19:16 ++++###ያልበሩ_ችቦዎች####++++

በዓለ ደብረ ታቦር በእኛ ቤተ ክርስቲያን ከዘጠኙ ዐበይት በዓላት መካከል አንዱ ነው። በግብጽ ግን ዐበይት በዓላት ተብለው የሚከበሩት ሰባት ስለ ኾኑ በዓለ ደብረ ታቦር ከዐበይት አይመደብም።

ይህ በዓል ብዙ መለያዎች ያሉት ቢኾንም፥ በኢትዮጵያ ለየት የሚያደርገው ከበዐሉ ጋር ተያይዘው የሚከበሩት ትውፊታዊ ባህሎች ናቸው። ጅራፉ፣ ሙልሙሉ፣ ችቦው፣ ሕፃናት እየዞሩ የሚያቀርቡት ግጥም። እነዚህ በዓሉን ውብ አድርገው የሚያሳዩ ጌጦች ናቸው። ዋና ዓላማቸውም ጌታችን በታቦር ተራራ የገለጠውን ምሥጢረ መንግሥቱን ማሳየትና በዚያን ዕለት የኾነውን ነገር አኹን እንደ ኾነ አድርጎ ማቅረብ ነው።

አምላካችን ክርስቶስ ለቅዱሳን ሐዋርያት ከፍ ባለው ስፍራ (በታቦር ተራራ) አስደናቂውን አምላካዊ ብርሃን ብልጭታውን ጨረፍ አድርጎ አሳይቷቸዋል። በጣም በጥቂቱ። አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ አዳም ቀድሞ በገነት የለበሳትን የብርሃን ልብስ ገለጣት ይሉናል። አምላክ በአምላክነቱ ይገለጥ ዘንድ ተገቢ አይደለምና! ቢገለጥ የታቦር ተራራ አትችለውም ነበርና። የኾነው ኾኖ መገለጡ የተከወነው በከፍታ ነው። ነገሩ "በሰማይ የሀሉ ልበክሙ" ልቡናችሁን ከፍ አድርጋችሁ በሰማይ አኑሩት ነው! አእምሩ ኀበ ዘትቀውሙ "የቆማችሁበትንም ቦታ አስቡ" እንዲል። ወደ ታቦር መውጣት ቅዳሴን ወደ መረዳት መውጣት ነው። በንጽሕና እና በሥርዓት በቅዳሴ ውስጥ ከኾን፡በሕያዊት የታቦር ተራራ ላይ መኾናችንን ልብ እንበል። በዓለ ታቦርን ራቅ አድርገን ሳይኾን እዚሁ አጠገባችን እንዳለ ከመረዳት እንነሣ! ስለዚህ አስተሳሰባችንን ወደ ላይ ከፍ እስካላለ ድረስ በዓሉን በውስጣችን እያከበርነው አይደለም ማለት ነው። በዓሉን በዋናነት ማክበር ያለብን በእኛው ውስጥ ነውና!

ጅራፉ በራሱ መጮኸ አይችልም። በሰው እጅ ተይዞ ሲጮኸ ግን በታቦር ተራራ ላይ የተሰማውን ድምፅ የሚወክል ይኾናል። ይህም ድምፅ በእኛ ሰውነት ውስጥ መሰማት አለበት። ለሰው ልጆች በሙሉ ያለን የፍቅር ድምፅ! ክርስቶስን በሙሉ ሰውነታችን ለማግኘት የመጓጓት ድምፅ! ሰላምን ለዓለም የሚያበራ ድምፅ! ይህ ድምፅ ከሕያው ሰውነታችን መውጣት አለበት። እኛ ዕውቀት ያላቸው ጅራፎች ኾነን መቅደስ በኾነ ሰውነታችን ውስጥ የቅድስናና የንጽሕናን ድምፅ ማሰማት አለብን። ሌላ ታቦር ፍለጋ አንሂድ ሰውነታችንን ከቀደስነው ሕያዋን የታቦር ተራራዎች እኛው ነንና። አምስቱ አገልጋዮች (ሙሴ፣ አልያስ፣ ጴጥሮስ፣ ያዕቆብና ዮሐንስ) የአምስቱ የስሜት ሕዋሶቻችን ምሳሌዎች ናቸው። እንግዲህ እኒህን አካላት ቀድሰን ለእግዚአብሔር ስናቀርብ እግዚአብሔር በእኛ ሰውነት አድሮ ብርሃኑን ይገልጣል። የፍቅር ድምፁን በእኛ በኩል ለኃጥአን ያሰማል፥ ኑ ወደ እኔ እኔ አምላካችሁ ነኝና ይላል።

ልበ አምላክ ዳዊት "ታቦር ወአርሞንኤም በስመ ዚአከ ይትፌስሑ ወይሴብሑ ለስምከ" ያለው ስለ ታቦርና አርሞንኤም ለማውራት ብቻ አይምሰለን፥ ስለ እኛም እንጂ። የተግባራዊ ሕይወት ድምፃችንን ከፍ አድርገን ክርስቶስን መምሰል ለዓለም በማሳየት ደስ ልንሰኝ የሚገባ ነውና። የጅራፉ ጩኸት የአብን ድምፅ የሚወክል እንደ ኾነ ከጅራፉ በላይ የኾን እኛ የአብን ድምፅ በእውነተኛ ሕይወታችን ለአሕዛብ ልናሰማ ይገባናል። በሕይወት ጨለማ ውስጥ ላሉት ኃጥአን በሕይወታችን የክርስቶስን የፍቅር ብርሃን እያበራን ወደ እውነት ልንጎትታቸው ይገባል።

ታቦር ጨለማ አይደለችም፥ የሥግው ቃል ብርሃን የተገለጠባት ልዩ ስፍራ እንጂ። እንግዲህ ያን በታቦር ተራራ የበራውን ብርሃን በችቦ በኩል እንገልጠዋለን። በችቦው ብርሃን በኩል ወደ አማናዊው ብርሃን እንጓዛለን። እንግዲያውስ ከክርስቶስ ሕያዊት ማኅደር ሰውነታችን በቀር ብርሃኑ የማይቋረጥ ችቦ ወዴት ያለ ይመስላችኋል? የእኛ ሰውነት እየነደደ የሚያበራ ችቦ ነው። ወንጌልን የሚያበራ ችቦ! ወዲህ አለ። የኸውም የቅዱሳን ሰውነት ነው። ለዚህም ነው ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ የሚነድና የሚያበራ መብራት ተብሎ በጌታችን የተመሰከረለት። ስለዚህ ችቦውን ስታዩ፡ ወደ ሰውነታችሁ ተመለሱና የእግዚአብሔር ትእዛዝ በመጠበቅ ማብራት አለማብራታችሁን መርምሩ። እግዚአብሔር ለጨለማው ዓለም መብራት እንኾን ዘንድ በክርስቶስ ክርስቲያን ብሎ ከብርሃናዊው አምላክ ብርሃን ሲያሳትፈን እኛ ግን የዚህን ዓለም ርካሽ የጨለማ ሐሳብ ይዘን አልላቀቅ አልን። እንኳንስ ለሌላው ለራሳችንም ማብራት አቅቶን በዘረኝነት፣ በጥላቻ፣ በትዕቢት፣ በስንፍና እና በመሳሰሉት ጨለማዎች ውስጥ ተሸሸግን። ለዓለም ችቦ መኾን ሲገባን ጨለማ ኾንን። ብርሃን በማጣት ለጨለመችው ዓለም ተጨማሪ ጨለማ ኾነን ጨለምተኝነቷን አሰፋነው። እንግዲህ እርሱ እግዚአብሔር በቸርነቱ ወደ እውነተኛ የክርስትና ሕይወት እንድንመለስ የሚያደርግ ኀይል ያድለን አሜን!
862 views19:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ