2022-05-19 20:26:36
የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ !!
በድሬዳዋ ባለፉት ጥቂት ቀናት ከወትሮው የተለየ ከፍተኛ የሆነ የሙቀት መጠን እንደተስተዋለ መረጃዎች ያሳያሉ።
ከባቢያዊ የሙቀት መጠን በጨመረ ቁጥር ሰውነታችን የሙቀት መጠኑን መቆጣጠር እየተሳነው በተለይም አረጋውያን፣ ህፃናትና የተለያየ የጤና እክል ያለባቸው ግለሰቦች ለከፍተኛ የጤና ችግርና ሞት ሊዳረጉ እንደሚችሉ የተለያዩ ጥናቶች ያሳያሉ።
በመሆኑም የአስተዳደራችን ነዋሪዎች በተለይም አረጋውያን እና የተለያዩ ተጓዳኝ ህመም ያለባቸው(ከፍተኛ ደም ግፊት፣የስኳር ህመም፣የልብ ህመም፣የኩላሊት ህመምና ሌሎችም)፣እራሳቸውን መንከባከብ የማይችሉ የአይምሮ ህሙማን እና ህፃናት በተለየ መልኩ ከታች የተዘረዘሩትን የጥንቃቄ መልእክቶች ተግባራዊ ያድርጉ ።
1. ወቅታዊው ከፍተኛ የሙቀት መጠን እስኪያልፍ መኖሪያ ቤትዎን በተለያዩ መንገዶች ማቀዝቀዝ
2. እቤትዎ በሚሆኑበት ግዜና በእንቅልፍ ወቅት የቤትዎን መስኮትና በር ክፍት ማድረግ
3. በቤትዎ የአየር መታፈን እና ከፍተኛ ሙቀት በሚኖርበት ወቅት ከቤትዎ ውጪ/በረንዳዎ ላይ መቆየት
4. ጥም ባይኖርቦትም በቂ ፈሳሽ/ውሃ/ መውሰድ
5. አመጋገብዎን ማስተካከል(ስብና ቅባት የበዛባቸው ምግቦችን መቀነስ)
6. ቀለል ይሉ አካላዊ እንቅስቃሴዎችን ጥላማ በሆኑ ቦታዎች ላይ መስራት
7. የአልኮል መጠጦችን አለመጠቀም/መቀነስ
8. ህፃናትን እና የአዕምሮ ህሙማንን በተዘጉ/አየር በሌላቸው ክፍሎች ለብቻ አለመተው እና
9.የተለያየ ህመም ማለትም እንደ ከፍተኛ ደም ግፊት፣ስኳርና የልብ ህመም ካለብዎ የህክምና ክትትልዎን በሚገባ ያድርጉ፣የታዘዘሎትን መድሃኒት በትዕዛዙ መሰረት በመውሰድ ጤናዎን ይጠብቁ!
961 viewsSamuel.T, 17:26