Get Mystery Box with random crypto!

ኢየሱስ አለልን! ሐጢአተኛ ነኝ ወደ እግዚአብሔር መቅረብ አልችልም አንበል።ኢየሱስ ወደ አብ የምንገ | ጵራቅሊጦስ

ኢየሱስ አለልን!
ሐጢአተኛ ነኝ ወደ እግዚአብሔር መቅረብ አልችልም አንበል።ኢየሱስ ወደ አብ የምንገባበት ድፍረታችን ነው።በእግዚአብሔር ፊት ይዤ የምቀርበው ነገር የለኝም አንበል።አብ የረካበት መስዋዕት የሆነልን ኢየሱስ አለልን።ምን ለብሼ እግዚአብሔር ፊት ልቅረብ አንበል።ኢየሱስ ጉድፍ የሌለበት ልብሳችን ነው።ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርብ መልካም ጠረን የለኝም አንበል።ኢየሱስ በአብ ፊት መአዛችን ነው።ኢየሱስ በድካማችን ሐይሉን፣በሐጢአታችን ምህረቱን ገልጧል።በባዶነታችን ላይ እሱ ሙላታችን ነው።

አለኝ ብዬ የምመካብህ ኢየሱስ ተባረክ።