Get Mystery Box with random crypto!

ጠበቃችን ኢየሱስ ነው! ሐጢአት ሰርተን በሞት እስር ቤት ነበርን።ከኢየሱስ በቀር በዚህ እስር ቤት | ጵራቅሊጦስ

ጠበቃችን ኢየሱስ ነው!
ሐጢአት ሰርተን በሞት እስር ቤት ነበርን።ከኢየሱስ በቀር በዚህ እስር ቤት ያልነበረ ማን አለ?ሮሜ 3:23ጌታ ኢየሱስ ፍጹም ሰው ሆኖ ስለ ሐጢአታችን ደሙን ከፍሎ በሞቱ ማልዶ ነጻ አወጣን።ዛሬም ብንደክም ለሐጥያታችን ይቅርታ እንድናገኝ ሞቼላቸዋለው ብሎ የሚከራከርልን ኢየሱስ ነው።ቃሉ እንዲህ ይላል"ልጆቼ ሆይ፥ ኃጢአትን እንዳታደርጉ ይህን እጽፍላችኋለሁ። ማንም ኃጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን እርሱም ጻድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።"1 ዮሐ 2:1

በእግዚአብሔር ፊት ለመቆም አቅም ስናጣ እሱ ስለ እኛ ይቆምልናል።በደከምን ጊዜ በእግዚአብሔር ፊት የሚታይልን ያመንነው ኢየሱስ ነው።አብ እስከ ሞት የታዘዘውንና ደስ የተሰኘበትን ጻድቅ ልጁን በልባችን ውስጥ ሲያይ ይራራልናል።

በሰማይ የነበረው ከሳሻችን ሰይጣን ወድቆ ጠበቃችን ቆሟል።ጠበቃ አንተ ስትፈቅድ ነው የሚቆምልህ።የኢየሱስም ጥብቅና በጠበቃነቱ ላመኑበት ብቻ ነው።

የማታሳፍረን ጠበቃችን ኢየሱስ ስምህ በትውልድ መካከል ይክበር።