Get Mystery Box with random crypto!

ኢንትራንስ ተፈታኝ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ይዘው መሄድ የማይፈቀድላቸው ነገሮች ማንኛውም ድም | Our World

ኢንትራንስ ተፈታኝ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ይዘው መሄድ የማይፈቀድላቸው ነገሮች

ማንኛውም ድምፅ የሚቀዳ፣ፎቶ የሚያነሳ ፣ ቪድዮ የሚቀርፅ ፣ ከቴሌ መስመርም ሆነ ከቴሌ መስመር ውጭ መልዕክት በዲጅታል መንገድ የሚሰጥ ወይም የሚቀበል የግል ዕቃ/መሳሪያ/የቴክኖሎጂ ውጤት ፣ ስልክ ፣ አይ-ፓድ፣ታብሌት፣ኮምፒውተር፣ላፕቶፕ፣ስማርት ሰዓት ፣ ማጂክ ብዕር፣ማጂክ ጃኬት እና ሌሎች ማናቸውም ፎቶ፣ምስል እና ድምፅ የሚቀርጹ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችን በዩንቨርሲቲው ግቢ ውስጥም ሆነ ግቢ ዙሪያ ይዞ መገኘት ክልክል ነው።

በዩንቨርሲቲ ውስጥ ማንኛውም ዓይነት የግል ፍላሽ ዲስክ፣ሃርድ ዲስክ፣ሲዲ፣ሚሞሪ ካርድ ፣ሚሞሪ ሪደር፣ ኦ ቲጂ፣ኮንቨርተርና መሰል ዕቃዎችን ይዞ መገኘት ክልክል ነው

ማንኛውም ዓይነት የአንገት ሐብል፣የፀጉር ጌጥ፣የጆሮ ጌጥ፣የጣት ቀለበት፣የእጅ አንባር አድርጎ ወይም ይዞ መገኘት ክልክል ነው (ከልሙጥ የጋብቻ ቀለበት በስተቀር)