Get Mystery Box with random crypto!

በቻይና ሲያቅፈኝ የጎን አጥንቴን ሰብሯል ያለችዉ ግለሰብ የስራ ባልደረባዋን ከሰሰች በቻይና ሁናን | Our World

በቻይና ሲያቅፈኝ የጎን አጥንቴን ሰብሯል ያለችዉ ግለሰብ የስራ ባልደረባዋን ከሰሰች

በቻይና ሁናን ግዛት ዩያንግ ከተማ ነዋሪ የሆነችዉ ግለሰብ በስራ ላይ እያለች አንድ ወንድ የሥራ ባልደረባዋ መጥቶ እቅፍ አድርጎ ሰላምታ ያቀርብላታል፡፡እቅፍ ሲያደርጋት ግን ከፍተኛ ህመም ስለተሰማት ትጮኃለች፡፡ ሰውዬው በጣም አቅፎት የነበረ ሲሆን ከስራ ከወጣች በኋላም ደረቷ ላይ ህመም ይሰማት ይጀምራል፡፡ነገር ግን ወዲያውኑ የህክምና እርዳታ አልፈለገችም ደረቷ ላይ ትንሽ ትኩስ ዘይት በመቀባት እና በምትኩ መተኛትን ትመርጣለች።

በጣም ጥብቅ ከሆነው እቅፍ ከአምስት ቀናት በኋላ በደረቱ ላይ ያለው ህመም እየጠነከረ ይሄዳል፡፡ በመጨረሻ ምርመራ ለማድረግ ወደ ሆስፒታል ትሄዳለች፡፡በኤክስሬይ ምርመራ አንድ ሳይሆን ሶስት የተሰበሩ የጎድን አጥንቶች፣ ሁለቱ የጎድን አጥንቷ በቀኝ እና አንድ በግራ በኩል እንዳለ ይረጋገጣል፡፡

በዚህም የተነሳ ከስራ እረፍት ለመዉሰድ ትገደዳለች ፣ይህም ገቢ እንድታጣ እና ለህክምና ሂሳብ ብሎም ለነርሶች አገልግሎት በርካታ ገንዘብ አውጥታለች።በህመሜ ወቅት እንዲረዳኝ ብጠይቀዉም ፍቃደኛ አልነበረም ያለችዉ ግለሰብ ካገገመች በኃላ በስራ ባልደረባዋ ላይ በዩኢያንግ ከተማፍርድ ቤት ክስ በመመስረት ለደረሰባት የገንዘብ ኪሳራ ካሳ ትጠይቃለች፡፡ፍርድ ቤቱ በሥራ ባልደረባው ላይ በአጋጣሚ በማቀፍ የጎድን አጥንቷን በመስበር 10,000 ዩዋን (1,500 ዶላር) ካሳ እንዲከፍላት ትእዛዝ አስተላልፏል።