Get Mystery Box with random crypto!

ዓለም አቀፍ የግራኞች ቀን አስደናቂ መረጃዎች ~ ዛሬ ነሀሴ 7 ቀን ዓለም አቀፉ የግራኞች ቀን | Our World

ዓለም አቀፍ የግራኞች ቀን አስደናቂ መረጃዎች

~ ዛሬ ነሀሴ 7 ቀን ዓለም አቀፉ የግራኞች ቀን የሚከበር ሲሆን እ.ኤ.አ ከ1996 ጀምሮ በዓለም አቀፉ የግራኞች ማህበር መስራች ዲን ካምቤል አማካይነት መከበር ጀምሯል።

~ 12 በመቶ የአለም ህዝብ ግራኝ ሲሆን ወንዶች ከሴቶች የበለጠ ግራኞች ናቸው።17 በመቶ መንትዮች ግራኝ ናቸው።

~ ታይም መፅሄት በ10ሺ ሰዎች ላይ በሰራው ጥናት በወሲባዊ ህይወት ግራኞች ከቀኞች ደስተኛ ናቸው ይላል።ከግራ ጭንቅላት አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ግራኞች ከስትሮክ ከቀኞች በተሻለ በቶሎ ያገግማሉ።

~ በኮከብ ቆጠራ ረገድ ስንመለከተው ከግንቦት 14 እስከ ሰኔ 13 የተወለዱት ከሌሎች ዞዳይኮች ሲነፃፀር ጄሚኒዎች ውስጥ ብዛት ያላቸው ግራኞች አሉ።

~በየአመቱ ለቀኝ ተጠቃሚዎች ብቻ ተብለው በተሰሩ መገልገያዎች የተነሳ ከ2500 በላይ ግራኞች ህይወታቸውን ያጣሉ።ግራኞች በገቢ ከቀኞች በአማካይ 12በመቶ ያንሳሉ።

~አለማችን ላይ ታዋቂ ከሚባሉ ግራኞች መካከል ቻርሊ ቻፕሊን፣ዳ ቬንቺ ፣ኦፕራ ፣አንስታይን፣ ኒውተን ቢል ጌት እና ሚካኤል አንጄሎ  ተጠቃሽ ናቸው።ከቅርብ ጊዜ 9 የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች መካከል አምስቱ ግራኝ ናቸው።እነርሱም ኦባማ፣ቢል ክሊንተን፣ፎርድ፣ሮናልድ ሬገን እና ትልቁ ቡሽ ናቸው።

~ በሂሳብ ስሌት ረገድ ግራኞች የበለጠ ውጤታማ ናቸው።ነፍሰ ጡር ሴት በተደጋጋሚ በእርግዝና ወቅት በድብርት የምትጠቃ ከሆነ ግራኝ ልጅ የመውለድ ሰፊ እድል አላት።

~ በኮምፒውተር ኪቦርድ ላይ ታይፕ ለማድረግ ከ3ሺ በላይ የእንግሊዝኛ ቃላት ለመፃፍ በግራ የተመቸ ሲሆን በቀኝ ከ300 የበለጠ አይደለም።

~ ግራኞችን በተመለከተ ከተነገሩ ዝነኛ አባባሎች መካከል ጀርመናዊው ፈላስፋ ዋልተር ቤንጃሚን ሁሉም ከባድ ቡጢዎች በግራ ያርፋል ብሏል።