Get Mystery Box with random crypto!

በህንድ መአዛ ያለዉን ኮንዶም አፍልተዉ የሚጠጡ ወጣቶች ቁጥር መበራከቱ ስጋት ፈጥሯል ተባለ በህን | Our World

በህንድ መአዛ ያለዉን ኮንዶም አፍልተዉ የሚጠጡ ወጣቶች ቁጥር መበራከቱ ስጋት ፈጥሯል ተባለ

በህንድ በምዕራባዊ ቤንጋል ዱርጋፑር ከተማ ተማሪዎች ኮንዶም የመጠቀም ሱስ ዉስጥ ወድቀዋል ተብሏል፡፡የተለየ መዓዛ ያለዉ ኮንዶም ሽያጭ በከተማዋ የተለያዩ ክፍሎች በሚያስገርም ሁኔታ ጨምሯል፡፡ በዱርጋፑር ከተማ ቢድሃናጋር፣ ሙቺፓራ እና ቤናቺቲ፣ ሲ ዞን፣ ኤ ዞንን በተባሉ አካባቢዎች በሚገኙ የመድኃኒት መደብሮች ዉስጥ የኮንዶም ሽያጩ በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩ ተጠቁሟል፡፡

ተማሪዎቹ ኮንዶም በሞቀ ውሃ ውስጥ እየነከሩ ያቆያሉ፤ ከዚያም በኋላ ከ 10 እስከ 12 ሰአታት ድረስ ፈሳሹን እንደሚጠጡ ተነግሯል፡፡መዓዛ ያለዉን ኮንዶም ለመስራት ጥቅም ላይ የሚዉሉ ንጥረ ነገሮችን በሙቅ ውሃ ውስጥ ለረጅም ጊዜ በማቆየት የአልኮሆል ውህድ እንዲፈጠር ያደርጋሉ። ድርጊቱ ግን ዘላቂ ሱስ ከማስያዝ ባለፈ ለጤና እጅግ ጎጂ ስር የሰደደ እክል ሊፈጥር እንደሚችል የጤና ባለሙያዎች ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ቀደም ከሶስት እስከ አራት ፓኬቶች ኮንዶም በአንድ ሱቅ በቀን ይሸጥ የነበረ ሲሆን አሁን ግን አንድ ጥቅል ሙሉ ኮንዶም በየቀኙ እንደሚሸጡ የመድኃኒት መደብር ባለሙያዎች ገልጸዋል፡፡