የ
ዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ የዓለማችን አሳሳቢ የጤና ችግር መሆኑን የአለም ጤና ድርጅት አስታወቀበጥቂት አገሮች በቅርቡ የተከሰተው “የዝንጀሮ ፈንጣጣ” በሽታ የዓለማችን አሳሳቢ የጤና ችግር መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ።
ድርጅቱ ዛሬ ባወጣው መግለጫ የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፋ መሆኑንና ባልተጠበቀ ሁኔታ በዓለማችን በ70 ሀገራት ውስጥ በወረርሽኝ መልክ መከሰቱን ገልጿል።
በሽታው ክትባት ያልተገኘለትና ለሕክምናውም ከፍተኛ ኢቨስትመንት የሚጠይቅ በመሆኑ ሌላኛው የዓለማችን አሳሳቢ ወረርሽኝ ሆኗል ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አውጇል።