Get Mystery Box with random crypto!

የራስሽ ውሽማ ኤልያስ ሽታኹን ~ ~ ~ ~ ~ የልጆች ዋጋ ው | የኛ ግጥም ና ታሪክ

የራስሽ ውሽማ
ኤልያስ ሽታኹን
~ ~ ~ ~ ~

የልጆች ዋጋ ውድ ነው ርካሽ
ሰልስትም አትቆይም ወረት እየነካሽ?

ፈውስ የለም
ዘላለም
ምን ሀኪም አስታሞን?
ሞትሽ የዘላለም ለቅሶሽ የአንድ የሰሞን::

እኔማ
ዕንባና ለቅሶሽን ወረትሽ አርሞት
እጠብቅሻለሁ
እስከምንግናኝ ደሞ በሌላ ሞት::

(እኛ እኮ ክፉ ነን)
ይኸውልማ
ሰው እንዴት ይሆናል የራሱ ውሽማ?
የሞቱ ውሽማ?
የነገው ውሽማ?

አንቺ የሰው ሲኦል አንቺ የሰው ገነት
ስንት ገባ ህይወት ስንት ነው ዜግነት?
ስንት ነው ሰውነት?
ስንት ነው ማንነት?