Get Mystery Box with random crypto!

የባጃጅ ሾፌሮች ጉዳይ … ————————————— ዶ/ር ሠዒድ መሐመድ (የአጥንት ህክምና ስፔሻሊስት | ♒Orthopedic Surgery in Ethiopia ♒

የባጃጅ ሾፌሮች ጉዳይ …
—————————————
ዶ/ር ሠዒድ መሐመድ
(የአጥንት ህክምና ስፔሻሊስት)
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

"ባጃጅ" እየተባሉ የሚጠሩት ባለሶስት እግር ተሽከርካሪዎች ከጊዜ ወደጊዜ እየተበራከቱ መጥተው አዲስ አበባን ጨምሮ በሐገራችን ትላልቅ ከተሞች ውስጥ ሳይቀር በስፋት የትራንስፖርት አገልግሎት እንደሚሠጡ ይታወቃል።

በአብዛኛው እነዚህን ተሽከርካሪዎች የሚነዱ ሾፌሮች ግን በዕድሜ አነስ ያሉ  ፣ በልምድም ጀማሪ በመሆናቸው ከቀላል እስከ ከባድ አደጋዎች ፣ አለፍ ሲልም የህይወት ህልፈት እንዲከተል ምክንያት ሲሆኑ ይስተዋላል። በተለይ እንደኔ የስራ ባህሪው ከአደጋዎች እና የአጥንት ስብራቶች ጋር በየቀኑ የሚያገናኘው ሠው የባጃጅ አደጋን መስማት ለጆሮው እንግዳ ያልሆነ የተለመደ ክስተት ቢሆንበት እምብዛም አይገርምም።

የዛሬዋ ባለታሪኬ 62 ዓመት ዕድሜ ያላቸው የአዲስ አበባ ነዋሪ ሲሆኑ፣ በሚኖሩበት ኮንዶሚኒየም ግቢ ውስጥ በባጃጅ ለመሳፈር ወንበር በሚይዙበት ሠዓት ገና አንድ እግራቸው  ከመሬት ሳይነሳ ወንበር ላይ መቀመጥ እንደጀመሩ ሹፌሩ በችኮላ መንዳት በመጀመሩ ምክንያት የእግራቸው ቁርጭምጭሚት መገጣጠሚያ ዙሪያ ከፍተኛ ስብራቶች እና የመገጣጠሚያ ውልቃት ሊያጋጥማቸው ችሏል።

(ቀዶ ህክምና ከመስራቴ በፊት እና በኋላ ያሉት የራጅ ምስሎች ከስር ተያይዘዋል።)

የባጃጅ ሾፌሮች የተሳፋሪን ዝግጁነት ሳያረጋግጡ በመንዳታቸው ምክንያት ልክ እንደዛሬዋ ባለታሪክ አይነት ስብራቶች እና ህይወትን በከፍተኛ ደረጃ ችግር ውስጥ የሚከቱ ጉዳቶች  ከጊዜ ወደጊዜ እጅግ እየጨመሩ መምጣታቸውን በማስተዋል፣ ለባጃጅ ሾፌሮች የልምምድ ስልጠና እና የመንጃ ፈቃድ የሚሠጡ አካላት የአነዳድ ስልጠና ከመስጠት ባለፈ  ይህንን ባጃጅ ላይ ብቻ ተደጋግሞ የሚስተዋል የክህሎት ችግር ልዩ ትኩረት እንዲሠጡት እንመክራለን።
——————————————————————
ይከተሉን…

የቴሌግራም ቻናል: https://t.me/patientstories

የፌስቡክ ገፅ: የአጥንት ህክምና/Orthopedic Surgery (https://www.facebook.com/EthioOrthopedics/)

ለህክምና ቀጠሮ ስልክ: 6194 (ዶ/ር ሠዒድ)