Get Mystery Box with random crypto!

♒Orthopedic Surgery in Ethiopia ♒

የቴሌግራም ቻናል አርማ ourpatients — ♒Orthopedic Surgery in Ethiopia ♒ O
የቴሌግራም ቻናል አርማ ourpatients — ♒Orthopedic Surgery in Ethiopia ♒
የሰርጥ አድራሻ: @ourpatients
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 313
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ቻናል በአጥንት ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስቶች የሚሠጡ ጠቃሚ ትምህርቶች እና የታካሚዎች ገጠመኞች ለአንባቢያን ይቀርብበታል።

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-25 18:12:36
ኮንዶምን ለመጠጥ?
——————————
በምስራቃዊ ህንድ የምትገኘው "ዱርጋፑር" ከተማ ውስጥ የሚገኙ ወጣቶች ኮንዶሞችን በውሃ እየቀቀሉ ውኃውን የመጠጣት ልማድ እያዳበሩ በመምጣታቸው ምክንያት በከተማው ከፍተኛ የኮንዶም እጥረት እንደተከሠተ ተነግሯል።

ወጣቶቹ ይህንን የሚያደርጉት ኮንዶሙ መልካም ጠረን እንዲኖረው ተብሎ የሚጨመረው ኬሚካል ኮንዶሙ ከተሠራበት ፕላስቲክ ጋር አብሮ ሲቀቀል እና በሞቀው ውኃ ውስጥ ለብዙ ሠዓታት ተነክሮ ሲቆይ የአልኮልነት ባህሪ ወዳለው ሌላ አስካሪ ኬሚካልነት ስለሚቀየር  ፣ ወጣቶቹ ያንን ውኃ እየጠጡ አዲስ ሱስ ውስጥ ሊገቡ ችለዋል። በዚህም ምክንያት እዚያች ከተማ ውስጥ አዲስ የኮንዶም ምርት ገበያ ላይ እንደገባ ወዲያውኑ ተሽጦ ማለቅ ጀምሯል። የከተማው አስተዳደርም ጉዳዩን የደረሰበት ይሄንኑ ያልተለመደ የኮንዶም ፍላጎት መጨመርን ተከትሎ "ምን ተፈጥሮ ይሆን?" ብሎ ሲከታተል ነው።

"Durgapur Syndrome" loading ...
355 viewsedited  15:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-17 16:26:12
839 views13:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-17 16:25:55 የባጃጅ ሾፌሮች ጉዳይ …
—————————————
ዶ/ር ሠዒድ መሐመድ
(የአጥንት ህክምና ስፔሻሊስት)
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

"ባጃጅ" እየተባሉ የሚጠሩት ባለሶስት እግር ተሽከርካሪዎች ከጊዜ ወደጊዜ እየተበራከቱ መጥተው አዲስ አበባን ጨምሮ በሐገራችን ትላልቅ ከተሞች ውስጥ ሳይቀር በስፋት የትራንስፖርት አገልግሎት እንደሚሠጡ ይታወቃል።

በአብዛኛው እነዚህን ተሽከርካሪዎች የሚነዱ ሾፌሮች ግን በዕድሜ አነስ ያሉ  ፣ በልምድም ጀማሪ በመሆናቸው ከቀላል እስከ ከባድ አደጋዎች ፣ አለፍ ሲልም የህይወት ህልፈት እንዲከተል ምክንያት ሲሆኑ ይስተዋላል። በተለይ እንደኔ የስራ ባህሪው ከአደጋዎች እና የአጥንት ስብራቶች ጋር በየቀኑ የሚያገናኘው ሠው የባጃጅ አደጋን መስማት ለጆሮው እንግዳ ያልሆነ የተለመደ ክስተት ቢሆንበት እምብዛም አይገርምም።

የዛሬዋ ባለታሪኬ 62 ዓመት ዕድሜ ያላቸው የአዲስ አበባ ነዋሪ ሲሆኑ፣ በሚኖሩበት ኮንዶሚኒየም ግቢ ውስጥ በባጃጅ ለመሳፈር ወንበር በሚይዙበት ሠዓት ገና አንድ እግራቸው  ከመሬት ሳይነሳ ወንበር ላይ መቀመጥ እንደጀመሩ ሹፌሩ በችኮላ መንዳት በመጀመሩ ምክንያት የእግራቸው ቁርጭምጭሚት መገጣጠሚያ ዙሪያ ከፍተኛ ስብራቶች እና የመገጣጠሚያ ውልቃት ሊያጋጥማቸው ችሏል።

(ቀዶ ህክምና ከመስራቴ በፊት እና በኋላ ያሉት የራጅ ምስሎች ከስር ተያይዘዋል።)

የባጃጅ ሾፌሮች የተሳፋሪን ዝግጁነት ሳያረጋግጡ በመንዳታቸው ምክንያት ልክ እንደዛሬዋ ባለታሪክ አይነት ስብራቶች እና ህይወትን በከፍተኛ ደረጃ ችግር ውስጥ የሚከቱ ጉዳቶች  ከጊዜ ወደጊዜ እጅግ እየጨመሩ መምጣታቸውን በማስተዋል፣ ለባጃጅ ሾፌሮች የልምምድ ስልጠና እና የመንጃ ፈቃድ የሚሠጡ አካላት የአነዳድ ስልጠና ከመስጠት ባለፈ  ይህንን ባጃጅ ላይ ብቻ ተደጋግሞ የሚስተዋል የክህሎት ችግር ልዩ ትኩረት እንዲሠጡት እንመክራለን።
——————————————————————
ይከተሉን…

የቴሌግራም ቻናል: https://t.me/patientstories

የፌስቡክ ገፅ: የአጥንት ህክምና/Orthopedic Surgery (https://www.facebook.com/EthioOrthopedics/)

ለህክምና ቀጠሮ ስልክ: 6194 (ዶ/ር ሠዒድ)
833 views13:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 20:11:57
1.3K views17:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 21:40:36 የነፃ ህክምናው ሂደት …
——————————————
ከዚህ በፊት የነፃ ህክምና ዕድል ለመስጠት የታቀደበትን ቪዲዮ በዚሁ ገፅ ላይ አጋርተናችሁ በርካቶች የዕድሉ ተጠቃሚ ለመሆን ጥያቄ አቅርባችሁ እንደነበረ ይታወሳል። በመሆኑም ሂደቱ የደረሰበትን ለገፃችን ተከታታዮች ማሳወቁ አስፈላጊ ስለሆነ እንደሚከተለው ተብራርቷል።

ማስታወቂያው ይፋ በተደረገበት ቪዲዮ ላይ (

) የዕድሉ ተጠቃሚ ለመሆን የቀረበው መስፈርት: ማስታወቂያው የተነገረበትን ቻናል "ሰብስክራይብ ማድረግ፣ የደወል ምልክቱን መጫን እና የዕድሉ ተጠቃሚ ለመሆን ፍላጎት እንዳለ መግለፅ" የሚል ነበር።

በገለፃውም መሠረት ሰብስክራይብ አድርገው የዕድሉ ተጠቃሚ ለመሆን የጠየቁትን በመለየት እና ከመሐል በዕጣ ሃያ ሰዎችን በመምረጥ ከሶስት ሳምንታት በፊት የዕድለኞችን ስም ዝርዝር እና የሚጠበቅባቸውን ቀጣይ ሂደት ይፋ አድርገን እንደነበርም ይታወሳል (ቪዲዮውን በዚህ ሊንክ ማየት ይቻላል:

) ። በዕጣ የተለዩት ሃያ ሰዎች በቀጣይ ቀናት ውስጥ እንዲታከም የፈለጉትን ጉዳይ የሚያብራራ ምላሽ እንዲሰጡ በዚያው ቪዲዮ ላይ ጥያቄ ቀርቦ ነበር።

በመጀመሪያ የነበረው ዕቅድ በሚልኩት ማብራሪያ መሠረት  ከሃያው ውስጥ ትክክለኛ የአጥንት ህክምና የሚያስፈልጋቸውን እና በህክምና ሊድን የሚችል ችግር ያለባቸውን በመለየት እና በተጨማሪ ዕጣ አምስት ሠዎችን መርጠን የዕድሉ ተጠቃሚ ማድረግ የነበረ ቢሆንም፣ ከሃያው ውስጥ ሠባት ሠዎች ምላሽ እንዲሰጡ ከተጠየቁበት ከአምስት ቀናት አልፎ በሶስት ሳምንታት ውስጥ ምንም ምላሽ ስላልሰጡ "የደወል ምልክቱን (notification) መጫን" የሚለውን ቅድመ ሁኔታ ባለሟሟላታቸው ምክንያት ቪዲዮ መለቀቁን የሚገልፅ መልዕክት እንዳልደረሳቸው (በሌላ አነጋገር ቅድመሁኔታውን እንዳላሟሉ) በተዘዋዋሪ በመገንዘብ ከዕድሉ የተሰረዙ ሲሆን ፣ ከተቀሩት አስራ ሶስት ሰዎች ውስጥ ደግሞ አንዷ እህት ለቻሪቲ በሚል ለማሳከም የመረጠቻቸው ታካሚ ሁኔታ በተወሰነ ህክምና ሊድን የሚችል ሳይሆን በርካታ ዓመታት ክትትል የሚያስፈልገው ችግር በመሆኑ፣ ሌላኛው ባለዕድል ደግሞ የሁሉም ምላሽ እስኪጠበቅ ድረስ ለሶስት ሳምንታት ያህል መጠበቁ ስላስቆጣው እና "too late" የሚል መልዕክት በመላክ የዕድሉ ተጠቃሚ መሆን ባለመፈለጉ የተቀሩትን አስራ አንድ ሰዎች ያለተጨማሪ ዕጣ ተራ በተራ ህክምና እንዲያገኙ ለማድረግ ተወስኗል።

በመሆኑም ማብራሪያችሁን ልካችሁ ምላሽ የተላከላችሁ ዕድለኞች እንኳን ደስ ያላችሁ እያልን፣ እነዚህ 11 ታካሚዎች በሙሉ ዕድል ካገኙ በኋላ የሌላ ዙር ዕጣ ዕድል ለማስተዋወቅ የታቀደ መሆኑን ለማስታወስ እንወዳለን። በቀጣይ በሚኖረውን የነፃ ህክምና ዕድል ተጠቃሚ ለመሆን የምትፈልጉ ታካሚዎች ቻናሉ ላይ የሚለቀቁ መልዕክቶችን እንድትከታተሉ እየጠየቅን፣  በዚህ ዙር እየታከሙ ካሉት ዕድለኞች ውስጥ ፈቃደኛ የሚሆኑትን ብቻ (ያለማስገደድ እና ያለጫና ከተስማሙ ብቻ) ቪዲዮ እየቀረፅን የህክምናቸውን ሂደት እንዲያብራሩ የምናደርግ ይሆናል።
1.6K viewsedited  18:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 21:40:36
1.1K views18:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-25 11:31:04
የመውደቅ አደጋ ለደረሰባት ታካሚያችን በዚህ መልኩ የሠራነው የዳሌ መገጣጠሚያ ቅየራ በአጭር ጊዜ ዳግም ለመራመድ አስችሏታል።
1.6K views08:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-20 20:36:27
1.7K views17:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-17 22:22:40
1.8K views19:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-17 22:22:28 ለአመታት ተደብቆ የሚያድገው "ደስሞይድ" እጢ
—————————————————
ዶ/ር ሠዒድ መሐመድ (የአጥንት ስፔሻሊስት)
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የዛሬው ባለታሪክ የአርባ ዘጠኝ ዓመት ጎልማሳ ሲሆን እኔ ዘንድ ለህክምና የመጣው  ላለፉት ጥቂት ወራት እግሩ አካባቢ የመወጠር ስሜት እየተሰማው ስለነበረ "ለማንኛውም ልታየው" በማለት ብቻ ነበር።

ምርመራዎች ሲደረጉ ግን እግሩ ውስጥ ትልቅ መጠን ያለው ዕጢ እንዳለ ስለተረዳን የእጢውን ባህሪ እና ምንነት ከገለፅኩ በኋላ አሁን ያለበት ሁኔታ ቀዶ ህክምና የሚያስፈልግበት ደረጃ እንደሆነ ለታካሚው አስረዳሁት። ሆኖም ታካሚው ለመራመድም ሆነ የዕለት ተዕለት ኑሮውን ለመከወን ምንም ስላልተቸገረ እና እኔ ዘንድ የመጣውም ለወራት ያህል ዛሬ ነገ እሄዳለሁ እያለ ቆይቶ ሰሞኑን ስለተመቸው ብቻ እንጂ ለቀዶ ህክምና የሚያበቃ ችግር ይኖርብኛል ብሎ በፍፁም ስላልገመተ የምርመራ ውጤቱን ለመቀበል ተቸገረ።

በስተመጨረሻ ግን ውጤቱ ትክክል እንደሆነ፣ ምንም እንኳን ከውጪ የሚታይ ግልፅ እባጭ ወይም የከፋ የህመም ስሜት ባይኖረውም፣ በምርመራ ውጤቱ መሠረት እስከ 17 ሴንቲ ሜትር የሚደርስ ትልቅ ዕጢ ጡንቻው ውስጥ መኖሩ እንደተረጋገጠ አስረድቼው ፣ ሁኔታውን ስለተገነዘበ ለቀዶ ህክምና ዝግጁ ሆነ።  በዕርግጥም ዕጢው መጠኑ ከፍ ያለ መሆኑ ብቻ ሳይሆን፣ ለእግር በህይወት መቆየት እጅግ አስፈላጊ የሆኑ ዋና ዋና የደም ስሮች እና ነርቮችን ተጭኖ የነበረ በመሆኑ ቀዶ ህክምናውን ስናደርግ ከፍተኛ ጥንቃቄ አስፈልጎን የነበረ ቢሆንም፣ በስተመጨረሻ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቆ ምስሉ ላይ የሚታየው ዕጢ ያለምንም ተከታይ ጉዳት ሊወጣለት ችሏል።

ደስሞይድ ዕጢ ምንድነው?
————————————
ደስሞይድ ዕጢ ከአንድ ሚሊየን ሠዎች ውስጥ ከሁለት እስከ አራት ሰዎችን የሚያጠቃ የስስ ጡንቻ ዕጢ ሲሆን፣ ልክ እንደዛሬው ባለታሪካችን መኖሩ ሳይታወቅ ለረጅም ጊዜ ጥልቅ አካል ውስጥ ሊቆይ ይችላል።  ይህ ዕጢ የካንሰርነት ባህሪ የሌለው እና ወደ ካንሰር የመቀየር ዕድሉም ጠባብ እንደሆነ በበርካታ ጥናቶች የተስተዋለ ቢሆንም፣ እያደገ ሲሄድ ግን በዙሪያው ያሉ የነርቭ እና የደም ስሮችን በመጉዳት በሂደት ከፍተኛ መዘዝ ሊያስከትል ይችላል።

በመሆኑም ከሐኪም ጋር እየመከሩ የዕድገቱን ሁኔታ በመከታተል እንደ ሁኔታው ቀድሞ የተሻለውን የህክምና አማራጭ መወሰን እና ሊከተል የሚችልን ችግር ቀድሞ መቅረፍ ወሳኝ ነው።
—————————————————
Take home message: ሠውነት ላይ የሚሠማን የህመም መጠን የችግሩን መጠን ላያሳይ ይችላል!
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ለዚህን መሠል መረጃዎች በነዚህ አድራሻዎች ይከተሉን:

YouTube: " Doctor Seid"

የቴሌግራም ቻናል: https://t.me/patientstories

የፌስቡክ ገፅ: የአጥንት ህክምና/Orthopedic Surgery (https://www.facebook.com/EthioOrthopedics/)

ስልክ: 6194
1.7K viewsedited  19:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ