Get Mystery Box with random crypto!

የነፃ ህክምናው ሂደት … —————————————— ከዚህ በፊት የነፃ ህክምና ዕድል ለመስጠት የታቀደ | ♒Orthopedic Surgery in Ethiopia ♒

የነፃ ህክምናው ሂደት …
——————————————
ከዚህ በፊት የነፃ ህክምና ዕድል ለመስጠት የታቀደበትን ቪዲዮ በዚሁ ገፅ ላይ አጋርተናችሁ በርካቶች የዕድሉ ተጠቃሚ ለመሆን ጥያቄ አቅርባችሁ እንደነበረ ይታወሳል። በመሆኑም ሂደቱ የደረሰበትን ለገፃችን ተከታታዮች ማሳወቁ አስፈላጊ ስለሆነ እንደሚከተለው ተብራርቷል።

ማስታወቂያው ይፋ በተደረገበት ቪዲዮ ላይ (

) የዕድሉ ተጠቃሚ ለመሆን የቀረበው መስፈርት: ማስታወቂያው የተነገረበትን ቻናል "ሰብስክራይብ ማድረግ፣ የደወል ምልክቱን መጫን እና የዕድሉ ተጠቃሚ ለመሆን ፍላጎት እንዳለ መግለፅ" የሚል ነበር።

በገለፃውም መሠረት ሰብስክራይብ አድርገው የዕድሉ ተጠቃሚ ለመሆን የጠየቁትን በመለየት እና ከመሐል በዕጣ ሃያ ሰዎችን በመምረጥ ከሶስት ሳምንታት በፊት የዕድለኞችን ስም ዝርዝር እና የሚጠበቅባቸውን ቀጣይ ሂደት ይፋ አድርገን እንደነበርም ይታወሳል (ቪዲዮውን በዚህ ሊንክ ማየት ይቻላል:

) ። በዕጣ የተለዩት ሃያ ሰዎች በቀጣይ ቀናት ውስጥ እንዲታከም የፈለጉትን ጉዳይ የሚያብራራ ምላሽ እንዲሰጡ በዚያው ቪዲዮ ላይ ጥያቄ ቀርቦ ነበር።

በመጀመሪያ የነበረው ዕቅድ በሚልኩት ማብራሪያ መሠረት  ከሃያው ውስጥ ትክክለኛ የአጥንት ህክምና የሚያስፈልጋቸውን እና በህክምና ሊድን የሚችል ችግር ያለባቸውን በመለየት እና በተጨማሪ ዕጣ አምስት ሠዎችን መርጠን የዕድሉ ተጠቃሚ ማድረግ የነበረ ቢሆንም፣ ከሃያው ውስጥ ሠባት ሠዎች ምላሽ እንዲሰጡ ከተጠየቁበት ከአምስት ቀናት አልፎ በሶስት ሳምንታት ውስጥ ምንም ምላሽ ስላልሰጡ "የደወል ምልክቱን (notification) መጫን" የሚለውን ቅድመ ሁኔታ ባለሟሟላታቸው ምክንያት ቪዲዮ መለቀቁን የሚገልፅ መልዕክት እንዳልደረሳቸው (በሌላ አነጋገር ቅድመሁኔታውን እንዳላሟሉ) በተዘዋዋሪ በመገንዘብ ከዕድሉ የተሰረዙ ሲሆን ፣ ከተቀሩት አስራ ሶስት ሰዎች ውስጥ ደግሞ አንዷ እህት ለቻሪቲ በሚል ለማሳከም የመረጠቻቸው ታካሚ ሁኔታ በተወሰነ ህክምና ሊድን የሚችል ሳይሆን በርካታ ዓመታት ክትትል የሚያስፈልገው ችግር በመሆኑ፣ ሌላኛው ባለዕድል ደግሞ የሁሉም ምላሽ እስኪጠበቅ ድረስ ለሶስት ሳምንታት ያህል መጠበቁ ስላስቆጣው እና "too late" የሚል መልዕክት በመላክ የዕድሉ ተጠቃሚ መሆን ባለመፈለጉ የተቀሩትን አስራ አንድ ሰዎች ያለተጨማሪ ዕጣ ተራ በተራ ህክምና እንዲያገኙ ለማድረግ ተወስኗል።

በመሆኑም ማብራሪያችሁን ልካችሁ ምላሽ የተላከላችሁ ዕድለኞች እንኳን ደስ ያላችሁ እያልን፣ እነዚህ 11 ታካሚዎች በሙሉ ዕድል ካገኙ በኋላ የሌላ ዙር ዕጣ ዕድል ለማስተዋወቅ የታቀደ መሆኑን ለማስታወስ እንወዳለን። በቀጣይ በሚኖረውን የነፃ ህክምና ዕድል ተጠቃሚ ለመሆን የምትፈልጉ ታካሚዎች ቻናሉ ላይ የሚለቀቁ መልዕክቶችን እንድትከታተሉ እየጠየቅን፣  በዚህ ዙር እየታከሙ ካሉት ዕድለኞች ውስጥ ፈቃደኛ የሚሆኑትን ብቻ (ያለማስገደድ እና ያለጫና ከተስማሙ ብቻ) ቪዲዮ እየቀረፅን የህክምናቸውን ሂደት እንዲያብራሩ የምናደርግ ይሆናል።