Get Mystery Box with random crypto!

#መቐለ_ዩኒቨርሲቲ ' ተማሪዎቻችንን እንደገና ለመቀበል ዝግጁ ስንሆን ይፋዊ መግለጫ እንሰጣለን ' | አገልግል

#መቐለ_ዩኒቨርሲቲ

" ተማሪዎቻችንን እንደገና ለመቀበል ዝግጁ ስንሆን ይፋዊ መግለጫ እንሰጣለን " - ዶ/ር ፋና ሀጎስ (የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንት)

ከትላንት ምሽት አንስቶ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች መቐለ ዩኒቨርሲቲን የሚመለከቱ መረጃዎች እየተሰራጩ ይገኛሉ።

እነዚህ መረጃዎች ፦
- ዩኒቨርሲቲው ወደ መማር ማስተማር ስራው እዲመለስ መወሰኑ፣
- በጦርነቱ አቋርጦ የነበረውን ስራ ከመጪው ሳምንት አንስቶ እንደሚጀምር፣
- በመንግስት በኩል አስፈላጊው #በጀት እንደተለቀቀለት፣
- 24 ሺህ ነባር ተማሪዎችን በቀጣይ 4 ወር ትምህርት እንዲያጠናቅቁ እንደሚያደርግ
- ከመስከረም 2016 ጀምሮ አዲስ ተማሪዎችን እንደሚቀበል የሚገልፁ ናቸው።

ነገር ግን ይህ የተሳሳተ መረጃ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ኃላፊዎች እና ሰራተኞች ገልጸዋል።

መቐለ ዩኒቨርሲቲም ቢሆን በይፋዊ የፌስቡክ እና የትዊተር አካውንቱ ላይ ምንም አይነት መረጃ አልለጠፈም።

የተሰራጨውን መረጃ በተመለከተ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ፋና ሀጎስ ለ" ኢትዮጵያ ቼክ " መረጃ ማጣሪያ ድረገፅ በሰጡት ቃል ፥ ዩኒቨርሲቲው ስራ ለመጀመር ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በቅርበት እየሰራ ቢሆንም በዩኒቨርሲቲው ላይ የደረሰውን ጉዳት ለመጠገን የራሱን ጊዜና ሂደት እንደሚወስድ ተናግረዋል።

ዶ/ር ፋና " ዩኒቨርሲቲው ሥራውን ይጀምራል ነገር ግን በሚቀጥለው ሳምንት አይደለም ፤ በእርግጥ ይህን ለማድረግ ወራትን ይወስዳል " ሲሉ ተናግረዋል።

ዶ/ር ፋና እስካሁን መቐለ ዩኒቨርሲቲ ለተማሪዎች ጥሪ እንዳላደረገ ገልፀው " እኛ (ዩኒቨርሲቲው ወይም የትምህርት ሚኒስቴር) ተማሪዎቻችንን እንደገና ለመቀበል ዝግጁ ስንሆን ይፋዊ መግለጫ እንሰጣለን " ሲሉ አሳውቀዋል።

Credit : ethiopiacheck.org