Get Mystery Box with random crypto!

#ግንቦት_12 የመምህር ወመገስጽ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የእረፍቱ ቀን፣ የአባታችን የጻድቁ አቡነ | ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ

#ግንቦት_12

የመምህር ወመገስጽ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የእረፍቱ ቀን፣ የአባታችን የጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ፍልሰተ አጽም እና የእናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ የቃልኪዳን ዓመታዊ ክብረ በዓል ነወ።

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
ባሕረ ምስጢራት የሆነ የሰውን ፊት አይቶ የማያደላ "መምህር ወመገስጽ ዘኢያደሉ ለገጽ" (በርሱ ዘንድ ንጉሥ፣ ሐብታም፣ ደሃ፣ ነዳይ እኩል ነውና)፣ አፈ በረከት፣ አፈ መዐር (ማር)፣ አፈ ሶከር (ስኳር)፣ አፈ አፈው (ሽቱ)፣ ልሳነ ወርቅ፣ የዓለም ሁሉ መምሕር፣ ርዕሰ ሊቃውንት፣ ዓምደ ብርሃን (የብርሃን ምሰሶ)፣ የሐዲስ ኪዳን ዳንኤል፣ ሊቀ ዻዻሳት ዘበርትዕ (እውነተኛው)፣ ጥዑመ ቃል... እየተባለ የሚጠራው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እረፍቱ ነው።

#ቅድስት_ክርስቶስ_ሠምራ
ብፅዕት ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ ሰይጣንን ከፈጣሪ ጋር ልታስታርቅ በሄደች ጊዜ ከሲኦል ቅዱስ ሚካኤል እየተራዳት ብዙ ነፍሳትን ያወጣችበት የቃልኪዳን በዓል ነው።

#አቡነ_ተክለሃይማኖት
የአባታቸንና የኢትዮጵያ ፀሐይ የፃድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ግንቦት 12 ከደብረ አሰቦ ወደ ደብረ ሊባኖስ አጽማቸው የፈለሰበት (ፍልሰተ አጽም) ይከበራል።

አምላከ ቅዱሳን በቅዱሳኑ ጸሎት ልመናና ቃልኪዳን ሀገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ከጭንቀትና ከመከራ ይጠብቀን።.

@ortodoxtewahedo