Get Mystery Box with random crypto!

ኦርቶዶክስ መረጃ

የቴሌግራም ቻናል አርማ ortodox_merja — ኦርቶዶክስ መረጃ
የቴሌግራም ቻናል አርማ ortodox_merja — ኦርቶዶክስ መረጃ
የሰርጥ አድራሻ: @ortodox_merja
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.43K

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-04-02 22:14:08
ታዋቂው የፕሮቴስታንት ፓስተር በወላይታ ተጠመቀ
***

ታዋቂው የፕሮቴስታንት ፓስተር የሆነው በቀድሞ ስሙ ፓስተር ቢኒያም ተብሎ የሚጠራው

ጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት ሃዋርያዊ ተጋድሎ በፈጸሙበት እና የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስትያን 3ኛ ቅዱስ ፓትርያሪክ ከወጡበት

ወላይታ ደብረ መንክራት አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን በመጠመቅ "ፍቅረ ኢየሱስ" በሚል ስመ ክርስትና ሐብተ ወልድን ተቀብሏል።

እግዚአብሔር ይመስገን !!!

Kune Demelash kassaye -Arba Minch

#Share
@ORTODOX_MERJA
710 views19:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-28 11:18:04 + አቤቱ ቅጣኝ ነገር ግን እንዳታዋርደኝ! +

እግዚአብሔር ፍቅር ነው ፣ መሐሪ ነው ፣ ይቅር ባይ ነው፡፡ ፍቅር ይቆጣል ወይ? ይቅር ባይስ ይቀጣል ወይ? ብዙዎቻችን ስለ ክርስቶስ ሲነገረን መሐሪነቱና ፍቅሩ ብቻ ቢነገረን አንጠላም፡፡ ጨርሶ የማንፈራው እግዚአብሔር እንፈልጋለን፡፡ እንዲህ አታድርግ! የሚለን ሲመጣ ‘አትፍረድ’ እንላለን ፤ ቆይተን ግን የሰማዩን ዳኝም አትፍረድ ማለት ይቃጣናል፡፡ ቅጣት የሌለበት ክርስትና እንሻለን፡፡

ይህ ዓይነቱን ክርስትና ‘ጣፋጭ ክርስትና’ {የስኳር ክርስትና ይሉታል} ምንም ምሬት የሌለበት ሁሌም ማር ማር የሚል ሕይወት አድርገው ክርስትናን የሚሰብኩም ብዙ ናቸው፡፡ ‘አይዞህ ብትታመም ትፈወሳለህ ፣ ቤትህ ይሞላል ፣ ቀዳዳህ ይደፈናል ፣ ብትበድልም አትቀጣም’ ብቻ የሚሉ ስብከቶች የስኳር ክርስትና ስብከቶች ናቸው፡፡ ይህንን ብቻ የሚያጮሁ ሰዎች ክርስቶስ ‘የምድር ጨው ናችሁ’ ያለውን ትተው የምድር ስኳር ለመሆንና ዓለምን ለማስደሰት የሚፈልጉ ናቸው፡፡
በእርግጥ እግዚአብሔር ይቆጣል ወይ? አዎን ይቆጣል! እንዲህ ይላል መጽሐፉ

‘እግዚአብሔር ቀናተኛና ተበቃይ አምላክ ነው እግዚአብሔር ተበቃይና መዓትን የተሞላ ነው እግዚአብሔር ተቃዋሚዎቹን ይበቀላል፥ ለጠላቶቹም ቍጣውን ይጠብቃል። በቍጣው ፊት የሚቆም ማን ነው? የቍጣውንም ትኵሳት ማን ይታገሣል? መዓቱ እንደ እሳት ይፈስሳል፥ ከእርሱም የተነሣ ዓለቶች ተሰነጠቁ’ ናሆ 1፡1፣6
‘‘ከቍጣው የተነሣ ምድር ትንቀጠቀጣለች አሕዛብም መዓቱን አይችሉም’’ ኤር 10፡10
‘‘እኛ በቍጣህ አልቀናልና፥ በመዓትህም ደንግጠናልና’’ መዝ. 90፡7

እግዚአብሔር በተቆጣ ጊዜ የሚመልሰው የለም፡፡ ቅዱሳን የቁጣውን መጠን ስለሚያውቁ በትሕትና ይለምኑታል፡፡

ይሁንና መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እግዚአብሔር ቁጣ ደጋግሞ ቢነግረንም አንድ ሌላ ደስ የሚያሰኝ ነገርም ነግሮናል፡፡ የእግዚአብሔር ቁጣው ለዘላለም አይደለም፡፡ "ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" ይላል እንጂ "ቁጣው ለዘላለም ነውና" አይልም:: የእግዚአብሔር ቁጣ ጊዜያዊ ነው፡፡

‘መሐሪ ነኝና ለዘላለም አልቆጣም’ ኤር 3፡12
‘ቁጣው ለጥቂት ጊዜ ሞገሱ ግን ለሕይወት ዘመን ነው’ መዝ 29፡5
‘ጌታ ለዘላለም አይጥልም ቢያሳዝንም እንደ ምሕረቱ ብዛት ይራራል ፤ የሰው ልጆችን ከልቡ አያስጨንቅም አያሳዝንምም’ ሰ.ኤር 3፡31

የፈጣሪን የነነደ የቁጣ እሳት ማጥፋት የሚቻለን በዕንባ ነው፡፡ በደላችንን አምነን ቅጣት ይገባናል ነገር ግን መሐሪ ነህና ማረን ማለት ይገባል፡፡ ንጉሥ ዳዊት ‘አቤቱ በቁጣህ አትቅሠፈኝ በመዓትህም አትገሥፀኝ’ ብሎ የፈጣሪን ቁጣ አበረደ፡፡ /መዝ 38፡1/ ነቢዩ ኤርያስም ‘አቤቱ ቅጣኝ ነገር ግን እንዳታዋርደኝ በመጠን ይሁን እንጂ በቁጣ አይሁን’ ብሎ ተለማመጠ፡፡ ኤር 10፡24

አንድ ሠዓሊ በጣም ብዙ ደክሞ የተጠበበትን ሥዕሉን የፈለገ ቢበሳጭ ለረዥም ጊዜ ያንን ሥዕል ለመሳል የተጠበበትን ጥበብ አስቦ ሥዕሉን ወደ እሳት አይጨምረውም፡፡ አባ ጊዮርጊስ እንዲህ ሲል ይለምናል ‘ሠዓሊ ሥዕሉን ያጠፋል ወይ? [ጌታ ሆይ እኔን ስትፈጥር የተጠበብክበትን] የቀደመ ጥበብህን አስብ እንጂ! አስበህም ማረኝ! [ያጠፋዖኑ ለሥዕሉ ሠዓሊ ፤ ኪነተከ ዘትካት ኀሊ]

ይቅርታውን በንስሓ ለሚለምኑ ሁሉ ምሕረቱ ቅርብ ነው፡፡ በቀኝና በግራው ወንበዴዎች በተሰቀሉበት በዕለተ አርብ የግራው ወንበዴ ሲሰድበው ጌታ መልስ አልሠጠም፡፡ የቀኙ ወንበዴ ማረኝ ሲለው ግን ከአፉ ተቀብሎ በገነት ትሆናለህ አለው፡፡ ቁጣው የራቀ ምሕረቱ የበዛ እርሱ የራበው ሰው ለምግብ የሚቸኩለውን ያህል ይቅር ለማለት ይቸኩላል፡፡ ‘ምሕረትን ይወድዳልና ቁጣውንም ለዘላለም አይጠብቅም ተመልሶ ይምረናል ፤ ክፋታችንንም ይጠቀጥቃል ፤ ኃጢአታችንንንም በባሕሩ ጥልቅ ይጥለዋል’ ሚክ 7፡18

ልጆች ሳለን ጥፋት ስናጠፋ ከወላጆቻችን እንደበቃለን፡፡በተደበቅንበት ሰዓት ውስጣችን በፍርሃት ይርዳል፡፡ ‘ዛሬ ገደለኝ’ ‘ዛሬ መሞቴ ነው’ ብለን እንጨነቃለን፡፡ የሚደርስብንን ቅጣት እጅግ አጋንነን ከመፍራታችን የተነሣ መሬት ተሰንጥቃ ብትውጠን አንጠላም፡፡ በዚያ ሁሉ ጭንቀት ውስጥ ግን ወላጆቻችንም እስኪያገኙን ይጨንነቃሉ፡፡ እግዚአብሔርም እንዲህ ነው፡፡ አጥፍቶ በገነት ዛፎች መካከል የተሸሸገ አዳምን ወዴት ነህ ብሎ የፈለገ እርሱ እኛንም ይፈልገናል፡፡ አዳም ከገነት ሳይባረር ገነት ውስጥ እንደጠፋ ፈጣሪ ሳያባርረን ራሳችንን በኃጢአት ተሸማቅቀን ያባረርን እኛን ይፈልገናል፡፡ እርሱ ስለመጥፋትህ ይጨነቃል አንተ ‘ዛሬስ አይምረኝም’ ትላለህ፡፡

የሚገርመው በጥፋታችን ከተደበቅንበት ወላጆቻችን ካገኙን በኋላ ሁለተኛው ዙር ጭንቀታችን ‘ምን አጥፍተህ ነው የተደበቅከው’ መባል ነው፡፡ ጥፋታችንን ሲያውጣጡን እንንቀጠቀጣለን፡፡ ያጠፋነውን ስለምናውቀው ስንት እንደሚያስገርፈንም እናውቀዋለን፡፡ ‘ብትናገር ይሻላል? ግዴለህም!’ ብለው አግባብተውም አስፈራርተውም ወላጆቻችን ጥፋታችንን ያውጣጡናል፡፡ እየፈራን ያጠፋነውን ጥፋት ስንናዘዝ ግን ወላጆቻችን በጥፋታችን ቅጥል ብለው ‘አልመታህም ተናገር’ ያሉንን ረስተው የዱላ ዝናም ያዘንቡብናል፡፡ እግዚአብሔር ግን ጥፋትህን ስትነግረው ቁጣው የሚገነፍል አባት አይደለም፡፡
’’ኃጢአታችንን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነፃን የታመነና ጻድቅ ነው’ 1ዮሐ 1፡9

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
መጋቢት 18 2012 ዓ ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
284 views08:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-13 13:03:26 በጣም ምርጥ ቻናል በተመጣጣኝ ዋጋ 94500 Subscribers
7,000,000+ Views
Monitized የሆነ እና ከ5000$ በላይ የሰራ Strike Free
በሳምንት ከ1000$ በላይ መስራት ትችላላቹ አሁኑኑ ያናግሩን @Majesty_Yb
0912370195
763 views10:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-06 15:01:20                †               

በሕገወጥ መንገድ የተሾሙት ግለሰቦች በምእራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ስም ሹመትና ዝውውር እያደረጉ እንደሆነ ተገለጸ፡፡

የካቲት 27 ቀን 2015 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)

በሕገወጥ መንገድ የተሾሙት ግለሰቦች በመንግሥት ድጋፍ በምእራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት በአሉ አብያተ ክርስቲያናት ዝርፊያ መፈጸሙን መዘገባችን ይታወሳል ለዚህም ምንም አይነት እርምጃ በአለመወሰዱ ምክንያት አሁን ላይ ካህናትን በማፈናቀል እና የወረዳ ቤተ ክህነት የሥራ መደቦቸን የሀገር ስብከቱን ማሕተም በመጠቀም ሹመትና ዝውውር በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በዚህም የተነሳ የምእራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ በማለት በሚጠራው የሕገ ወጡ ቡድን አባል በሆነ ቄስ ታዳሳ ደሪቤ በተጻፈ ደብዳቤ የደብረ ንጉሥ መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን የስብከተ ወንጌል ኃላፊና ሒሳብ ሹም የነበሩትን ቄስ ሀሰቤ ታዳሳ በጡሎ እና ዶባ ቤተ ክህነት ወረዳዎች ተዛውረው በሥራ አስኪያጅነት እንዲሠሩ መሾሙን የማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት ዘግቧል።

[ TMC ]

         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬

Share ያድርጉት @ORTODOX_MERJA
2.0K views12:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-18 23:18:44 24,300 ዶላር ደርሷል።

በመላው ዓለም የምትገኙ ቅድሚያ ለጋሾች እናተው ናችሁ!!

አገር ቤት ያለነው መልዕክቱን በማጋራት የተግባር ሰው እንኹን!

ብዙዎች በበጎ ይነሱ ዘንድ ስክሪን ሻት ላኩልን እናጋራለን!!

https://www.gofundme.com/f/eotc-charity-fundraiser-united-we-stand?utm_campaign=p_cf+share-flow-1&utm_content=undefined&utm_medium=copy_link&utm_source=customer&utm_term=undefined

Yared Shumete - ያሬድ ሹመቴ

#ሼር
@ORTODOX_MERJA
278 viewsedited  20:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-17 19:01:34
             †             

[ የሰማዕታት ቤተሰቦች የሃይማኖት ጽናት ! ]

አባት

" በሰማዕትነት በመሞቱ እግዚአብሔር ይመስገን፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር መገናኘት ማለት ከሰው ጋር መገናኘት ማለት አይደለም፡፡ እኔ በበኩሌ የእርሱን ዕድል ባገኘሁኝና በሞትኩ ደስ ባለኝ፡፡ ግን የወለደ አንጀት ስለማይችል ያስለቅሳል እንጂ ከቅዱሳን ጋር እየሆነ ያ ሁሉ እየተመሰከረለት ... እኔ ደስተኛ ነኝ፡፡"

እናት

" ሳንበላ ሦስት ቀን አራት ቀን በሶ ጠጥተን የምንኖርለት እግዚአብሔር ... ቤቱ ሲሰበር ፣ ቤቱ ሲናድ ቆሞ ማየት አለበት ወይ ? እንኳንም ሞተ ... የኔ ልጅ በሃይማኖቱ እንኳንም ሞተ፡፡"

" እውነት እላችኋለሁ ፥ በእስራኤል እንኳ እንዲህ ያለ ትልቅ እምነት አላገኘሁም።" [ ማቴ.፰፥፲ ]


እንዲህ ያለ እምነትን መታደል እንደምን መታደል ነው? እንደምንስ መመረጥ ነው ! በዓለም ዙሪያ የምንገኝ ኦርቶዶክሳውያን የተዋሕዶ ልጆች የቤት ሥራ ይጠብቀናል፡፡ ያለ ረዳት ፣ ያለ ጧሪ የቀሩትንና ከእግዚአብሔር በቀር ረዳት ወገን የሌላቸውን እኚህን የሰማዕታት ቤተሰቦች የመጦር የመደገፍና የመርዳቱ ኃላፊነት የእኛ ነው፡፡

የሰማዕታቱ በረከተን እንድንካፈል የእግዚአብሔር ፈቃዱ ይሁን፡፡

          †             †             †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬

@ORTODOX_MERJA
720 viewsedited  16:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-17 18:24:32
ሰበር ዜና!

ቄሱን በጥፊ የተማታው የፖሊስ ባልደረባ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተሰምቷል።

#ሼር_አድርጉት

@ORTODOX_MERJA
1.3K views15:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-17 18:23:40
ልጅ ቢኒ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርቦ ነበር:: ፍርድቤትም በ5000 ብር ዋስ እንዲፈታ ወስኖለታል:: ነገር ግን ይግባኝ ተጠይቆበት ዛሬ ሳይፈታ ለሰኞ ተቀጥሯል ተብሏል::

"የዘገየች ፍትሕ እንደተነፈገች ትቆጠራለች::"

ስለ ቤተ ክርስትያን በመናገራቸው የታሰሩትን በስምምነቱ መሰረት ወንድም እህቶቻችንን ፍቱልን
.....*****.....
624 views15:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-16 00:28:47
የተሰደዱት ብጽአን አባቶች ወደመንበረ ክብራቸው ሲመለሱ የጀግና አቀባበል በማድረግ ጠላት የፍቅርህን ልክ ያይ ዘንድ እንዘጋጅ።
***

እግዚአብሔር ይመስገን ።

ከእዚህ ቀድሞ ከሚያገለግሉት ሀገረስብከት "በአስቸኳይ እንድትወጡ" ተብለው ከመንበራቸው እንዲሰደዱ የተደረጉ አባቶች ወደ ቀደመው የምድባ ሀገረስብከታቸው ይመለሳሉ።

ይህን ጊዜ ድንቅ በሆነ ሰማያዊ ሠልፍ እና ድምቀት ምን ያህል መንጋው እረኛዋን እንደናፈቀ እና እንደሚያከብር መግለጥ ያስፈልጋል።

የበጎችም እረኛ ማን እንደሆነ በግልጥ ማሳዬት በጎ ነው።

*** ጅማ
*** ሻሸመኔ
*** ነቀምት
*** በኖ በደሌ

@ORTODOX_MERJA
206 views21:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-15 18:38:33
ሰበር ዜና

በሶስቱ አባቶች የተሾሙ የጨረቃ ጳጳሳት ወደ ቀደመ አገልግሎት እንዲመለሱ (ጵጵስና የተሾሙት ጵጵስናቸው እንዲሻር) ተወሰነ።
674 viewsedited  15:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ