Get Mystery Box with random crypto!

አጭር አስተማሪ ታሪክ , አንድ ሰው ነበር በባህር ብቻውን በመርከብ እየተጓዘ በመዓበል ተመታና መር | ተዋህዶ ሃይማኖቴ

አጭር አስተማሪ ታሪክ
,
አንድ ሰው ነበር በባህር ብቻውን በመርከብ እየተጓዘ በመዓበል ተመታና መርከቡ ተሰባብራ በባህሩ ሰመጠች ሰውዬው እንደምንም እራሱን
አድኖ አንድ ደሴት ላይ ያርፍና ጎጆ ነገር ሰርቶ ለቀናት ለብቻው እዛች ደሴት ላይ ይኖራል…… ምግቡን ዓሳ አያጠመደ እየተመገበ ብዙ ቆየ።
አንድ ቀን ዓሳ ሊያድን ወደ ባህሩ እየሄደ
በማሃል እዛች ባህር ላይ ጭስ ሸተት ዞር ብሎ ሲያይ ያቺ ጎጆው እየነደደች ነው……እየሮጠ ቢመለስም ጎጆዋን ሊያድናት አልቻለም ለካ ዓሳ
ለማብሰል ያቀጣጠለው እሳት ተያይዞ ጎጆውን አንድዷታል አለቀሰ ፈጠሪውን ወቀሰ እንዴት እዚህ ባህር ላይ ብቻዬን ጥለሀኝ ከቤተሰቦቼ ነጥለሀኝ
ስታበቃ በስንት ልፋት የሰራኋትን ጎጆ
ታቃጥልብኛለህ ብሎ አለቀሰ አማረረ……
ከደቂቃዎች በኃላ አንድ ድምፅ ሰማ ወደ ድምፁ ፊቱን ሲያዞር አንድ ትልቅ መርከብ አየ ተደሰተ…… የመርከቡ ሰዎች መጥተው ጭነው ወሰዱት
ከዚያም ለመርከቡ ሰዎች ጠየቃቸው! እንዴት አገኛቹኝ እዚህ አካባቢ እዚህ ባህር ላይ ማንም አይመጣም እኮ እናንተ እንዴት አገኛቹኝ? አላቸው……መርከበኞቹም እኛማ በዛኛው በኩል
ዞረን እየሄድን ነበር ከዚህ በኩል ጭስ አየንና እዚህ ሰዉ ይኖራል ብለን መጣን አንተ አገኘን አሉት። አቤት ጌታዬ ለካ ከዚህ ከስቃዬ ልታውጣኝ ፈልገህ ነው ትንሿ ጎጆዬን ያፍርስከው ወደ ትልቁ
ቤት ልትውሰደኝ ነው። አለ ::
አንዳዴ የሆነ ነገር ስናጣ ሲበላሽብን ሰውንም ፈጣሪንም ስናማርር እንኖራለን ግን ከጣነው ነገር ከጎደለብን ነገር ጀርባ ብዙ ጥሩ ነገር ልናገኝ እንደምንችል እንዘነገለን በችግራችን ጊዜ መጣጋት
ያለብንን አንድዬን እንረሳዋለን ከዚያም አልፈን የሁሉ ነገር ፈጣሪውን እንኮንነዋለን። ያጣነውን የሰጠን አንድዬ! አእምሮችን ከሚያስበው በላይ ሊሰጥህን እንደሚችል ማመን አለብን።