Get Mystery Box with random crypto!

ኦርቶዶክሳዊ ህይወት

የቴሌግራም ቻናል አርማ orthodoxy_life — ኦርቶዶክሳዊ ህይወት
የቴሌግራም ቻናል አርማ orthodoxy_life — ኦርቶዶክሳዊ ህይወት
የሰርጥ አድራሻ: @orthodoxy_life
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 11.43K
የሰርጥ መግለጫ

''ኦርቶዶክስ ክርስቶስ ያሰባት ፣ ሐዋርያት የሰበኳት ፣ አባቶች የጠበቋት'' ቅዱስ አትናቴዎስ
ኦርቶዶክሳዊ መንፈሳዊ ትምህርቶች የሚያገኙበት ቻናል!

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-06-22 19:18:08
ያላየኹት ግን የሚያየኝ
ያልሰማኹት ግን የሚሰማኝ
ያልፈለኩት ግን የሚፈልገኝ
ያልጠበቅኹት ግን የሚጠብቀኝ
ያላወቅኹት ግን ያወቀኝ
ያልተመኘሁት ግን የታመነልኝ
.
.
.
እኔ ሳፈርስ እርሱ ሲጠግን
እኔ ስንድ እርሱ ሲሰራ
እኔ ስጥል እርሱ ሲያነሳ
.
.
.
እንዳልጠፋበት ጥፋቴን የታገሰ
እንዳልሸሽ ማባባልን የወደደ
እንዳልርቅ አብዝቶ የሚጠጋኝ
.
.
.
ማን እንደክርስቶስ ? ከእኔ ኃጢአት ይልቅ የእርሱ ፍቅር እጅግ ይበልጣል ምክንያታዊም ነው።
2.0K views16:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-18 12:44:51
ቅዱሳን አንተን ባወቁበት መጠን አውቅህ ዘንድ እሻለሁ የቅዱሳኑ ንፅህና ግን በእኔ ዘንድ የለም። እጠጋለው ኀጢአቴም ዳግመኛ ታርቀኛለች እጠጋለው ኀጢአቴም ዳግመኛ ታርቀኛለች።አቤቱ ጌታዬ ሆይ አደከመቺኝ አንተን በፍፁም ንፅህና አፈልግህ ዘንድ ከለከለቺኝ።ደክሞኝም ፈፅሜ እንዳልተውህ ያቀመስከኝ የፍቅርህ ጣዕም ትዝ ይለኛል። አቤቱ ተጨነኩ አንተስ እስከመቼ ዝም ትላለህ? እስከመቼስ ለፈቃዴ ትተወኛለህ?...

አቤቱ አንተን እንደወደዱህ እንደ ቅዱሳንህ ከፈቃዴ እንድሰዋልህ ቅድስት የምትሆን በጎ ጭካኔንን አስጨክነኝ።

“ከፈቃዴ እሠዋልሃለሁ”
— መዝሙር 54፥6
2.7K views09:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-02 15:11:29
ኃጢአት መስራት ከሚያስጠሉ አጋንት ጋር መነጋገር ፣መብላት ፣መጠጣት ፣ መጓዝ ፣መተኛት ..ነው ፤ እጅግ ቆንጆ ነኝ ብሎ የሚያስብ ሰው ኃጢአት ሲሰራ የሚውለው ከሚቀፉ አጋንታት ጋር ነው።

ቆንጆስ ከክርስቶስ ጋር የሚውል ለክርስቶሰም ያደረ ነው !
2.1K views12:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-21 19:57:07
ክርስቶስን የምትፈራ ሴት ጠቢብነቷ የላቀ ነው ፤ ክርስቶስን የምትወድ ሴት ልቧ የእውነተኛ መውደድ ነው ፤ክርስቶስን የምትጠራ ሴት ንግግሯ የሕይወት ነው ፤ክርስቶስን የምትይዝ ሴት የማይሰበር ጥንካሬ ባለቤት ናት ፤ ክርስቶስን ወዳ የምታስወደድ ሴት ደግሞ መዳኛ ናት ፤ ክርስቶስን በምትወድ ሴት ለክርስቶስ መሸነፍ እንጂ ከክርስቶስ መጣላት የለም ።

#አውሎግሶን
813 viewsedited  16:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-05 10:25:27
"ሁሉን የያዘውን ያዙት፤ ሁሉን የሚገዛውን አሠሩት፤ የህያውን አምላክ ልጅ አሠሩት፤ በቁጣ ጎተቱት፤ በፍቅር ተከተላቸው። በሚሸልተው ፊት እንደማይናገር እንደ የዋህ በግ በኋላቸው እየተከተለ ወሰዱት፤ ሊቃነ መላእክት በመፍራት እና በመንቀጥቀጥ ከፊቱ የሚቆሙለትን በአደባባይ አቆሙት፤

ኃጢአትን ይቅር የሚለውን ኃጥእ አሉት፥ በመኳንንት የሚፈርደውንም በእርሱ ፈረዱበት፤ ለሱራፌል ዘውድ የሚያቀዳጃቸውን የሾህ ዘውድ አቀዳጁት፤ ለኪሩቤል የገርማ ልብስ የሚያለብሳቸውን ለመዘበት ቀይ ግምጃ አለበሱት፤ ኪሩቤል በእሳት ክንፍ ተሸፍነው በፊቱ የሚሰወሩለትን እርሱን ክፉ ባሪያ አሥሮ ፊቱን ጸፋው፤ የመላእክት ሠራዊት በፍጹም መደንገጥ የሚሰግዱለት እየዘበቱበት በፊቱ ተንበረከኩ፡፡

ይህን ያህል ትህትና እንደምን ያለ ትህትና ነው? ይህን ያህል ትእግስት እንደምን ያለ ትእግስት ነው? ይህን ያህል ዝምታ እንደምን ያለ ዝምታ ነው? ይህን ያህል ቸርነት እንደምን ያለ ቸርነት ነው? ኃያል ወልድን ፍቅር ከዙፋኑ ሳበው እስከ ሞትም አደረሰው በደል የሌለበትን እንደበደለኛ ሰቀሉት፡፡ ህይወትን የሠራውን ከበደለኞች ጋር ቆጠሩት፤ አዳምን የሠሩ እጆች በመስቀል ቀኖዎት ተቸነከሩ፤  ወዮ በገነት የተመላለሱ እግሮች በመስቀል ተቸነከሩ፡፡

ወዮ በአዳም ፊት የህይወት እስትንፋስን እፍ ያለ አፍ ከሃሞት ጋር የተቀላቀለ የኮመጠጠ መፃፃን ጠጣ፤... ወዮ የወልድን መከራውን የሚናገር ምን አፍ ነው? ምን ከንፈር ነው? ምንስ አንደበት ነው? የፍቁሩ የጌታ ህማማት በተነገረ ጊዜ ልብ ይለያል፤ ህሊናም ይመታል፤ ነፍስም ትንቀጠቀጣለች፤ ሥጋም ይደክማል የማይሞተው ሞተ፤ ሞትን ይሽረው ዘንድ ሞተ፤ ሙታንን ያድናቸው ዘንድ ሞተ። የምትወዱት ሰዎች ፈጽሞ አልቅሱለት፡፡"

/ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ/
925 views07:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 00:28:27
የምንበረታው ለምን ይሆን?
|
"ከቅዱሳን ሁሉ ጋር ስፋቱና ርዝመቱ ከፍታውም ጥልቅነቱም ምን ያህል መሆኑን ለማስተዋል፥ ከመታወቅም የሚያልፈውን የክርስቶስን ፍቅር ለማወቅ ትበረቱ ዘንድ፥ እስከ እግዚአብሔርም ፍጹም ሙላት ደርሳችሁ ትሞሉ ዘንድ" (ኤፌ 3: 18-19)

https://t.me/orthodoxy_life
120 viewsedited  21:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-22 08:43:52
"A man dreams of a complete woman.

A woman dreams of a complete man.

But they do not understand that God created them so simple to make each other complete." ~ Dostoevsky
625 views05:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-26 21:01:58 ዓይን የሌለው እግር ፣ እግር የሌለው ዓይን!

አንድ ዓይነ ሸውራራ ሰውዬ መንገድ ሲያቋርጥ ሳያስብ በድንገት ፊት ለፊት ይመጣ የነበረው ሰው ገፍቶት ጣለው ። በዚህ ጊዜ ተናደደና “ሰማህ ወንድሜ ! ምነው የምትሄድበትን ብታይ !” ቢለው ፤ ተጋፊውም ሰውዬ፡- “ምነው አንተስ ወደምታይበት ብትሄድ” ብሎ መለሰለት ይባላል ።

አንዱ የሚሄድበትን አያይም ፣ ሌላውም ወደሚያየው አይሄድም ። በዚህ ምክንያት ግጭቶች ይፈጠራሉ ። እግሩ የሚጓዝ ዓይኑ ግን የማያይ ብዙ ሰው አለ ። ይህ ሰው እግሩ በመጓዙ ብቻ ልቡ ቢተማመንም ዓይኑ ባለማየቱ ግን ሌላውን ገፍትሮ ይጥላል ፣ ወደ ገደልም ይገባል ። ሌላኛውም የሚያየውና የሚሄድበት ተለያይቶበታል ። የሚያየው ሌላ ነው ፣ የሚሄደው ግን ወዳላየው ነው ። የሚሄዱበትን የማያዩ ግብታውያን ናቸው ። የዘራፍ አብዮት አራማጆች ናቸው ። ያለ ርእሱ የሚጠቅሱ ፣ በብሔሬማ አትምጣብኝ ፣ በባንዲራዬ ድርድር የለኝም ፣ ሃይማኖቴንም አላስነካም ፣ በእመቤቴ ቀልድ የለም ፣ በጌታ አልደራደርም በማለት የተነሣው ጉዳይና የሚመልሱት መልስ ፍጹም የተለያየ ነው ። እንኳን የሰሙትን ነገር የሚናገሩትንም አያስተውሉትም ። ብሔር ማለት ምን ማለት ነው ? ባንዲራ ማለትስ ? ጌታስ ማነው ? ቢባሉ መልስ የላቸውም ። እየተጓዙ ነው ። የሚጓዙበትን እንዲያውቁት ሲነገራቸው ግን ፈቃደኛ አይደሉም ። “ምርምር ማብዛት ያሳብዳል” ይላሉ ። እንኳን ለምርምሩ ለሀሁ አልደረሱም ። የሚያውቁት አንድ ጥቅስ አለ ፣ እርሱን ሁሉ ቦታ ይጠቅሱታል ። መጽሐፉ አይልም ይላሉ ። መጽሐፉ የሚለውን አያውቁም ። ሕገ መንግሥቱ አይፈቅድም ይላሉ ፣ ሕገ መንግሥቱ ስለዚያ ነገር የሚተነፍሰው ምንም ነገር የለም ። ሁሉን ማርከስ ፣ ሁሉን መከልከል ፣ የሚቻልበትን ሳይሆን የማይቻልበትን ነገር መፈለግ የእውቀት መለኪያ ያደርጉታል ።

እነዚህ ሰዎች የሚሄዱበትን አያዩም ። ስለዚህ ይጋጫሉ ። አገር የጋራ ሳለ የእኔ ብቻ ነው ብለው ያስባሉ ። ሃይማኖት ፍቅር ሳለ “ኧረ ጎራው ተነሥ” ይላሉ ። ለማወቅ አይፈቅዱም ። ነገር ግን ደፋር ሃይማኖተኛ ናቸው ። ደፋር ፖለቲከኛም ናቸው ። ለመማር አይመጡም ፣ “ችግር ካለ ጥሩኝ” ይላሉ ። ራሳቸውን እንደ እሳት አደጋ ሠራተኛ ፣ እንደ አድማ በታኝ ፖሊስ ይቆጥራሉ ። በግርግር ቢሞቱ ታሪካቸው ከአርበኞች ጋር እንደሚነሣ ፣ ሲኖዶስ ተቀምጦ የቅዱስነት ማዕረግ እንደሚሰጣቸው ያስባሉ ። ሞቅ ሞቅ ሲል ደስ ይላቸዋል ። ዓይናቸውን ጨፍነው የሚነዱ ፣ ለተከተላቸው ሰው ኃላፊነት የማይሰማቸው ፣ ቀጥሎ ምን ይሆናል ? በዚህ ንግግሬ ምን ይፈጠራል ? የሚል ልቡና የራቃቸው ሰዎች ናቸው ። የሚሄዱበትን አያዩም ። ያየም ቢነግራቸው አይሰሙም ።

የሚሄዱበትን የማያዩ ሰዎች ብዙ እውቀት ጠል የሆኑ ሰዎችን ማስከተል ይችላሉ ። መምህር ኤስድሮስ፡- “ከመሃይም አትጣላ ፣ ደጋፊው ብዙ ነው ያሸንፍሃል” ብለዋል ። እነዚህ የሚሄዱበትን የማያዩ ሰዎች “አድማ ይሰምርልኛል” በማለት በጽድቁ ቀርቶ በኃጢአቱ ይመካሉ ። ክፋት የምስክር ወረቀት ቢኖረው ይንበሸበሹ ነበር ። የሰሙትን ቁምነገር ከማሰላሰል ቀድሞ ለማስተላለፍ ፣ ከመኖር ያንን ተናገሮ አዋቂ መባልን ይፈልጋሉ ። በሚወስዱት እርምጃ ቤተሰባቸው ምን ጉዳት እንደሚደርስበት ለማሰብ ጊዜ የላቸውም ። እብደታቸውን በብዙኃኑ አጸድቀው ቢሳደቡ “ተናዶ ነው ፣” ቢያዋርዱ “ልማዱ ነው ተዉት” ተብለው ቅድመ ይቅርታ አግኝተው የሚኖሩ ናቸው ። የሚናገሩትን ዓለም ሁሉ ይስማልኝ ይላሉ ። የሰማም እየመሰላቸው በደስታ ይሞላሉ ። ዓለም ግን ኢትዮጵያ የምትባል አገር መኖሯን ለማወቅ እንኳ ይቸገራል ። ኢትዮጵያዊ ነኝ ስንል እንኳ ግር የሚላቸው ፣ አፍሪካ ስንላቸው ኦ ብለው የሚሰሙን አያሌ የዓለም ሕዝቦች ናቸው ። ለራሳችን የሰጠነው ግምት ትልቅ ነው ። እንኳን አማራነትና ኦሮሞነታችንን ኢትዮጵያዊነታችን የማያውቅ የዓለም ሕዝብ አያሌ ነው ። እነዚህ የሚሄዱበትን የማያዩ ሰዎች የሚያዳምጣቸው ሰው ከኢትዮጵያውያን እንኳ ሦስት ፐርሰንት የማይሞላ ነው ። እነርሱ ሲያስነጥሱ ግን ዓለም ሁሉ “ይማርህ” የሚላቸው ይመስላቸዋል ። አዎ የሚሄዱበትን አለማየት ግጭት ያመጣል ።

የምናምነውን ነገር ማወቅ ቀዳሚ ሲሆን ለዚያ ነገር መታመንም ተከታይ ነገር ነው ። ያለ እውቀት የሚደረግ ነገር በመጀመሪያ ኃጢአት ነው ። ሁለተኛ ወደ እውነተኛ እምነት አያደርስም ። የሚሄዱበትን የማያውቁ ሰዎች ስለሁሉም ነገር የሚመለከታቸው ይመስላቸዋል ። ስለዚህ ርእስ ይዘው እገሌ ትዳሯን ፈታች ፣ እገሌ ባለመውለዱ ምክንያት ሚስቱን ተወ ይላሉ ። ከእውቅ ሰዎች ጋር ያለን ግንኙነት ከሙያቸው እንጂ ከኑሮአቸው ጋር አይደለም ። ትልቁ ችግራችን ድንበራችንን አለማወቃችን ነው ። የትኛውም ሰው የቱንም ያህል ቢቀርበን የግል ሕይወት እንዳለው ማመንና መቀበል አለብን ። እርሱነቱን እንጂ ነጻነቱን መወዳጀት አይገባንም ። የሚሄዱበትን የማያውቁ ሰዎች የሚመለከታቸውን ርእስ አያውቁትም ። ሰው ሲያዳምጣቸው በርግጥ እንደ አዋቂ የቆጠራቸው ይመስላቸዋል ። ሰው ግን የሚሰማቸው ቀጥተኛ የሆነው ኑሮ ሲሰለቸው ለመዝናናት ብሎ ነው ። የሚሰማቸውም የእብደታቸው ልኩ ምን ያህል እንደ ደረሰ ሊገመግም ነው ።
“አባቴ” ይላቸዋል ሞኙ ።
ሽማግሌውም፡- “አቤት” ይሉታል ።
“ሰው ሁሉ ይወደኛል” አላቸው ።
እርሳቸውም፡- “አይ ልጄ ጅልን ማን ይጠላዋል?” ብለህ ነው አሉት ይባላል ።

ወደሚያዩበት የማይሄዱ ብዙ ሰዎች አሉ ። የባከነ እውቀት ማለት ይህ ነው ። ተምሮ ወገንን መሰብሰብ ሲገባ ሕዝብ መበተን ፣ ተመራምሮ አገር መጥቀም ሲገባ ትውልድን መበከል ይህ የባከነ እውቀት ነው ። የሚያዩት ክርስቶስን ፣ የሚሄዱት ግን ወደ አረመኔነት የሆነ ብዙ ሰዎች አሉ ። “ክርስቶስን ወደድኩት ፣ ክርስቲያኖችን ግን ጠላሁ” የተባለው ለዚህ ነው ። በእግዚአብሔር ቤት ከዓለም ስለመውጣታቸው የሚያወሩ ብዙ ሰዎች አሉ ። ዓለም ግን ከልባቸው አልወጣችምና ይኸው የእግዚአብሔርን ቤት ያምሳሉ ። “ጀበና ጥዬ ነው የመጣሁት” በማለት ከጣዖት ቤት መምጣታቸውን ዘላለም የሚተርኩ ሰዎች አሉ ። ጀበናው ግን ከእጃቸው እንጂ ከልባቸው አልወደቀም ። ቅንጣት ፍቅር ለሰው የሌላቸው ፣ በአረመኔነት የሚወዳደሩ ፣ የጌታዬ ፍቅር እያሉ ነገር ግን ዘረኝነትን የሚያራምዱ ወደሚያዩት የማይሄዱ ናቸው ። እነዚህ ሰዎች ከሌላው ጋር ሲጋጩ ይኖራሉ ። ሰላም የላቸውም ፣ ከሁሉ ሰው ጋር ይነታረካሉ ። ጠባቸውን መንፈሳዊ ያደርጉታል ። “ስለ ጌታ ብዬ ተሰደድሁ” ይላሉ ። ያሳደዱአቸውን ሲረግሙ ይውላሉ ። ያለቀሱ እንደሆነ እንባቸው ከአዲሱ የዓባይ ግድብ ይልቃል ። “የውሸታም/የዓባይ እንባ ባቄላ ባቄላ ያህላል” ይባላል ። ቀላል ልብ ያላቸው ሰዎች በእንባቸው ይማረካሉ ። በግላቸው ሲጸልዩ እንባ የማይመጣላቸው ፣ ሰው ፊት ሲቆሙ ግን በእንባ የሚታጠቡ ብዙ ናቸው ። እግረ መስቀሉ ሥር ቆመን ያልመጣ እንባ ፣ ሰው ፊት ስንቆም ከመጣ የልመና ስልት እንጂ የክርስትና ፍቅር አይደለም ።

አዎ ይህች ዓለም የግጭት ስፍራ የሆነችው የሚሄዱበትን በማያዩ እውቀት ጠሎችና ያወቁትን በማይኖሩበት የአፍ አማኞች ነው ። ዓይን የሌለው እግር ወደ ገደል ይሄዳል ፣ እግር የሌለው ዓይን ሲመኝ ይኖራል ።  ጌታ ሆይ ወዳሳየኸን ዕለት ዕለት መጓዝ ይሁንልን ።

ተቀላቀሉን፦
https://t.me/orthodoxy_life
1.0K views18:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-06 16:18:45
እስከ መቼ አትምረንም ?

ጌታ ሆይ የምንጠብቀው የሚጠብቀን ካንተ በቀር ማነው ?

ቸር ሆይ! ያለንን ሁሉ እየተነጠቅን የሌለንን የምንናፍቀው ምስኪኖች ፣ ካንተ በቀር ሰጪአችን ማነው?

ወጋገን አየን ስንል የሚጨልምብን ፣ ከእህል ረሀብ ወደ ፍቅር ረሀብ የተሸጋገርን ካንተ በቀር ተስፋችን ማነው ?

ፍቅር ጌታ ሆይ ! የማልቀሻ ስፍራችን ፣ ሸክም የምናራግፍባት ደጀ ሰላማችን ፣ ደምን በይቅርታ ፣ በደልን በፍቅር የምንለውጥባት አንድ ዓይናችን የሆነች ቤተ ክርስቲያን ስትጎዳ ካንተ በቀር የሚያድናት ማነው ?

ገዳይም ሟችም እኛው ሁነን ፣ ፉከራም ልቅሶም ሲጠፋብን ካንተ በቀር ወደ ሕሊናችን የሚመልሰን ማነው?

አንዲት ቤተ ክርስቲያን አንድ እንድትሆን ፣ ሕመምና ልቅሶአችን ዳርቻ እንዲያገኝ እንማጸንሃለን! አማኑኤል ሆይ! በክንፍህ መዘርጋት አንተ ጋርደን ። ከልቅሶም ልቅሶ አለውና የቤተ ክርስቲያን ደጆች በምሕረት ይከፈቱልን ። እውነተኛው አዳኝ ክርስቶስ ሆይ ! አደባባይ የቆምህላት ቤተ ክርስቲያን አደባባይ ቆማለችና አንተ አስባት ! ለዘላለሙ አሜን !

መልዕክቱን ያካፍሉ(Share)!

https://t.me/orthodoxy_life
2.2K viewsedited  13:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-05 00:38:31 የካቲት 5 ሰልፍ የጠራው ቅዱስ ሲኖዶስ ብቻ አይደለም:: ሰልፉን የጠራው ዛሬ ጠዋት ለቅድስት ቤተክርስቲያን ክብር በግፍ የተሠዋው ሰማዕት ደም ድምፅ ነው::
ዛሬ ቤታቸው ሳይገቡ እህል ሳይቀምሱ ቤተክርስቲያናቸው ውስጥ ውለው በስናይፐር የተመቱ ምእመናን ደም እኔና አንተ ክርስትና ለተነሣንባት ኃጢአታችንን በንስሓ ለምናራግፍባት የምንቆርብባት የምንዳርባት ስንታመም የምንጠመቅባትና ስንሞት የምንቀበርባትን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንዳናጣ ብለው ነው::
ቤተ ክርስቲያን ለኢትዮጵያ ያልሆነችው የለም:: ትምህርት ሚኒስቴር ሆና ከድንቁርና ጤና ሚኒስቴር ሆና ከበሽታ መከላከያ ሚኒስቴር ሆና ከቅኝ ግዛት የቱሪዝም ሚኒስቴር ሆና ከተራነት ኢትዮጵያን የታደገች ቤተ ክርስቲያን ናት::
ውለታዋ ተረስቶ የተሳዳቢዎች አፍ መፍቻ የሐሰተኞች ትንቢት መለማመጃ ሆና በንዋየ ቅድሳትዋ ተቀልዶ በከበሮዋ ተጨፍሮ ዕረፍት እንድታጣ ሆና መቆየትዋ ሳያንስ አሁን ደግሞ በግልፅ ተዘምቶባታል::
ቅዱስ ሲኖዶስ በቀጣዮቹ የምህላ ቀናት ያቀረበው ቅድመ ሁኔታ ካልተፈጸመ እንደሚካሔድ ያወጀው የጾም አዋጅና የካቲት 5 የጠራው ሰልፍ አባቶቻችን አባት ሆነው የተገኙበት ነው:: ልጆች ሆነን መገኘት የእኔና አንተ ፋንታ ነው:: ሕጋዊነትዋን ይዛ በሰላማዊ መንገድ የጠራችው ተቃውሞ ነውና የተሻለው መንገድም ይኼ ነው:: ከዚህ ቀደም ተጀምሮ የቀረ ሰልፍ ምን ዋጋ እንዳስከፈለን እናውቀዋለን:: አሁን በምንም ወደ ኋላ ማለት የለብንም:: በጎበዝ አለቃ መመራት በተባራሪ ወሬ መነዳት ትተን ከቤተ ክርስቲያናችን ጎን እንቁም:: ጉዳዩ የሐዋርያዊው ቅዱስ ሲኖዶስ ልዕልና ጉዳይ ሆኖ ሳለ የዘርና የቋንቋ ጉዳይ ለማድረግ የሚጥሩ ሰዎችን ጆሮ ባለ መስጠት በማያምኑባት ቤተ ክርስቲያን ውድቀትዋን ተመኝተው የሚሳደቡ እነ "ብጥብጥ አማረኝ"ን በቻልነው ሁሉ ብሎክ በማድረግ ጆሮአችንን ለቤተ ክርስቲያን ብቻ እንሥጥ::
ድርድር ሽምግልና ወዘተ የሚሉ የማዘናጊያ ሃሳቦች ፈጽሞ ተቀባይነት የላቸውም:: ተጽእኖ ፈጣሪ ሰዎች እጃችሁን አስገቡ ብትባሉም እንኳን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን አክብራችሁ እጃችሁን ሰብስቡ:: መነጋገር ካለበት አካል ጋር ሊነጋገር መብት ያለው ቅዱስ ሲኖዶስ ብቻ ሲሆን ከሰልፉ በኋላ የሚለንን እንሰማለን:: የእኛ ድርሻ ቤተ ክርስቲያን ያለችንን ብቻ ማድረግ ነው::
#yekatit5
#one_patriarch
#አንድ_ሲኖዶስ
#eotc_one_holy_synod
#OrientalOrthodox
2.5K views21:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ