Get Mystery Box with random crypto!

Christian ዜማ Tube

የቴሌግራም ቻናል አርማ christian_zema_tube — Christian ዜማ Tube C
የቴሌግራም ቻናል አርማ christian_zema_tube — Christian ዜማ Tube
የሰርጥ አድራሻ: @christian_zema_tube
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.05K
የሰርጥ መግለጫ

ወንጌል ያሸንፋል ወንጌል ይለውጣል ወንጌል ለሁሉም!

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-17 19:51:22
የሰው ልጅ እስከነ ነብሱ በጠራራ ፀሀይ ተዘቅዝቆ ሲገደል ባየንበት ምድር፣ንፁሀን በዘራቸው ምክንያት ከመኖሪያ ቄያቸው ተፈናቅለው በሚሰደዱበት ሀገር ለምን ኢየሱስ ያድናል የሚል የመዝሙር ቪዲዮ ውስጥ ገባው ተብሎ ያዙኝ ልቀቁኝ አይባልም!
#እህታችን ዘሪቱ ገና ከአንቺ ብዙ እንጠብቃለን በርቺ!
Yoni-magna
716 views16:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 19:49:08
ኢየሱስ ክርስቶስ ያድናል!!
673 views16:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-09 00:17:49 እባካችሁ ይነብብ
ተነሡ

የእግዚአብሔር አገልጋዮች ትጥቃቸውን ሲጥሉ ምድር በክፋት ትያዛለች። እየሆነ ያለውም ይሄው ነው። አማኞች የምድር ጨው ተብለው ነበር፥ ዓላማቸውን ሲዘነጉ ግን አልጫነቱ ባሰ።

የምድራችን መፍትሄው ወንጌል እንደሆነ ሳይታለም የተፈታ ሀቅ ነው። ግን ማን ወንጌልን ይስበክ!? ነፃ የሚያወጣውን ወንጌል ማን ለትውልዱ ያድርስ!? አሁን አሁንማ ሰው ከተማ ብቻ የሚኖር ይመስል አገልጋዮች ከከተማ አልወጣ ብለዋል። የሚጮኸውም እዛው ነው። ይህም ሆኖ የተለወጠ ሰው ይኖር ይሆን!? እንጃ!

ወንጌል በሞራል፣ በሞቅታ ሳይሆን በሕይወት ቢሰበክ ኖሮ ስንት ህዝብ ወደ እግዚአብሔር መንግስት በተጨመረ ነበር።
ግን ምን ዋጋ አለው ወደ ውስጥ የማይገባ ነጥሮ የሚመለስ ባዶ ጩኸት ብቻ ሆነ።

አገልጋዮች ሆይ፦ "ማንን እልካለው?" የሚለው የእግዚአብሔር ድምጽ አሁንም እየጮኸ ነው። ከምቾታችሁ ውጡና የእግዚአብሔርን ቃል አንሱ። ከምን አገባኝ ስሜት ውጡና በሕዝብ ላይ የተጫነውን የክፋት አሰራር በኢየሱስ ስም ገስፁ። የጨለማው አሰራር ከምድራችን እንዲወገድ ጉልበታችን መሬት ይንካ። የትውልድን ደም ሊያፈስ፣ ነፍስ ሊቀጥፍ የወጣ የክፋት ሰይፍ ወደ ሰገባው እንዲመለስ ወደ እግዚአብሔር እንጩህ።

ሃይማኖተኝነት መቼም ቢሆን መፍትሔ ሆኖ አያውቅም። መፍትሄው መንፈሳዊ አማኝ መሆን ነው። ክርስቶስ በምድር ላይ ሲመላለስ የገሰጸው እምነት ማጣትን፣ ያደነቀውም እምነትን ነው። ስለዚህ ይህን ዘመን ለመሻገር በእምነት ወደ እግዚአብሔር እጅን ማንሳት ያስፈልጋል።

አማኝ ሲፀልይ እንጂ ሲያሸብር አያምርበትም። እቃ ጦሩ ፀሎት፣ መጽሐፍ ቅዱስ እንጂ ድንጋይ አይደለም። አማኝ የእግዚአብሔር ሥራ የበዛለት እንጂ ጊዜውን በአሉባልታ የሚያባክን ስራ ፈት አይደለም።

ወገኖቼ መከሩ ብዙ ነው ገና አልተነካም ፥ ሰራተኞቹ ግን ጥቂቶች ናቸው። ያላመነው ሳይሆን አምኖ የነበረውም ወደ ኋላ እየተመለሰ ነውና እንነሳ።

ተነሡ የቃሉን ብርሃን አብሩ፣ ብርሃን ባለበት ጨለማ አይሰለጥንምና!

እግዚአብሔር ምድራችንን ይፈውስ!

መፍትሄው ወንጌል ነው!
1.4K views21:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-23 22:46:03 ለወንጌል አማኞች በሙሉ
የእግዚአብሔር ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ!
ያለንበት ሁኔታ እጅግ ፈታኝ፣ አንገብጋቢና የሁላችንንም ትኩረት የሚሻ ነው፡፡ ከገባንበት የእርስ በእርስ ጥላቻና ግጭት፤ የሰዎች ሞትና መፈናቀል፤ የውጭና የውስጥ ተጽዕኖ፣ በአጠቃላይ የመጪው ጊዜ ስጋት ፈታኝ ተግዳሮት መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡ ይህንን ተግዳሮት ለማስወገድ በእግዚአብሔር ስም የተጠሩት ክርስቲያኖች ሰውነታቸውን አዋርደው በመፀለይና ፊቱን በመፈለግ ከክፉ መንገዳቸውም በመመለስ ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ናሽናል ክርስቲያን ሪፔንተንስ ኤንድ ሪኮንስሌሽን ሚኒስትሪ በአገር አቀፍ ደረጃ ነሐሴ 8 ቀን 2014 ዓ.ም የፆምና የፀሎትን ጊዜን በማድረግ ሁላችንም ክርስቲያኖች በየአጥቢያ ቤተክርስቲያናችን ተሰባስበን በአንድ ልብ በእግዚአብሔር ፊት በእውነተኛ ንስሀ እንድንቀርብና ምህረትን እንድንለምን መንፈስ ቅዱስ አሳስቦናል፡፡ ስለዚህ በዕለቱ ክርስቲያኖች በየአጥቢያ ቤተክርስቲያኑ በመሰባሰብ የአምላካችንን ፊት እንድንፈልግ ስንል የአክብሮት ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

ከመንፈሳዊ ሠላምታ ጋር


ቄስ ዶ/ር ቶሎሳ ጉዲና
ማሳሰቢያ፡-
እባክዎን ይህንን መልእክት ለሚያውቋቸው የወንጌል አማኞች ሁሉ ያስተላልፉ፡፡
666 views19:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 08:25:41
1.1K views05:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 08:25:37 ሁሉን ብእርሱ እንችላለን!!

" ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ።"
( ፊልጵ 4፥13)

ስሙኝ አንድ ዝሆን ነበረ አሉ እናም አንድ ቀን በሚኖርበት ይህንድ ቤንጋል ከተማ ትልቅ የሰርከስ ትእይንት ላይ ይሳተፋል። በጣም የሚገርመው ያንን የሚያህል ዝሆን ለሰርከስ ትእይንት የሚመራው ደግሞ ብእድሜ እስራዎች ውስጥ ያል ልጅ ነበር እናም ያ አንድ ፍሬ ልጅ ያን የሚያክል ዝሆን ብትንሽ ልምጭ ነገር አየሸነቆጠ የተለያየ ትእይንት እንዲያሳይ ካደረግው በኋላ አካባቢው በትልቅ ጭብጨባ ተናጋ: እናም በዛ ቦታ ከተሳተፉት ተመልካቾች መካከል: አንደኛው ከትእይንቱ ባሻገር ይህን የሚያህል ዝሆን በዚህ ትንሽ ልጅ ልምጭ መገላበጡ ያስግርመውና ትእይንቱ ከለቀ በኋላ ከድንኴኑ በስተጀርባ ልጁን አግኝቶ በምን ቀመር እንዲህ እንደሆነ ይጠይቀዋል : እናም ልጁ ከሰውይው የተሰውረ የሚመስለውን ነገር ይነግረው ጀመር እንዲህ ሲል: ይገርምሃል ለሰርከስ የሚሆኑትን ዝሆኖች የምናሰለጥናቸው ከህጻንነታቸው ጀምረን ነው ይህንንም የምናደርገው እንዲመቸን እነርሱን ለመግራት ነው : ታዲያ ከዚያ የህጻንነት እድሜ ጀምሮ እስከ ጉርምስናቸው ማብቂያ አካባቢ :በሁለት ዛፍና ዛፍ መካከል በጠንካራ ገመድ ታስረው እንዲቀለቡ እናደርጋለን እናም ይታዘዙትን እንዲያደርጉ በዱላ እንመታቸዋለን እናም እንቢታቸው ከበዛ ይዱላውን ኃይል እንጨምራለን እናም ድብድባው ዚበዛባቸውና የታሰሩበት ገመድ ሲጠነክርባቸው ሳይወዱ በግዳቸው የተባሉትን ማድረግ ይጀምራሉ
የዚያን ጊዜ እንፈታቸውና ከእነሱ በፊት ወደተገሩት ዝሆኖች እንቀላቅላቸውና የተላያየ ልምምድን በጋር ማድረግ ይጀምራሉ : ከዚያ በኀላ እንኳን ምንም ያህል ሰውነታቸው እየገዘፈ እንኳ ቢሄድም የኋለኛው ዘመናቸው ልምምድ ተጽእኖ ስላለባቸው የክር ያክል ቀጭን ገምድ እንኳን ብታስራቸው የመበጠሰ እቅማቸው በስልጠናው ስለተነፈጉ እቅም ያጥራቸዋል በመሆኑም ለመበጠስ እንኳ አይሞክሩም: ስለዚ ልምጯ በተንኮሰቻቸው ቁጥር የሚባሉትን ከማድረግ ውጭ ሌላ እቅም በውስጣቸው እንዳለ እንኳን አይረዱም በማለት ለሰውይው ገለጻ አደረገለ ።

ይህን ታሪክ ሳነብ ምን እንደ ነካኝ ታውቃላችሁ
በውስጣችን ትልቅ የእግዚአብሔር አቅም እያለ አስረው የያዙን " አትችልም" አትችይም " የሚል ድምጽ ፈጥኖ ሲከበን፣ በልጅነታችን ፣ከወላጆቻችን ፣ ከጎረቤት፣ ከመምህሮችችን፣ ከአካባቢያችን የሰማናቸው አሉታዊ ንግግሮች ሕሊናችንን ያጨናንቃሉ። እናም የእኛም አእምሮ ይህንን ተቀብሎ ያስተጋባል እምሮ በደረሰበት ውጫዊ ተጽእኖ ውስጣዊ መረጃን በመቆናጠጥ ገመዱን ያስራል ይህም ገመድ ትምህርትን ያነሳል ፣ ፍጥረትን ይዳስሳል ፣ ትውልድን ያወሳል እንዲህ እና እንዲያ ስለ ማንነታች ክንቱነት ገመድን ያጠብቃል : እነዚህ ድምጾች ድምጽ ብቻ ቢሆኑ ባልከፉ፤ ነገር ግን ከታሪካችን፣ ከገጠመኞቻችን ፣ በዙሪያችን ካሉ ጠንቅቀን ከምናውቃቸው እውንታ መሰል ክስተቶች ጋር ተዛምዶ ስላላቸው ያለማመንታት እንቀበላቸውና ጫና ያደርጉብናል : በእርግጥም የቀድሞ ያልተሳኩ ሙከራዎቻችን ፣ የኑሮ መደባችንን፣ የገንዘብ አቅማችንን ፣የትምህርት ደረጃችንን፣ የቆዳ ቀለማችንን.... የምንመለከት ከሆነ እንደ ቤንጋሊው ዝሆን በውስጣችን ታላቅ ኃይል ይዘን በታናሽ እጅ የምንመራ ፣ ሳንወድ የሌላውን ፈቃድ የምናድርግ የጠላት መጫወቻ ልንሆን እንችላለን። ነገር ግን በቀድሞ የሽንፈት ታሪካችንና በአሁኑ ውጪያዊ ገጽታችን በውስጣችን ያለውን ከሁሉ የሚበልጥ ኃይል እርሱም ክርስቶስን ከተመለከትን " እትችልም" " አትችይም" የሚለንን የሐሰት ድምጽ " ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ!" በሚል የድል ድምጽ ሽረን የተገለጠልንን የእግዚአብሔርን ፈቃድ በራሳችን ዘመን ፈጽመን ማለፍ እንችላለን።

" እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል።"
(የዮሐንስ ወንጌል 15:5)
1.0K views05:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 00:42:57
መለኮታዊ ጥሪ ባለው አገልጋይ ላይ መረጃ(ፍሬ)አልባ የሆኑ አሉባልታዋችና ወሬዋች ሊሰራጩበት ይችላል።አገልጋይ እዲህ አይነቱ መረጃና ፍሬ አልባ ወሬ ላይ ተመሥርቶ አይደናገጥም።ነህምያ ላይ የተነሱት ሰንበላጥና ጦቢያ ዓረባዊም ጌሳም ሥራውን ለማስቆም ብዙ ሙከራዋችን አድርገው አልሳካ ሲላቸው ወሬን ያስወሩበት ጀመር።ነህምያ ግን በወሬው ከመናወጥ ይልቅ "አንተ ከልብህ ፈጥረኸዋል እንጂ እንደተናገርከው ምንም የለም"ብሎ መለሰለት።(ነህ6:8 )ዓላማውን የሚያውቅ አገልጋይ ለፈጠራ ወሬ ጆሮውን ሰጥቶ እራሱን አያስቸግርም።በዚህች አጭር የአገልግሎት ጉዞዎቼ ውስጥ በፈጠራ ወሬዎችና ችግሮች ብዙ መከራ ተቀብያለሁ።ይሁን እንጂ ስራዬን ሳላቆም ቀጥያለሁ።ጌታም በዚህ ውስጥ ብዙ ረድቶኛል።የዘንድሮም መልካም ወጣት በጌታ ፀጋ ብዙ ምርኮ ያለበት እንደሚሆን አምናለሁ።ለእኔ ብርታት ለዶኢ ጤንነት ለሌዊ ጥበቃ እንዲሆንልን በፀሎታችሁ አስቡን።
949 views21:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 18:44:14
891 views15:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-05 04:28:28
#በዉጫዊ ሀሳብ ምርኮኛ ከመሆን ራስን የማዳን ጥበብ
ጥበብ#6
➠የሚጨነቅ እና የሚፈራ አይምሮ መቼም ቢሆን መልካም የሆነዉን መፍትሄ መፍጠር አይችልም ምክንያቱም የፍርሀት እና የጭንቀት ምርኮኛ ስለሆነ ሰይጣን የመረጠለትን ብቻ ነዉ እያሰበ ያለዉ ስለዚህ ሰዉን መታገስ አይችልም ቁጠኛ እና እረፍት አልባ ይሆናል የሚፈራ እና የሚጨነቅ ሰዉ

# 1ኛ በኑሮ ላይ ታላቅ ድካምን ይፈጥራል።
# 2 ተኛዉ የሚፈጥረዉ ነገር ፍሬ አልባነት ነዉ በየትኛዉም ቦታ ላይ ፍሬ ማፍራት አይችልም በዚህ አለም ኑሮ ዉድነት በሀብት እና በኑሮ ምቾት በመጨነቅ ሙሉ ፍሬ ሊያፈራ አይችልም
በተሰጠዉ በማንኛዉም ቦታ ላይ ፍሬያማ መሆን አይችልም ይጀምራል ፍሬዉ አይሳካለትም።
— ማርቆስ 4፥19 (አዲሱ መ.ት)
“ነገር ግን የዚህ ዓለም ውጣ ውረድ፣ የሀብት አጓጊነት እንዲሁም የሌሎች ነገሮች ምኞት ቃሉን አንቀው በመያዝ ፍሬ እንዳ ያፈራ ያደርጉታል።”

➂ኛ የሚጨነቅ እና የሚፈራ ሰዉ በአንድ ነገር ብቻ ነዉ የሚቆየዉ ሌላ ሀሳብ አይቀይሩም ለብዙ አመት የሚያወሩት አንድ ችግርን ብቻ ነዉ ሌላ ነገር ማሰብ እስከማንችል ድረስ ምርኮኛ ያደርገናል ማለት ነዉ።

እስራኤላዉያንን ጠላት ሸዉዷቸዉ ስለ እሱ ክፍት እና ሀይል ብቻ እንዲያስብ አድርጎ ለአርባ አመት ገዛቸዉ እግዚሀብሄርን አስበዉ ወደ አዲስ ነገር ዉስጥ እንዳይገቡ ጭንቅላታቸዉን ምርኮኛ አደረጋቸዉ አርባ አመት ያሰብት ስለ ጠላት ሀይል እና ጉልበት ብቻ ነዉ።

#ብዙ ክርስትያንኖች ቸርች ይመላለሳል እንጂ ሀሳባቸው ያለዉ አለም በፈጠረዉ ችግር ላይ ነው::
2.2K views01:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-24 07:34:36
2.0K views04:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ