​የአብይ ፆም ስያሜዎች አብይ ፆም ስምንት ስሞች አሉት 1. የአብይ ፆም ፦ በጌታችን በመድሃኒታች | የ ኦርቶዶክስ ቅዱሳን አባቶች ትምህታዊ ንግግሮች Wise sayings of holy fathers of orthodox

​የአብይ ፆም ስያሜዎች
አብይ ፆም ስምንት ስሞች አሉት

1. የአብይ ፆም ፦ በጌታችን በመድሃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የተመሰረተ ስለሆነ አብይ ይባላል።

2. ፆመ ሁዳዴ ፦ በጥንት ጊዜ ገባሮች ለባለ እርስቱ የሚያርሱት መሬት “ሁዳድ” ይባል ነበር እኛም ጌታችንን ባለቤቱን ኢየሱስ ክርስቶስ እያሰብን የምንፆመው ስለሆነ ሁዳዴ ተብሏል።

3. የካሳ ፆም ፦ አዳምና ሄዋን ከገነት የተባረሩት ለውርደት ሞት ለሲኦል ባርነት የበቁት በመብል ምክንያት ነው። በመብል ምክንያት የሞተውን የስው ልጅ ጌታችን በፈቃዱ በፈፀመው የሰው መንፈሳዊ ረሃቡን በረሃቡ ካሰለት።

4. የድል ፆም ፦ አርስተ ሃጣውዕ (ማቴ 4÷1) ድል የተነሱበት ስለሆነ የድል ፆም ተብሏል።

5. የመሸጋገሪያ ፆም ፦ ጌታችን ከህገ-ኦሪት ወደ ህገ ወንጌል ለመሸጋገር የፆመው ፆም ስለሆነ የመሸጋገሪያ ፆም ተብሏል።

6. ይቀድሶተ ገዳም ፆመ ፦ ጌታችን ከከተማ ርቆ ተለይቶ በመፆም በብህትውና መኖርን ቀድሶ የሰጠበት የመጥምቁ ዮሐንስን ፣ የነብዩ ኤሊያስን ገዳማዊነት የባረከበት በመሆኑ ይቀድሶተ ገዳም ፆመ ይባላል።

7. የመዘጋጃ ፆም ፦ ህዝበ እስራኤል የፋሲካን በግ ከመመገባቸው በፊት ዝግጅት ያደርጉ ነበር። ትንሳኤን ከማክበራችን ስጋውና ደሙን ከመቀበላችን በፊት በፆምና በፀሎት ዝግጅት የምናደርግበት በመሆኑ የመዘጋጃ ፆም ተብሏል ።

8. ፆመ አስተምህሮ ፦ ጌታችን የፆመው ለትምህርት ነው እንጂ መፆም ያለበት ሆኖ አይደለም ስለዚህ ይህ ፆም ፆመ አስተምህሮ ይባላል።

ማቴ 26÷29 ማቴ 16÷16 ዮሐ 15÷26

@wiseholyfathers
አስተያየት ካላቹ በ @Wisecomment_bot ይላኩልን
የ ኦርቶዶክስ ቅዱሳን አባቶች ትምህታዊ ንግግሮች Wise sayings of holy fathers of orthodox

የ ኦርቶዶክስ ቅዱሳን አባቶች ትምህታዊ ንግግሮች Wise sayings of holy fathers of orthodox

@orthodoxholyfathers
465 ተመዝጋቢዎች
ሃይማኖት ምድብ
This channel's aim is to help us learn from the spritual life of holy fathers . ከቅዱሳን አባቶች ትምህታዊ ንግግሮች እንማር ዘንድ የ ተዘጋጀ channel ነው።. ...