Get Mystery Box with random crypto!

ባለ ማስተሯ እማሆይ! በማስተርስ የተመረቁት እማሆይ ፍሬሕይወት ዘምሁር ገዳመ ኢየሱስ በወል | ኦርቶዶክሳዊት ሴት

ባለ ማስተሯ እማሆይ!

በማስተርስ የተመረቁት እማሆይ ፍሬሕይወት ዘምሁር ገዳመ ኢየሱስ

በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በBussiness and Economics በማስተርስ ደረጃ በዛሬው ዕለት ተመርቀዋል። የእናትነት ምንኩስና ሳይበግራቸው ለዚህ መድረስ ምንኛ መታደል ነው ! በምርቃታቸውም ስነ ስርዓት ላይ አባ ዘኢየሱስ (የምሁር ገዳመ ኢየሱስ አበ ምኔት) በአገልግሎት የሚመስሏቸው የገዳሙ እናቶች መነኮሳይያት በቦታው በመገኘት "የእንኳን ደስ አለዎት" መልካም ምኞታቸውን ገልጸውላቸዋል።

እማሆይ ፍሬ በወልቂጤ ከተማ በሚገኘው "በመልከ ጼዴቅ" አካዳሚ ት/ት ቤት እያገለገሉ ይገኛሉ።

እግዚአብሔር አምላክ ዕድሜ ፀጋ ያድለዎት እናታችን
(ከተስፋ ሰይፉ ገጽ የተገኘ)