Get Mystery Box with random crypto!

(ዲያቆን ሔኖክ ኃይሌ) የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ በጸሎት ተጀምሮአል:: የሁላችንም ጭንቀትና | ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ

(ዲያቆን ሔኖክ ኃይሌ)

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ በጸሎት ተጀምሮአል:: የሁላችንም ጭንቀትና ሃሳብ የቤተ ክርስቲያን ቀጣይ ህልውና ጉዳይ ነው:: በዚህ ዓመት የገጠመንን ጊዜያዊ ችግር ወደ ዘላቂ ችግርነት የሚያሳድግ ውሳኔ እንዳይወሰን የሁላችንም ሥጋት ነው:: በጾመ ነነዌ ከዕንባ እስከ ደም የፈሰሰለትን የቤተ ክርስቲያን ክብር በዘለቄታው የሚያፈርስ መንገድ እንዳይኬድ ቅዱስ ሲኖዶስ በነበረው ጽናት እንደሚታገልና የሚበጀንን እንደሚወስን በጸሎት እንጠብቃለን:: ሹመትን አጥብቆ መፈለግ ለሹመት ብቁ ያለመሆን አንዱ ምልክት መሆኑን የምታስተምር ቤተ ክርስቲያን እንደ ጌታዋ "ታላቅ ሊሆን የሚወድ ቢኖር ታናሽ ይሁን" ብላ ሁሉን መስመር እንደምታስይዝም እንጠብቃለን:: ጊዜው በሀገሪቱ ብዙ እሳት የሚነድድበት ምሕላ የሚያስፈልግበት ፣ ብዙዎች በአስተዳደራዊ ስኅተቶችና ከቤተ ክርስቲያን አስተዳደር የሚጠብቁትን ባለማግኘታቸው ልባቸው ቆስሎ ቤተ ክርስቲያንን ተቀይመው ሃይማኖት የለሽ የሆኑበት ነው:: በመሆኑም ጊዜው ብዙ ነገር የሚስተካከልበት እንጂ የሹመትና ሽልማት ጊዜ አለመሆኑ ከአስተዋይ አባቶቻችን እንደማይሰወር ተስፋ እናደርጋለን:: ከቤተ ክርስቲያን የማይለየው እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ከአባቶቻችን ጋር ይሁንልን::


Facebook Link   follow ያድርጉ
https://www.facebook.com/deaconezemarefitsume.keb