~ኃጢአተኛዋ ሴትና ፈሪሳዊው ስምዖን~ ዘማዊቷ ሴት እግሮቹን ስማ ከእግሮቹ በኅቡዕ ጸጋን ተቀበለ | ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ
~ኃጢአተኛዋ ሴትና ፈሪሳዊው ስምዖን~
ዘማዊቷ ሴት እግሮቹን ስማ ከእግሮቹ በኅቡዕ ጸጋን ተቀበለች። በጉዞ ከደከሙት እግሮቹ የኃጢአት ሥርየት አገኘች።በነጻ ከሕመሟ የምትድንበትን መድኃኒት ይሰጣት ዘንድ ይህቺ ሴት የአዳኟን በጉዞ የደከሙ እግሮች በነጻ መልካም መዓዛ ባለው ዘይት በመቀባት ዘና አደረገቻቸው።....ርሃቡን ለማስታገስ አልነበረም ጌታችን እንግዳ ሆኖ ከስምዖን ቤት መገኘቱ። ነገር ግን ኃጢአተኞችን ይቅር የሚለው እርሱ ንስሐ ስለምትገባው ስለዚህች ኃጢአተኛ ሴት ሲል ግብዣው ቤት ተገኘ። የፈሪሳዊውን የቅንጦት ማዕድ አልነበረም ጌታችን ራቡ፤የዚያች የኃጢአተኛ ሴት እንባ እንጂ።እርሱ ከተራበው ከእንባዋ ከረካና ከተጽናና በኋላ ነፍሳትን ሊረዳ ወደዚህ ምድር እንደመጣ፣ ሓላፊ የሆነውን ምግብ ሽቶ በእንግድነት ወደ እርሱ እንዳልመጣ ያስገነዝበው ዘንድ ጌታችን ለግብዣ የጠራውን ስምዖንን ወደ መገሰጽ ተመለሰ።
~ኅብረ ወንጌል ዲያቴሳሮን ትርጓሜ በቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ገፅ 132 ከህዳግ ማስታወሻ ~።
~ትርጉም በመ/ር ሽመልስ መርጊያ።~