+ በወለደች ትሞታለች + የእፍኝት (አርዌ ገሞራዊት )ልጆች በእናታቸው ማሕፀን ሲፀነሱ በእናታቸ | ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ

+ በወለደች ትሞታለች +

የእፍኝት (አርዌ ገሞራዊት )ልጆች በእናታቸው ማሕፀን ሲፀነሱ በእናታቸው ምክንያት አባታቸው ተገድሎ ሲሆን እነርሱ ደግሞ ሲወለዱ የእናታቸውን ሆዷን ቀድደው በመብላት ነው ከእናታቸው ማሕጸን የሚወለዱት ። ለዚህም ምክንያታቸው የእናታቸው አፈ ማሕጸኗ ጠባብ በመሆኑ የሚፈጠር ክስተት መሆኑን ሊቃውንት ያስረዳሉ (ምዕላደ ጥበብ ቅጽ ፩) ። በመሆኑም እፍኝትን ልጆቿ የሚበሏት ከውስጥ ከሆዷ ጀምረው ወደ ውጪ ነው ። እንዲህ አድርገው በልተው ሆዷ ሲቀደድላቸው ይወለዳሉ ። የሸረሪት ደግሞ ሲጀመር የሚፀነሱት እንደ ዕንቁላል ባለ ነገር ውስጥ ነው። እንዳንድ ጊዜ በመጨረሻ አካሏ ይዛው ትንቀሳቀሳለች ፣ አንዳንድ ጊዜም አስቀምጣው ስትንቀሳቀስ ትታያለች ።

በመጨረሻም በሚወለዱበት ጊዜ ገስግሰው ሒደው እናታቸውን ይወሩና ይበሏታል ሸረሪት በተፈጥሮ አጥንት የሌላት በመሆኑዋ ምንም ቅሬታ አካል ሳይኖራት ተበልታ ታልቃለች ። ስለዚህ የሸረሪት ልጆች እናታቸውን ሲበሉ ከውጭ ጀምረው ወደ ውስጥ ነው ። እስኪ አሁን ተመልሰን ኢትዮጵያን እናስባትና እንደ እፍኝት ከውስጥ ወደ ውጭ እንደ ሸረሪት ደግሞ ከውጭ ወደ ውስጥ በሁለቱም የአበላል መንገድ አይደለምን ? እየተበላች ያለችው እንዲህም ስተበላ ይህ ዘመን የመጀመሪያዋ አለመሆኑ ከአለፈ ታሪክም መረዳት ይቻላል ። ( ምዕላደ ጥበብ ቁጥር ፪ በመምህር መምህራን በጽሐ ዓለሙ ገጽ 121-122 )


#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ
ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ

ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ

@orthodoxamero
165.52K ተመዝጋቢዎች
ሃይማኖት ምድብ
ዲያቆን ፍፁም ከበደ ሀሳብ ካሎዎት @Fisumkeb YouTube 👇👇👇 https://youtu.be/FvQ26dWWEj4?si=TDOpAAm1yXzAdjWR facebook Link... https://www.facebook.com/deacon...