Get Mystery Box with random crypto!

የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ጥቅሶች ✝

የቴሌግራም ቻናል አርማ ort_tiksoch — የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ጥቅሶች ✝
የቴሌግራም ቻናል አርማ ort_tiksoch — የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ጥቅሶች ✝
የሰርጥ አድራሻ: @ort_tiksoch
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 196

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-03-08 10:01:45 በስመአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን

ሰላም ውድ የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እንዴት ናችሁ

ብዙዎቻችሁ መዝሙር ይለቀቅልን ብላችሁ ጠይቃችሁ ነበር ፍላጎታችሁን ለመሙላት ሲባል በነገው ዕለት በ YOUTUBE ቻናላችን ላይ የተለያዩ የንሰሐ መዝሙሮችን የያዘውን VIDEO እንለቅላቹአለን እስከዛ ድረስ አብሮነታቹ አይለየን።

በ TELEGRAM
https://t.me/+7ATtlQzOyQY2MTk8
በ FACEBOOK
https://www.facebook.com/profile.php?id=100067027770667
በ YOUTUBE
https://youtube.com/@barkot_tube

የተዋሕዶ ልጆች ለወዳጅ ዘመዳቹ SHARE በማድረግ ይተባበሩን
SHARE
SHARE
SHARE
176 views07:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-28 04:51:59 የ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ጥቅሶች pinned a photo
01:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-26 09:32:42 ቅድስት (የዐቢይ ጾም ሁለተኛ ሳምንት)

«ቅድስት» ማለት የዘይቤ ፍችው « የተቀደሰች የተለየች » ማለት ነው። ምስጢራዊ መልእክቱ ግን የምስጢረ አድኅኖት ታላላቅ ሥራውን ለመጀመር መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶሰ በገዳመ ቆሮንቶስ ገብቶ ከቆመ ሳያርፍ፣ ከዘረጋ ሳያጥፍ የጾማት የአርብዓው ቀንና ሌሊት ልዩ የሆነችና ክብርት ጾም የምትጀመርበትን ሁለተኛ ሳምንት ከልብ ያሳስበናል፡፡ ማቴ. 4-2

ቅድስት የዐቢይ ጾም ሁለተኛ ሰንበት ስያሜ ነው፡፡ ስያሜውም ከኢትዮያዊው የዜማ ሊቅ ከቅዱስ ያሬድ የተገኘ ነው። ከዚህ ሰንበት ዋዜማ ጀምሮ ስለ ዕለተ ሰንበት ቅድስና ይዘመራል፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም ሰንበቱን ስለ ቅድስና ልጆቿን ታስተምርበታለች ፡፡

በቅዳሴ ጊዜ የሚሰበከው ምስባክ ፤ የሚነበቡ መልዕክታት ፤የሐዋርያት ሥራ ና ወንጌል ስለ ቅድስት የሚያስተምሩ ናቸው፡፡

‹‹ቅዱስ›› ማለት ልዩ፤ ክቡር ማለት ነው፡፡እግዚአብሔር አምላካችን በባሕርዩ ቅዱስ ነው፡፡ ይህም ቅድስና ከማንም ያላገኘው የባሕርይ ገንዘቡ ነው። መጻሕፍትም የባሕርይ ቅድስናውን ተባብረው መስክረዋል፡፡ ባባሕርዩ ቅዱስ ስለሆነ ‹‹ቅዱስ፡ቅዱስ፡ቅዱስ›› እየተባለ ይመሰገናል፡፡ ( ኢሳ 6፡1-3፤40፡25 ራዕ 15፡4 ፤ 1ሳሙ2፡2-3፡፡) እኛም ቅዱስ ልጁ በሥጋ ተገልጦ እንዳስተማረን በየዕለት ጸሎታችን ‹‹ስምህ ይቀደስ›› እንለዋለን፡፡

የቅድስና ምንጭ ፡ ቅድስናን የሚሰጥ እርሱ ብቻ ነው፡፡ ‹‹ ቅዱስ ›› የሚለው ቃል ለሰዎች ፡ለመላእክት ፡ ለቦታ ፡ለዕቃ: ለዕለታት … ቢቀጸልም ቅድስናቸው በባሕርይው ቅዱስ ከሆነው ከእግዚአብሔር የተገኘ ነው፡፡ ይህም የጸጋ ቅድስና ይባላል፡፡

እግዚአብሔር ቅዱስ ስለሆነ በመልኩና በምሳሌው አክብሮ የፈጠረንን እኛም ቅዱሳን እንድንሆን ይፈለጋል፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ‹‹ዳሩ ግን እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁን›› ተብሎ ስለተጻፈ የጠራቸው ቅዱስ እንደሆነ እናንተ ደግሞ በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ ›› ያለንም
ይህንን ሲያስተምረን ነው። ከመፈጠራችን አስቀድሞ መጠን በሌለው ፍቅር የወደደን እግዚአብሔር ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣን ፤ ለውርደት ሳይሆን ለክብር፤ ለርኩሰት ሳይሆን ለቅድስና፤ ለሞት ሳይሆን ለሕይወት ነው፡፡ የመፈጠራችንም ዓላማ በፊቱ በፍጹም ምግባርና ሃይማኖት በመመላለስ ከእርሱ ጋር እንድንኖር ነው፡፡ ብርሃን ከጨለማ፡ ጽድቅ ከኃጢአት፡ ጋር ኅብረት የለውምና ከእርሱ ጋር ለዘላለም ነግሰን ለመኖር በቅድስና መኖር ይጠበቅብናል፡፡

ቅድስናችን በኑሮአችን ሁሉ እንዲሆን ታዘናል (1ጴጥ1፡15)፡፡ ስለዚህ በተሰማራንበት የሥራ መስክ ፣ በማኅበራዊ ኑራአችን ፣በምንበላው ምግብ ፣በምንለብሰው ልብስ ፣ በንግግራችንና በመሳሰለው ሁሉ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኘውን በማድረግ እግዚአብሔርን በሚሞት ሥጋችን እናክብረው፡፡ ‹‹እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ የኃጢአትንም ጭንቀት ከእኛ አስወግደን በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግስት እንሩጥ፡፡

የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን እንከተለው፤ እርሱ ነውርን ንቆ ፣ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጧል ›› ተብሎ እንደተጻፈ ደምን እስከ ማፍሰስ ድረስ ተጋድሎ አድርገን ከኃጢአት ርቀት በቅድስና እንድንኖር ይገባናል (ዕብ 12፡1)።

ሥጋዊ ምኞታችንንና መሻታችንን ሰቅለን አሮጌው ሰዋችንን አስወግደን ንስሐ ገብተን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ተቀብለን በቅድስና እንድናኖር ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

በ TELEGRAM
https://t.me/+7ATtlQzOyQY2MTk8
በ FACEBOOK
https://www.facebook.com/profile.php?id=100067027770667
በ YOUTUBE
https://youtube.com/@barkot_tube

የተዋሕዶ ልጆች ለወዳጅ ዘመዳቹ SHARE በማድረግ ይተባበሩን
SHARE
SHARE
SHARE
31 views06:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-25 23:14:15 በስመአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን

ሰላም ውድ የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እንዴት ናችሁ

እንግዲህ እንደሚታወቀው ይህ አዲሱ የ TELEGRAM ቻናላችን ነው።
በቅርብ ቀን የምንጀምራቸው አገልግሎቶች

አዳዲስ መዝሙሮች

የንስሐ መዝሙሮች

የበገና መዝሙሮች እና ወዘተ...

ከ 11 ሺህ በላይ ተከታዮች ያለው የ FACEBOOK ፔጃችንን እንዲሁም የ YOUTUBE ቻናላችን እንድትቀላቀሉ የ አክብሮት ጥሪዬ ነው።
በ TELEGRAM
https://t.me/+7ATtlQzOyQY2MTk8
በ FACEBOOK
https://www.facebook.com/profile.php?id=100067027770667
በ YOUTUBE
https://youtube.com/@barkot_tube

የተዋሕዶ ልጆች ለወዳጅ ዘመዳቹ SHARE በማድረግ ይተባበሩን
77 views20:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-25 23:14:15
እንኳን አደረሳችሁ

አብሳሪው መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ቸር ነገር ያሰማችሁ

ከ 11 ሺህ በላይ ተከታዮች ያለው የ FACEBOOK ፔጃችንን እንዲሁም የ YOUTUBE ቻናላችን እንድትቀላቀሉ የ አክብሮት ጥሪዬ ነው።
በ TELEGRAM
https://t.me/+7ATtlQzOyQY2MTk8
በ FACEBOOK
https://www.facebook.com/profile.php?id=100067027770667
በ YOUTUBE
https://youtube.com/@barkot_tube

የተዋሕዶ ልጆች ለወዳጅ ዘመዳቹ SHARE በማድረግ ይተባበሩን
SHARE
SHARE
SHARE
78 views20:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-03 01:43:28 The owner of this channel has been inactive for the last 5 months. If they remain inactive for the next 7 days, they may lose their account and admin rights in this channel. The channel will remain accessible for all users.
22:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-08 13:39:36
201 views10:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-07 10:02:00 #ይህንን_ያውቁ_ኖሯል

የ24ቱ ካህናተ ሰማይ ስማቸው የሚከተለው ነው

፩. አካኤል
፪. ፋኑኤል
፫. ጋኑኤል
፬. ታድኤል
፭. አፍድኤል
፮. ዘራኤል
፯. ኤልኤል
፰. ተዳኤል
፱. ዮአኬል
፲. ገርድኤል
፲፩. ልፍድኤል
፲፪. መርዋኤል
፲፫. ኑራኤል
፲፬. ክስልቱኤል
፲፭. ኡራኤል
፲፮. ባቱኤል
፲፯. ሩአኤል
፲፰. ሰላትኤል
፲፱. ጣውርኤል
፳. እምኑኤል
፳፩. ፔላልኤል
፳፪. ታልዲኤል
፳፫. ፐሰልዱኤል
፳፬. አሌቲኤል

(ከአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ - ተአምኆ ቅዱሳን ንባቡና ትርጓሜው ገጽ 149)
70 views07:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-06 08:40:42
53 views05:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-30 23:28:17
277 views20:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ