Get Mystery Box with random crypto!

አንድ አምላክ ብቻ አለ፡፡ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት አንድ አምላክ ብቻ ነው እንጂ ሰዎች እንደ | የተመረጠ ትውልድ (The choosen generation)

አንድ አምላክ ብቻ አለ፡፡
እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት አንድ አምላክ ብቻ ነው እንጂ ሰዎች እንደሚመስላቸው
ሦስት አምላክ የለም፡፡ እንፍጠር፤ እንውረድ፤ ... ወዘተ ስላለ ከአንድ አምላክ በላይ ነው
ብለው ወስኗል። ቃሉ ግን በማያሻማ ሁኔታ ከአንድ አምላክ ሌላ እንደሌላ ያስተምረናል።
ዘዳ.4:35 እግዚአብሔርም አምላክ እንደ ሆነ ታውቅ ዘንድ ይህ ለአንተ ተገለጠ ከእርሱም
ሌላ አምላክ የለም። ዘዳ.4:39 እንግዲህ እግዚአብሔር በላይ በሰማይ በታችም በምድር
አምላክ እንደ ሆነ ሌላም አንደሌለ ዛሬ እወቅ፥ በልብህም ያዝ። ኢሳ.43:10-12 ታውቁና
ታምኑብኝ ዘንድ እኔም እንደሆንሁ ታስተውሉ ዘንድ እናንተ የመረጥሁትም ባሪያዬ ምስክሮቼ
ናችሁ ይላል እግዚአብሔር ከእኔ በፊት አምላክ አልተሠራም ከእኔም በኀላ አይሆንም። እኔ
እኔ እግዚአብሔር ነኝ፥ ከእኔ ሌላም የሚያድን የለም። ተናግሬአለሁ አድኜማለሁ
አሳይቼማለሁ፤ በእናንተ ዘንድ ባዕድ አምላክ አልነበረም ስለዚህ እናንተ ምስክሮቼ ናችሁ፥
ይላል እግዚአብሔር፥ እኔም አምላክ ነኝ። ኢሳ.44:6-7 የእስራኤል ንጉሥ እግዚአብሔር
የሚቤዥም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ ፊተኛ ነኝ እኔም ኀለኛ ነኝ
ከእኔ ሌላም አምላክ የለም። እንደ እኔ ያለ ማን ነው? ይነሣና ይጥራ ይናገርም ከጥንት
የፈጠርሁትን ሕዝብ ያዘጋጅልኝ፥ የሚመጣውም ነገር ሳይደርስ ይንገሩኝ። አትፍሩ
አትደንግጡም ከጥንቱ ጀምሬ አልነገርኀችሁምን? ወይስ አላሳየኀችሁምን? እናንተ
ምስክሮቼ ናችሁ። ከእኔ ሌላ አምላክ አለን? አምባ የለም ማንንም አላውቅም። ... እንደ
እግዚአብሔር ቃል ከአንድ አምላክ በቀር ሌላ አምላክ እንደሌላ እንደማይኖርም በዘመናችን
ሁሉ እንመሰክረለን፡፡ .... ይቀጥላል
@onegodonlyjesuss