የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ የክረምት የሕዋ ሥልጠና መርሃግብር በጅማ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ መሠጠት ተጀመረ። በመረሃግብሩ ከኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ ዋናው መሥሪያቤት የመጡ አሰልጣኞች፣ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ ጅማ ቅርንጫፍ አመራሮች ፤ የጅማ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ተወካዮች ፣ እንዲሁም ሌሎች የዩኒቨርሲቲው ማሕበረሰብ አባላት ተገኝተዋል። ሠልጣኞቹ በጅማ ከተማ የተውጣጡ ተማሪዎች ሲሆኑ ከነኅሴ 23 እስከ 27 በሚቆየው በዚህ የክረምት የሕዋ ስልጠና መሠረታዊ የሆኑ የሥነ-ፈለክ፣ የሳተላይት ቴክኖሎጂ እንዲሁም የኤሮስፔስ ምህንድስና ዘርፎች ተግባራዊ የሆኑ ሥልጠናዎችን ይወስዳሉ። የኢት.ስ.ሳ.ሶ የክረምት ሥልጠና በዚህ ክረምት ከሚያካሂዳቸው 5 የሥልጠና መረሃግብሮች ይህ የመጨረሻው እና የመዝጊያ ሥልጠና ነው። #ESSS #SST #Jimma 690 viewsLealem, 16:42