Get Mystery Box with random crypto!

#ምንድነበር_ኮዱ? ~~ ከሩቅ ተቀምጦ ባይኖቹ እያደባ ፣ ስንቱ ነው የለፋ ከልቤ ሊገባ ፣ | Fortune

#ምንድነበር_ኮዱ?
~~
ከሩቅ ተቀምጦ ባይኖቹ እያደባ ፣
ስንቱ ነው የለፋ ከልቤ ሊገባ ፣
አልከፈት ሲለው ሊገነጥል በሩን ፣
ስንት ቆራጥ ሰው ነው ከኔ የጣለ ክብሩን
.
ኧረ ቤት ይቁጠረው ስንቱ እንደተንጋጋ፣
ማስተዋል ተስኖት ልቤ እንደተዘጋ
.
እናልህ
የሞከሩት ሁሉ ባንዴ እየተረሱ፣
እንኳንስ ሊከፍቱት ደጁም አልደረሱ፣
እኔም ተብሰለሰልኩ እነሱም ተጎዱ፣
በሞቴ ንገረኝ የልቤ መክፈቻ ምንድንነበር ኮዱ?

JOIN @Durat_a
@Durat_a