Get Mystery Box with random crypto!

Besmeti 😍😍😍

የቴሌግራም ቻናል አርማ officalemutiii — Besmeti 😍😍😍 B
የቴሌግራም ቻናል አርማ officalemutiii — Besmeti 😍😍😍
የሰርጥ አድራሻ: @officalemutiii
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 736
የሰርጥ መግለጫ

in dis channel u can get
arif arif music 🎶🎶
arif arif keledoch😂
Join as my sweet channel
Jøïñ äs 👉 @officalemutiii
gruop lelalachu 👉 @emutiii844
Inbox me @mehzeba
and @Rehimetii

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 19:40:52 እየተፍለቀለቀች ነገረቻቸውና ወደ አባቷ ጋር አምርታ እንደመጡ ነገረችው.....
መኩሪያው ወዲያው ከልጁ ጋር እጅ ለእጅ ተያይዞ መጣ.....
እነ ሚኪ ከመቀመጫቸው ብድግ ሲሉ "ጀግኖቼ መጣችሁ...አይገባም ተቀመጡ" አላቸው......
ሰራተኛዋ ማክዳ በልዩ ሁኔታ አጣፍጣ የሰራቻቸውን ምግቦች የመመገቢያ ጠረጴዛው ላይ በመደርደር "መልካም ምግብ" ብላቸው ወደ ኪችን ተመለሰች።
"ልጆች በሉ እራት ከበላን በሁላ እንጨዋወታለን....መልካም ምግብ" አላቸው መኩሪያው ሹኪያ በእጁ እየያዘ...
ሚኪ የቀረበለትን ምግብ እንደነገሩ ጠንቆል ጠንቆል እያደረገ ስለ ሰላም እናት በእራት ዝግጅቱ ላይ አለመገኘት ያስባል...
"ለምን ይሆን ያልተገኘችው..? በህወት የለችም ወይስ ተፋታለች....? ሰላሜ ስለ እናቷ ምንም አላለችኝም...
ሚኪ የጥያቄዎቹን መልስ ከማን ማግኘት እንደሚችል ጠንቅቆ ያውቃል።
"ይሄንንማ ሰላም ልታስረዳኝ ይገባል" አለና አይኑን በሹኪያ ከሚያንገላታው የተጠበሰ ስጋ ላይ ነቅሎ ሰላምን አየት አደረጋት......


Share ለወዳጅዎ

@officalemutiii

:¨·.·¨: ❀
·. ┈┈••◉❖◉●••┈ይ ላ ሉ
91 viewsŘéçá Łoveĺý ğãl, 16:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 19:40:51 በቀልና ፍንጥርጣሪው

ክፍል


.
.
.
ሚኪን እድል እጇን ዘርግታለታለች...ምክንያቱም አሁን ላይ መኩሪያው ወዶቷል..የልጁንና የራሱን ህይወት ስላተረፈለት ሚኪ ከምንም በላይ ባለውለታው ነው...አዎ ሚኪ ብዙ ህይወት የቀጠፈችውና ለብዙ ሰው ህይወት መመሰቃቀል ምክንያት የሆነችው የመኩሪያው ነፍስ ወደ ሲኦል እንዳታመራ ታድጓታል..
ይሄ የጭካኔ መጨረሻ...የግፎች ሁሉ ግፍ የተፈጸመበት ቤተሰብ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መኩሪያውን ከሞት መንጋጋ መንጭቀው አውጥተውታል....ትላንት የሚኪ አባት ዛሬ ደግሞ ሚኪ ለመኩሪያው ትልቅ ውለታ ውለውለታል...እዚህች ምድር ላይ በህይወት የመቆየቱ ምክንያቶች እነሱ ናቸው። እሱ ቁባ ባይኖረውም....
ያ ሁሉ መተረማመስና ግርግር ካለፈ እነሆ ሶስት ቀን ሆኖታል...ሚኪ ቤቱን ከነአካቴው እራስቶታል ማለት ይቻላል....ሰላም ከታገተች ጀምሮ ሮቤል ጋር እንደከተመ ነው....ሂዊ ልጇ ማራማዊት ጋር የተወሰነ ጊዜ ስለምታሳልፍ ሄደት መጣ ትላለች።...
ለእውነትና ለፍትህ የሚታገሉት ሶስቱ ፈርጦች ዛሬም ተሰብስበዋል.......
ሚኪ በጥይት የተጫረው ክንዱ በፍጥነት እየዳነለት ቢሆንም ያሳለፋቸውን እነዚያን አስቀያሚ ቀናቶች ከአእምሮው ሊፍቃቸው አልቻለም..."የሰላም የድረሱልኝ ድምጽ ፤ የሰላም እገታና በመጨረሻም ሽጉጥ ተደግኖባት የደረሰላት ትእይንት ሁሌ በቅዠት መልክ እየመጣበት ይባንናል....የጦርነት ወይም የሆረር ፊልም እንዳየ ህጻን ልጅ በላብ ተጠምቆ ሲወራጭና ሲንፈራገጥ ያድራል።....
ሂዊም የሚኪን ያህል ባይሆንም ፍርሃትና መሸበሩ በውስጧ እንዳለ ነው....ያን የጥይት ፉጨትና የተኩስ ልውውጥ ሰምታ ባትፈራ አያስደንቅም። ሂዊ በመኲሪያው ሰዎችና በመካሻ ሠዎች መካከል የተደረገውን ግብግብ ትንሽም ቢሆን ለማየት ችላለች...በራሪ ጥይቶች ሳይቀሩ የመኪናዋን መስታወቶች ሰብረውባታል...ተኩሱ እያየለ ሲሄድ ነው እንግዲህ ሚኪና ሮቤል እንዳስጠነቀቋት በቅልጥፍና መኪናዋን በማስነሳት ያመለጠችው..ምናልባትም ቶሎ ባትዎስን ኖሬ ለሰላምና ለመኩሪያው የተዘጋጀው የሞት ድግስ ለሂዊ ይሆን ነበር።
ከሁሉም በተለየ ሁኔታ የእለት ተእለት ኑሮውን ምንም እንዳልተፈጠረ ሲከውን የነበረው ሮቤል ብቻ ነበር....ሚኪና ሂዊ እራሱ በሮቤል አለመረበሽ ተደምመዋል....ሮቤል የጥይት ተኩሱም ሆነ ሌላው ትእይንት እንደ ቦሊውድ ፊልም የሆነለት ነው የሚመስለው....የኖረበት ሁኔታም ሊሆን ይችላል ቀለል አድርጎ እንዲመለከተው የረዳው ወይም ተፈጥሮው...
"ይሄ ኮማንደር ማነው...?" ሚኪ ሲያብሰለስለው የነበረውን ጥያቄ ሰነዘረ..
ሮቤልና ሂዊ አልመለሱለትም..ዝም ብለው ያዩታል..
"ለምን ስለኮማንደር አሰብክ...?" ሂዊ ሚኪን መልሳ ጠየቀችው
"የመኩሪያው ቀኝ እጅ ስለሆነ ነዋ....ሮቤል ዘንግተኸው ካልሆነ መኩሪያው ስልክ ደውሎ ትእዛዝ ሲሰጥ ኮማንደር እያለ ነበር...ካሁን አሁን ስሙን ይጠራል ብዬ ብጠብቅም ጉጉቴ ከንቱ ሆነ...መኩሪያው ወሬው ላይ ስሙን ሊጠቅስ አልቻለም.."
"አሃ ገባኝ...ኮማንደሩ ከፓሊስ አባል ነው ግን የመኩሪያውን ቆሻሻ ስራ የሚሰራውም የሚያጸዳውም እሡ ነው ማለት ነው። አለ ሮቤል
"ya እኔም ያሰብኩት እሡን ነው...እእ ሂዊ ከመኩሪያው ጋር በነበሩሽ የግንኙነት ጊዜያት ውስጥ ኮማንደር ስለሚባለው ሰው የሰማሽው ወይስ ያየሽው ነገር የለም..? እሥቲ አስቢ.." አላት ሚኪ ከአይኗ ውስጥ የኮማንደሩን ስም ያገኝ ይመስል ትግ ብሎ እያያት...
"አይ የለም...እርግጠኛ ነኝ አላውቅም...ሠውዬውኮ ሁሉ ነገሩ ሚስጥር ነው ከሱ ሰዎች ጋር በጭራሽ አያነካካኝም.....
"እንግዲያውስ በእገታው ምክንያት ተቋርጦ የነበረው ስራችንን እንጀምራለን.." አለ ሚኪ
"እንደ እኔ ግን እቅዳችን መቀየር አለበት ባይ ነኝ.." አለ ሮቤል የሁለቱንም ትኩረት ለማግኘት እየሞከረ...
"እንዴት......?" አሉት
"ሂዊ የተሰጣትን ድርሻ ትቀጥል ችግሩ እዛ ላይ አይደለም ችግሩ እኔ እዛ ድርጅት ላይ መቀጠሬ ነው....አደጋ ይኖረዋል ምክንያቱም መኩሪያው ከ3 ቀን በፊት እገታው ላይ በደንብ አይቶኛል ዛሬ ተንስቼ ልቀጠር ብል ያስጠረጥረኛል.."
"እና ምን ብናደርግ ይሻላል....?" አለው ሚኪ
"መኩሪያውን እጅ ማሰጠትና መዘረር እንችላለን...ግን ስኬታችን ሚኪ ባንተ ፍላጎት ይወሰናል"
"ንገረኝ ልስማው እሥኪ" አለ ሚኪ በጉጉት
"ምን መሰለህ ሚኪ የሰላም እገታ መጥፎ ጎኑ ቢያመዝንም ለእቅዳችን መሳካትና መፋጠን ግን ጥሩ እድል ፈጥሮልናል። አሁን ላይ መኩሪያውን ይበልጥ ልትቀርበው ይገባል....ለሱ ካንተ የበለጠ ባለውለታውና ቤተሰቡ የለም...ለልጁ እንደምትሆናት አምኗል ስለዚህ ቀርበኸው ሁሉን ነገር ማጥናት እንችላለን...አውቃለሁ ሚኪ ቀንደኛ ጠላትህን ወዳጅህ አድርገህ ማስመሰል ያማል ያውም እንደመኩሪያው አይነቱን ግን ይሄ ትልቅ እድልህ ነው መኩሪያውን ለማስቆም... 'ከወዳጅህ ይልቅ ጠላትህን ይበልጥ አቅርበው'ይባላልና ያልኩህን አስብበት" አለው ሮቤል
"አይ ምንም ማሰብ አያስፈልግም አደርገዋለሁ...መኩሪያውን እድሜ ልኩን እሥር ቤት ለማስወረወር የማልከፍለው መሰዋእትነት የለም" አለ በእልህና ስሜት ጣቱን ቀስሮ
የሚኪ ስልክ ጭርር አለ...ሚኪ በረድ ለማለት እየሞከረ ስልኩን አነሳው
"ሄሎ ሰላሜ"
"ሄሎ ህይወቴ...እንዴት ነህልኝ"
"አለሁልሽ ልደውልልሽ እያሰብኩ ነበር ቀደምሽኝ.. አንቺስ እንዴት ነሽ እየተረጋጋሽልኝ ነዋ.."
"አዎ አሁን ፍጹም ሠላም ሆኛለሁ...እእ ማታ ከተመቸህ እራት ተጋብዘሃል.."
"አግኝቼ ነው ናፍቀሽኛልኮ የት ነው ቦታ ያስያዝሽው..?"
"እረ ሚኪዬ አረጋጋው እኔ አይደለሁም የጋበዝኩህ ዳድ ነው እንድነግርህ አጥብቆ ነው የጠየቀኝ..ስለዚህ ማታ ቤት ከጓደኛህ ሮቤል ጋር እንድትገኝ"
"እሺ እመጣለሁ የኔ ውድ"
"ዋ! እንዳታረፍድ ዳድ ትንሽ ከጠበቀ ይቆጣል...ደግሞ ዘንጠህ ናልኝ .."
"እሺ እስካይሽ ቸኩያለሁ.."
"እኔም የኔ ህይወት..ቻው በቃ ሠራተኛዋን ላግዛት"
ሚኪ ስልኩን ዘግቶት ፈገግ አለ....ሂዊና ሮቤል እሥኪነግራቸው አፋቸውን ከፍተው ይጠብቁታል....
"ኑ ጓደኞቼ እቀፉኝ...ሊሳካልን ነው መኩሪያው ራት ጋብዞኛል" አላቸው እጁን እየዘረጋ...
ሁለቱም ተጠግተው ተቃቀፉ....እነዚህ የእውነት ልጆች ስራ ቢያገናኛቸውም ግንኙነታቸው ከስራ በላይ ሆኗል...በአንዱ ደስታ መደሰት በአንዱ መከፋት ማዘን..የአንዱን ችግር ለመፍታት ህይወታቸውን እሥከመክፍል ድረስ ደርሰዋል.....እንዲህ በንጹህ ልባቸው ሲተቃቀፉ ደግሞ እስከዘላለሙ አይለያቸው ያስብላል።...
****---***-
መኩሪያው የቀጠሮው ሰአት እሥኪደርስ መኖሪያ ቤቱ ያለው ቢሮው ውስጥ ተቀምጦ የስራ ዝርዝሮችን እያየ ነው...ሰአቱን ተመለከተና እራሱን በመስተዋት እያየ ከረባቱን አስተካከለ ይሄም ለሚመጣው እንግዳ ያለውን ትልቅ አክብሮት ያሳያል.....ፊቱን በእጁ እየዳበሰ "አይ መካሻ..." አለ
የመኩሪያው ፊት በከፊልም ቢሆን መካሻ ባንጠባጠበበት የላስቲክ ቅላጭ ምክንያት ጠባሳ አውጥቷል....
ሚኪና ሮቤል በተባሉበት ሰአት በሱፍ ቂቅ ብለው ወደ ግቢው ገቡ....የመኩሪያው ቪላ ከጥግ እሥከ ጥግ በጠባቂዎች ተሞልቷል.....
"ይሄን ያህል ጠባቂ ካደረገ መኩሪያው ፈርቷል ማለት ነው" አለው ሮቤል ድምጹን ቀነስ አድርጎ እየሳቀ...
"አዎ ባክህ የጦር ካምፕ የገባሁኮ ነው የመሰለኝ" አለው ሚኪም በተራው እየሳቀ.....
ድምቅ ያለ ቀይ ቀሚስ የለበሰችው ሰላምም ከበር ተቀብላቸው እንዲቀመጡ..
77 viewsŘéçá Łoveĺý ğãl, 16:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 19:40:51 በቀልና ፍንጥርጣሪው

ክፍል


.
.
.
ሚኪና ሮቤልም ከቆሙት ሁለት መኪናዎች ውስጥ አንዱን በማስነሳት መካሻን ተከተሉት....
መካሻና ሰዎቹ የሚከተላቸው መኪና እንዳለ አላስተዋሉም ለ20 ደቂቃ ከነዱ በሁዋላ ወደ ሌላው መኖሪያ ቤታቸው ገቡ.......መካሻ የሚመርጣቸው መኖሪያ ቤቶች ከሰው የተገነጠሉና ጭር ያለ ቦታ ለብቻቸው የተሰሩ ናቸው በዚህም ምክንያት ያሻውን ቢያደርግ ከልካይ የለውም.....
"ወንበሩ ላይ እሠሩት" አለ መካሻው በንዴት
ሁለቱ ሰዎችም እየገፈታተሩ ወስደው ጠፍንገው አሰሩት...
"አሁን ቶሎ ግደለኝ ብለህ ትለምኛለህ....." መካሻው የቀለጠ ፕላሥቲክና ሀይላንድ በአናቱና በፊቱ ላይ ያንጠባጥብበት ጀመር...
መኩሪያው እየተንቀጠቀጠ ያጓራል
የሚያሳዝን ድምጽ ያሰማል...
"እረስቼው አንተ ሴሰኛ የልጆቼን እናት በዚህ እቃህ አይደል ያማገጥክብኝ...ቤተሰቤን በአመንዝራነትህ አይደል የበተንከው....አምኜ የወንድምነትን ቦታ ሰጥቼህ ነበር ወደ ቤቴ ወሰድኩህ ጓዳዬን አሳየሁህ አንተ ግን ምን አደረክ አልጋዬ ላይ ወጣህ....የበደልህን ጽዋ ትቀምሳታለህ አሁን አኮላሽልሃለሁ...መኖር እንድጠላ አደርግሃለሁ...ልጆች ኑ ሱሪውን ዝቅ አድርጉልኝ" አለ መካሻ
ሠላም በፈርጣማ እጆቹ የያዛትን ጠባቂ በንክሻ ዘልዝላው ተንደርድራ አባቷ ላይ ተወሸቀች መካሻ አባቷን እንዳይጎዳባት በመከለል በአቅሟ ለመከላከል ሞከረች.."አባዬን ልቀቁት እባካችሁ በእግዛብሄር ተለመኑኝ...እባክህ" አለችው መካሻን
"ዘወር በይ አባትሽ ማን እንደሆነ ብታውቂው ኖሮ እንዳደርገው ትፈቅጂልኛለሽ...አታናጂኝ ተንሽ ከላዪ ላይ" አላት መካሻ እጇን በመጎተት ለማላቀቅ እየሞከረ...
"እባክህ ምንም ቢሆን አባቴ ነው በድሎህ ከሆነም ምህረት አድርግለት.."
"ይሄ ምህረት የሚገባው ሠው አይደለም ዘወር በይ" መካሻ ሰላም ላይ ሽጉጥ ደገነባት
"የአባቴን ስቃይ ቆሜ ከማይ ቀድመህ ግደለኝ..በላ ተኩስ" አለችው
"ሰላሜ ተይ እንደዚህ አታድርጊ ተንሺ...እሡ ችግሩ እኔ ላይ ነው...እባክሽ ልጄ...መካሻ ተው እንዳታደርገው " እያለ መኩሪያው ቢጮኽም ሰላም ልትነቃነቅ አልቻለችም....
ሰላም "እግዛብሄር ሆይ ነፍሴን ተቀበላት በቤትህም አኑረኝ" ብላ አነበነበችና አይኗን ጨፍና ሞቷን ትጠባበቅ ጀመር......አዎ በሰከንዶች ልዩነት ጥይት ተተኮሰ ሰላምም መሬት ላይ ዘንፈል አለች....ነገር ግን አቶ መካሻም በእኩል ቅጽበት ከመሬት ወድቋል...
መኩሪያው ልጄ እያለ ይጮሃል...ያለቅሳል..
የአቶ መካሻ መዘረር ግራ ያጋባቸው ሁለቱ ጠባቂዎች ተጠግተው አዩት ከደረቱ ደም እየፈሰሰው ነው....ተደናግጠው ወደ በሩ ፊታቸውን ሲያዞሩ በድጋሜ ሌላኛው ሰው ተተኩሶበት ወደቀ.........የቀረው ጠባቂ የተኮሳት ጥይት ግን የሚኪ ግራ ክንድ ላይ አረፈች...ሮቤል የቀረውን ጠባቂም በሚገርም ፍጥነት ገደለው.......
ሮቤል የሚኪን በጥይት መመታት ስላየ " ሚኪ እንዴት ነህ...ተጎድተሃል...?" አለው እየደገፈው...
"አይ ደህና ነኝ ጥይቱ ጫር አድርጎኝ ነው ያለፈው..." አለውና ሠላም ወደ ወደቀችበት እየሮጠ ሄደ።
በቂጡ ተዘርፍጦ በቀኝ እጁ ከጭንቅላቷ ከፍ አደረጋትና ጭኑ ላይ አሥቀመጣት....
"ሚኪ ተረጋጋ ድንጋጤው እራሷን አሥቷት እንጂ አልተተኮሰባትም" አለው...
ሮቤል መኩሪያው የታሰረበትን ገመድ ሙሉ በሙሉ አሥወገደለት ....
መኩሪያው ወደ መሬት ተጎንብሶ "ልጄ እኔ ዝም ልበልልሽ..."እያለ እንድትነቃ እጇንና ትካሻዋን ወዘወዘው....ነቀነቃት..
ሮቤል የቤቱን ግቢ ሲቃኝ ትንሽ ፈቀቅ ብሎ የውሃ ታንከር እይታው ውስጥ ገባ....በጆግ ውሃ ይዞ ተመለሰና...."ተረጋጉ ሰዎች...ትንሽ አየር ስጧት..ከላይዋ ላይ ገለል በሉላት" አላቸው....
ትንሽ ለቀቅ ሲያደርጉለት አሁን ትነቃለች" አለና በጆግ ይዞ የመጣውን ውሃ ፊቷ ላይ እረጨባት በአናቷም አፈሰሰባት.....
ሠላም ተንፈራግጣ ተነሳች...መላ ሰውነቷ ይንቀጠቀጥ ነበር...
አባቷን ከጎኗ በህይወት ስታየው እውነት አልመሰላትም.... ፊቱን በእጇ ዳበስ አደረገችው አዎ የእውነት አጠገቧ ያለው የሙት መንፈስ ሳይሆን በህይወት ያለው አባቷ መሆኑን አረጋገጠች.....በሌላኛው አቅጣጫ ደግሞ ሚኪን አየችው ቅዠት ውስጥ ያለች መሰላት....
" ሰላሜ ደህና ነሽ.....?" አላት ሚኪ
"እንዴ ምንድነው ነገሩ ሚኪ እዚህ ምን ያደርጋል....?"ጠየቀችው አባቷን ግራ ተጋብታ
"ልጄ እነሱ ናቸው ህይወታችንን ያተረፏት...እነሱ ናቸው እቺን አየር እንድንተነፍስ እድል የሰጡን" አላት ፈገግ ብሎ
ሰላም ተጠግታ ሚኪን ተጠመጠመችበት...."ሚኪዬ ለሁለተኛ ጊዜ አተረፍከኝ...ሁለቴ ደረስክልኝ...አንተ እንደማተወኝ አውቅ ነበር.....በዚያ በጭንቅ ጊዜዬ እንኳን አንተን ማሰብ አላቆምኩም ነበር...አፈቅርሃለሁ የኔ ጌታ" አለችው እየተንሰቀሰቀች...
"መቼም አልተውሽም...ከአንቺ ውጭ ምን ህይወት አለኝና..አፈቅርሻለሁ የኔ ልእልት..ሞት እንኳን ከአንቺ ሊለየኝ አይችልም " ሚኪ እያለቀሰ እጆቿን፤ጉንጮቿን፤ ግንባሯንና አንገቷን እያፈራረቀ ይሥማት ጀመር እሷም እንደዛው.....
ቆፍጣናው መኵሪያ በመካከላቸው ያለውን ጥልቅ ፍቅር አይቶ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደ ሰውኛ ልቡ እራርቶና አዝኖ አለቀሰ...ባለማወቅ ሚኪ ላይ ጨክኖ ሳያመዛዝን ባደረሰበትም ጉዳት እፍረት ተሰማው....
ሰላምና ሚኪ ተላቅሰው እንደጨረሱ ሰላም ብድግ አለችና ሮቤልን አመሰገነችው......
ሰላም ሞትና ህይወት፤ ጭንቀትና ደስታ በአንዴ ተደራርበውባት እሥካሁን የሚኪ ክንድ መቁሰሉንና እየደማ መሆኑን አላየችውም....
መኩሪያው ከለበሰው ሸሚዝ ላይ እራፊ ጨርቅ ቀደደና "ና ልጄ ሀኪም ጋር እሥክንሄድ ልሰርልህ" አለው..
ሚኪም እሺ ብሎ እጁን ዘረጋለት....
ሁሉም ሰላም እንደሆነ መኩሪያው ለኮማንደር መኮነን በሮቤል ስልክ ደወለለት..
"ሄሎ...አቤት" አለ ኮማንደሩ
"ሄሎ ኮማንደር እኔ ነኝ መኩሪያው.."
"አለቃ የት ናችሁ....ተርፈሃል"
"አዎ ሁሉም ሰላም ነው...አንተስ ጋር አልቋል....?"
"አዎ ጨርሰናል የተወሰኑትን በቁጥጥር ሥር አውያለሁ....ግን እንዴት ሆኖ ልታመልጡ ቻላችሁ..?"
"አምልጠን አይደለም መካሻ ሞቷል"
"እንዴት ሊሆን ቻለ....?"
"እሱን ተወው...ይልቅ ሰዎቹን ይዘህ ትመጣና ቦታውን ታጸዳዋለህ....አድራሻውን በሚሴጅ እልክልሃለሁ"
"አንተ እንዳልክ ይሁን"
መኩሪያው ስልኩን ዘግቶ"በሉ ልጆች እንሂዳ አላቸው"
ሮቤል መኪናውን እየነዳ ጉዞ ጀመሩ
አዲስ አበባ እንደገቡ ወደ እሱ ቤት እንዲነዳው መኩሪያው ለሮቤል ነገረው
ይሄን የሰማው ሚኪ ሆዱ ሻከረበት እስካሁንም አብሮት ሆኖ ልክ እንደ ዘመድ ሲያስመስል የነበረው ለሰላምና ለጀመሩት እቅድ ሲል ነበር..መኩሪያውን ሲያየው የሚሰማውን ንዴት ሚኪ ብቻ ነው የሚያውቀው..እውነትም ሚኪ የተዋጣለት ተዋንያንና አስመሳይ ሆኗል።
"በቃ እኔን ጫፍ ላይ ታወርደኝና እነሱን ወደ ቤት አድርሳቸው" አለው ሮቤልን
"እንዴ ለምን..? አብረን ነው ወደ ቤት የምንገባው..የግል ዶክተር እጠራልሃለሁ.. ታክመህና አረፍ ብለህ ነው የምትሄደው" አለ መኩሪያው
ሰላምም አባቷን በመደገፍ አዋከበችው..ሚኪ አማራጭ ስለሌለው በዝምታና በቁዘማ ወደ ቦሌ መጓዝ ጀመረ።
በዝምታው መሀል ግን አንድ ነገር
ደጋግሞ እያሰበ ነው.."ይሄ ሙሰኛና የመኩሪያው ጭራ ኮማንደር ማነው..?"

@officalemutiii
@officalemutiii

@officalemutiii
65 viewsŘéçá Łoveĺý ğãl, 16:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 19:40:51 በቀልና ፍንጥርጣሪው

ክፍል


.
.
.
መኩሪያው በአጋቾቹ ሌላ አካል እንዳያስከትል ጥብቅ ትእዛዝ ቢሰጠውም እሡ ግን አልሰማቸውም.....በአጋቾቹ ከተደወለለት ጀምሮ እሥኪነጋ ድረስ ብዙ ስራ ሰርቷል....ሁለት ቡድኖችን አደራጅቷል..በኩማንደር መኮነን የሚመራ ሀይልና በራሱ ሰዎች የተዋቀረ ጥምር ቡድን ሠርቷል።......መኩሪያው ይሄ ድርጊቱ የሠላምን ህይወት አደጋ ላይ ቢከተውም ትእቢትና አልነካም ባይነት ወጥሮ ይዞት ከትእዛዛቸው ውጪ ሆነ....አዎ አሁን ላይ ሠላምን ማትረፍ ብቻ አይደለም ፍላጎቱ ይሄን ያህል እሱን የተሳፈጡትን ሰዎች እሥከመጨረሻው አደባይቶ ልክ ማስገባትና ክብሩን ማስጠበቅ ይፈልጋል።......
መኩሪያው ከጠዋቱ 2 ሰአት አከባቢ መኪናውን አስነስቶ ወደ ተባለበት መጋዘን ጉዞ ጀመረ.....በቤቱ አከባቢ አድፍጠው የነበሩት እነ ሚኪም በቅርብ እርቀት ይከተሉት ጀመር.....
"ይገርማል መኩሪያው በህይወቱ አንድ ጊዜ ጥሩ ስራ ሊሰራ ነው....ህይወቱን ለልጁ አሣልፎ ለመስጠት ብቻውን እየሄደ ነው" አለች ሂዊ
"ምንም ጨካኝ ቢሆንኮ ልጁ ናት...ሁሉም አባት ለልጁ ጥሩ ነው" አለ ሮቤል
ሚኪ ግን በሀሳባቸው አልተሥማማም እንዲያውም የመኩሪያው እንዲህ በነጻነት ብቻውን መሄድ ጥርጣሬ አሳድሮበታል...
"አይ እኔ እንኳን አልተዋጠልኝም...እንደ መኩሪያው አይነት እራስ ወዳድ ሠው ይሄው መጣሁላችሁ ግደሉኝ ብሎ የሚሄድ አይመስለኝም ብቻ ምን እንደሆነ ባላውቅም የሆነ ተንኮል አስቧል.." አለ ሚኪ ሽጉጡን እያገላበጠ
መኩሪያው የተነገረው መታጠፊያ ጋር ሲደርስ መኪናውን አቆመውና ስልክ ደወለ.....
"ሄሎ አለቃ...."
"ኮማንደር ሁሉም ነገር ሠላም ነው....?" መኩሪያው እርግጠኛ ለመሆን ጠየቀው
"አዎ አለቃ በትእዛዝህ መሰረት ያልከንን ቦታ ከጠዋቱ 1 ሰአት ጀምረን ከበነዋል..."
"የያዛችሁት ቦታ ምንም አያስጠረጥርም... ? ሰዋራ ነው....?"
"እሡን ለእኔ ተወው...አከባቢውን ከቃኘሁ በሁዋላ ነው ጥሩ ቦታ ፈልጌ የመሸግኩት ማንም ሊያየን አይችልም.."
"እሺ ሁኔታው እንዴት ነው...?"
"ብዙ የታጠቁ ሰዎች አሏቸው..ሠዎቹ የተደራጁ ናቸው ግን ቢሆንም እንችለዋለን.."
"አምንብሃለሁ ኮማንደር"...መኩሪያው ስልኩን ዘጋና የኮረኮንች መንገድ ጉዞውን ጀመረ....
እነ ሚኪ የመኩሪያው መንገድ ላይ መቆም ግር እያላቸው መከተላቸውን ቀጠሉ..........
ቦታው ላይ ለመድረስ ትንሽ እንደቀራቸው ሚኪ ቅጠል ውስጥ የተደበቁትን የመኩሪያው ሰዎች አያቸው....
"ሮቤል እዚህ ጋር አቁመው መኪናውን" አለው ሚኪ ፈጥኖ
"ምን ተፈጠረ . ...?"
"እዛ ቅጠል ውስጥ የተደበቁትን ሰዎች እያቸው" ብሎ በእጁ ጠቆመው...
"የአጋቾቹ ሰዎች ናቸው...?"
"አይ አይመስለኝም....እርግጠኛ ባልሆንም የመኩሪያው ሠዎች ይመስሉኛል.."
"እሺ አሁን ምን እናድርግ..?"አለች ሂዊ
"መኪናውን ሠዋራ ቦታ ደብቀን በእግራችን እየተሹለከለክን በደረታችን እየተሳብን መጋዝኑ ጋር መድረስ ነዋ...ግን ሂዊ እንዳታስቸግሪ አንቺ መኪና ውስጥ ትጠብቂናለሽ" አላት ሮቤል
"እንዴ ለምን...?" አለች ኩስትርትር እያለች
"ምን መሰለሽ ሂዊ ቆራጥ ሴት እንደሆንሽ አውቃለሁ ነገር ግን እዛ የሚያስፈልገው ሽጉጥ የያዘ ሠው ብቻ ነው.....እዚህ ደግሞ ሁኔታውን እየቃኘ የሚያሳውቀን ሰው ያስፈልገናል ስለዚህ እኛን በዚህ እርጂን" አላት ሮቤል ሽጉጡን በጀርባው እየሻጠ...
እንደማያስከትሏት ያወቀችው ሂዊ ተስፋ ቆርጣ ዝም አለች....
"ሂዊዬ ምንም ቢፈጠር ከመኪናው እንዳትዎርጂ አያድርገውና መጥፎ ነገር ቢከሰት መኪናውን አስነስተሽ ከዚህ ተሰወሪ" አላት ሚኪ
ሚኪና ሮቤል ጥንቃቄ በተሞላበት አካሄድ እየተሽሎከለኩ የየትኛውም አካል እይታ ውስጥ ሳይገቡ ከመጋዝኑ ከጀርባው ክፍል ደረሱ....ነገር ግን ያገኙት መጋዝን አልነበረም....ትልቅና የሚያምር ቤት ነው.....
"የቱ ነው መጋዝኑ" አለ ሚኪ
"እያቸው እነዚህን 4 መኪኖች" አለው ሮቤል ለምን ከጀርባ እንደቆሙ ያስተዋለውን ሊነግረው ፈልጎ...
"እእእእእ ምን..?"
"ሰዎቹ እዚሁ ቤት ውስጥ ናቸው....መጋዝን ብለው የነገሩት መኖሪያ ቤት ላለማለት ነው.....እነዚህ መኪኖች ከጀርባ የተዘጋጁት መኩሪያው ችግር ከፈጠረ በጀርባ ለማምለጥ ነው" በማለት ሚኪ ያላሰበውን ነገረው...
ብዙም ሳይቆይ ከምድር ቤት ድምጽ ሰሙ......ድምጹን ለማጣራት ጆሯቸውን ቀስረው አይናቸውን ቢያቅበዘብዙም ጭላንጭል ድምጹ ከየት እንደሚመጣ መለየት ከበዳቸው በመጨረሻም ሚኪ የቆሙበት ጋር በራፍ ተመለከተ....ራመድ ብሎ ተጠጋና በመዝጊያው ክፍተቶች አሾልኮ ለማየት ሞከረ......አዎ እንደ እድል ሆኖ አጋቹና መኩሪያው ያሉት እነ ሚኪ የቆሙበት ቦታ ላይ ነው....."ሮቤል ና እይማ እዚህ ናቸው... በጀርባ ማምለጫቸው ይሄ መሆን አለበት" አለው...
ሮቤልና ሚኪ በጀርባ ደህንነታቸው ቢጠበቅም ለጊዜው ከፊት በኩል አምርተው ሠላምን ሊያድኗት አይችሉም ምክንያቱ በብዙ ሰዎች እየተጠበቀ ነው።....
"እእእ አንተ ነህ መካሻ ልጄን ይዘህ ልታስፈራራኝ የሞከርከው" አለው መኩሪያው ትቢት በተሞላበት አነጋገር ጮኽ ብሎ
"መኩሪያው የድሮ ጓደኛዬ እንዲህ ነው እንዴ የናፈቀህ ወዳጅህን የምትቀበለው..." አለው መካሻ እያፌዘ
"አሁን ቀልዱን ተውና ልጄ የት ናት....? ይሄው እኔ መጣሁልህ እኔን አይደል የምትፈልገው"...
"አትቸኩል ገና ብዙ ጊዜ እናሳልፋለን እኔና አንተ...አዎ እፈልግሃለሁ ጓደኛዬ ሆንክ ስል ለፈጠምክብኝ ክህደትህ የዘላለም አሽከሬ ላደርግህ እፈልግሃለሁ" አለው ትካሻውን መታ መታ እያደረገ....
መካሻ ሠላምን እንዲያመጧት ለሰዎቹ ነገራቸው....ወዲያውም እንደታሠረች ይዘዋት ከተፍ አሉ...
"ሠላሜ...ልጄ....ይሄ ከይሲ ያደረገሽ ነገር አለ.....?" አላት ፊቷን ቀና እያደረገ...
"አባትና ልጅ እሥቲ ናፍቆታችሁን ተወጡ...ከዚህች ቅጽበት በሁዋላ ስለማትተያዩ በደንብ ተሳሳሙ ካካካ" ብሎ ሳቀባቸው....
"መካሻ ያው እኔን ይዘኸኛል ልጄን ልቀቃት እሷ ምንም አላጠፋችም"
ሚኪ ሰላምን ሲያያት የሚሆነውን አጣ...መረጋጋት ተሳነው....
ሮቤል ዘሎ በፊት በር እንዳይገባ ስለሰጋ ጭምድድ አድርጎ ያዘው....
"ተረጋጋ እንጂ ወዳጄ ገና ድራማውንኮ አልጀመርንም...
መካሻው ሁለት ሞተረኞችን ጠርቶ አከባቢውን እንዲቃኙ ትእዛዝ ሰጣቸው.....ሞተረኞቹ ትእዛዙን ተቀብለው ዙሪያ ገባውን ማሰስ ጀመሩ....በመንገዱ ዳርቻዎች ላይ የደረቁ የዛፍ ቅጠሎች መንኮሻኮሽ ትኩረታቸውን ሳበውና ከሞተራቸው ወርደው ሽጉጣቸውን በማቀባበል ወደ ዛፎቹ አመሩ.....
ሲመጡ ያያቸው የመኩሪያው ሰው ከኮማንደር መኮነን ምንም አይነት ትእዛዝ ሳይጠብቅ ፍርሃት ተጸናውቶት አንደኛውን ሞተረኛ ተኩሶ ገደለው...ሌላኛውም የተኩስ ልውውጥ ሲያካሂድ እዚያው ወደቀ.......
ይሄን የተኩስ ድምጽ የሰማው መካሻ.....ለሰዎቹ የመኩሪያውን ሰዎች አንድ ባንድ እንዲለቅሟቸው ተናገረና ሁለት ሠዎቹን አሥከትሎ መኩሪያውንና ሰላምን በጀርባ በር ይዟቸው ለመውጣት ሲሰናዳ ሚኪና ሮቤል ገለል ብለው ተደበቁ...
መካሻና ሰዎቹ ሰላምና መኩሪያውን በሁለቱ መኪና ጭነው ተፈተለኩ.....
ሚኪና ሮቤልም ከቆሙት ሁለት መኪናዎች ውስጥ አንዱን በማስነሳት መካሻን ተከተሉት.....


@officalemutiii
@officalemutiii
@officalemutiii
96 viewsŘéçá Łoveĺý ğãl, 16:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 17:20:12 በሴት ልጅ መንገድ ላይ እሾህ አታስቀምጥ! እህትህ በዛ መንገድ ላይ ባዶ እግሯን ትመጣ ይሆናልና።
110 viewsإيمان , 14:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 19:57:56 ጥ ለመሆን እንዳትሞክር"አለና የመኩሪያውን መልስ ሳይጠብቅ ስልኩን ዘጋው...
ሚኪ ሙሉ አድራሻውን በጥንቃቄ ወረቀት ላይ አሥፈሮ ከጨረሰ በሁዋላ በጩኸት ቤቱን ቀውጢ አደረገው...ሮቤል ከተኛበት ተሰፈናጥሮ ተነሳ....ሮቤል ላየው ሰው ሰይጣን በህልሙ ያየ ነበር የሚመስለው.....ሂዊም ጩኸቱን ሰምታ ከክፍሏ ወጣች።
"ምንድነው...ሚኪ...?" አለው ሮቤል አይኑን እያሸ
"ሠላሜ አልሞተችም" ሁለቱንም እያፈራረቀ ያቅፋቸውና ይስማቸው ጀመር...
"እንዴት ልታውቅ ቻልክ...?" አለችው ሂዊ
"አጋቾቹ ለመኩሪያው ደወሉለት...ልጅህን ማግኘት ከፈለክ ብቻህን ና ብለው አድራሻ ነገሩት። ይሄው አድራሻው ስለዚህ ነገ ሂደን እናስመልጣታለን"
"ሚኪ ተረጋጋ በችኮላ የምናደርገው ነገር የሠላምን ሂይወት አደጋ ላይ ይጥለዋል...ስለዚህ መጠንቀቅ አለብን" አለው ሮቤል
"አምንሃለሁ ሮቤል እሺ ምን እናድርግ....?"
"የምንሄደው በኔ መኪና ነው...ሹፌሩም እኔው ነኝ....መኩሪያው ነገ ሲወጣ በጥንቃቄ እንከተለዋለን..
ሁኔታውን እያየን እዛው እንወስናለን.....የተኩስ ልውውጥ ሊኖር ስለሚችል ሂዊ እዚሁ ትቆያለሽ"
"አይ አልስማም ሶስታችንም አንድ ቡድን የሆን መስሎኝ!!..ስለዚህ እዚህ አልቀመጠም መሳሪያ ታጥቄ ባላግዛችሁ እንኳን በሌላ ነገር እረዳችሁ ይሆናል"
ሚኪና ሮቤል እንድትቀር ሊያሳምኗት ብዙ ቢሞክሩም ሂዊ በእምቢተኝነቷ ፀናች.......
ሶስቱም የነገው ከባድ ፈተና ላይ እራሳቸውን ለመማገድ ተስማምተው ወደ የክፍላቸው አመሩ ትንሽ አእምሯቸውን ለማሳረፍ..........


ተደራሽ እንዲሆን SHARE

:¨·.·¨: ❀
·. ┈┈••◉❖◉●••┈
ይ ላ ሉ @officalemutiii
@officalemutiii
@officalemutiii
177 viewsŘéçá Łoveĺý ğãl, 16:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 19:57:56 በቀልና ፍንጥርጣሪው

ክፍል


.
.
.
......ወደ እራሷ አዞረችውና ሚኪ ሳያስበው ከንፈሩን በከንፈሯ ገመጠችው።...
ሚኪ ከላዩ ላይ መንጭቆ ገፈተራት "ሂዊ ምን ማድረግሽ ነው....እኔና አንቺኮ በሥጋ ዝምድና ባይኖረንም ወንድምና እህት ነው....እንዴት እንደዚህ ታደርጊያለሽ...?" ጮኸባት...በጥፊ ሁሉ ሊመታት ከጀለ...
ሂዊ በሀፍረት ተሸማቀቀች "ሚኪ እምነትህን ስላጎደልኩ ይቅርታ አድርግልኝ...አእምሮዬ ስለተጨናነቀ ነው ይሄን ያደረኩት እንጂ ምንም አሥቤ አልነበረም...ትሞታለህ ብዬ ስለፈራሁ ስሜቴ ተፈታተኘኝ"...እንባዋ ኩልል እያለ ወረደ
"በይ በቃሽ ሂዊ አታልቅሺ...አሁን በሁለታችን መካከል የተፈጠረውን እንዳልተፈጠረ አርገን እንረሳዋለን" ትካሻዎን ያዝ አድርጎ አባበላት....
"ሰዎች ምንድነው የምትላቀሡት" አለ ሮቤል ከሄደበት ተመልሶ እየተቀላቀላቸው..
"እእእ ምን አዲስ ነገር አለ..? ሰላሜ እንዴት ናት...?" አለው ሚኪ
"ግቢው በፓሊሶች ተሞልቷል...የህክምና ቡድኑ ጥቃት የደረሠባቸውን የጥበቃ ሰራተኞች እያከመ ይገኛል...መርማሪዎቹም ቦታ ከልለው ስራቸውን እየሠሩ ነው...."
"ሮቢ እባክህ መስማት የምፈልገውን ንገረኝ" አለው ሚኪ ሆዱ እየሻከረበት..
"ምን መሰለህ ሚኪ ሰላም በቤቱ ውስጥ የለችም.."
"ምን....?" አለ ሚኪ አይኑ እየተጉረጠረጠ
"ሚኪ ተረጋጋ እንደሚመስለኝ ከሆነ ሰላም አልሞተችም ተጠልፋ ነው.."
"ለምን ይሄን ልታስብ ቻልክ...?"
"ቢገሏት ኖሮ አሥክሬኗ ይገኝ ነበር....ሌላው ደግሞ መኩሪያው ከብዙ ሠዎች ጋር ይነካካል..ብዙ ጠላት አለው ስለዚህ እሷን ይዘው ሊጠቀሙበት ነው..."
"እሺ አሁን ማድረግ የምንችለው ነገር ምንድነው...?" አለው ሚኪ
"አሁን ያለን እድል እንደ ሰዎቹ ብልጠት ይወሠናል...ስልኳን የሆነ ቦታ ካልጣሉት በስልኳ ያለችበትን ማወቅ እንችላለን.....አሁን ወደ ቤት እንሂድና ኮምፒውተሬ ላይ ላፍጥጥ" አለ ሮቤል..
መኪና ውስጥ ገብተው ወደ ሮቤል ቤት ሄዱ....ኮምፒውተርና አሥፈላጊ እቃዎች የሚያስቀምጥበት ክፍል ገብተው ሶስቱም ኮምፒውተሩ አይናቸውን ተከሉ።...
ሮቤል ስልኳ ያለበትን አድራሻ አገኘው ነገር ግን አቅጣጫው የሚጠቁመው መኩሪያው መኖሪያ ቤት ነው...
"ስልኳን አልያዘችውም ማለት ነው....አለ ሮቤል ምንም ማድረግ እንደማይችል እያሳበቀበት..
"ኡፍፍፍ እና በሌላ መንገድ ልናገኛት አንችልም...?" ሂዊ ነበረች የጠየቀችው..
"አዝናለሁ አንችልም...ውጪ አገር ቢሆን በየጎዳናው የመንገድ ላይ ካሜራዎች ስላሉ እሡን ጠልፈን መኪናውን መለየት እንችል ነበር.....እዚህ ግን ምንም አይነት ካሜራ የለም"..
"እና ደርሰንላት ልናድናት አንችልም እያልከኝ ነው ሮቢ" አለው ሚኪ እያለቀሰ
"ምን መሰለህ ሚኪ ታግታ ከሆነ ነገ ወይ ከነገ ወዲያ አጋቾቹ ለድርድር መኩሪያው ጋር ይደውሉለታል....እስከዛ ድረስ መጠበቅ ነው...ባይሆን ሲደውሉለት እንድንሰማ የመኩሪያውን ስልክ መጥለፍ አለብን...ስለዚህ ስልክ ቁጥሩ ያስፈልገኛል"
"እእ እኔ አውቀው ነበር በቃሌ ቆይ ላስታውስ" አለች ሂዊ
"እስቲ ሞክሪ..ሂዊ ለኔ ስትይ አድርጊው...አሥታውሺ" አላት ሚኪ
"ኦው መጣልኝ 0910................መጨረሻው 65 መሰለኝ"
"እሥቲ ለማረጋገጥ በዚህ ሲም ደውይለትና ድምጹን ስሚ" ሮቤል ያልተመዘገበ ሲም ከጠረንጴዛው ኪስ አውጥቶ ሰጣት....
ሂዊም ስልኳ ውስጥ ከተተችና ደወለችለት...ስልኩ በፍጥነት ተነሳ
"ሄሎ ማን ልበል...? አለ መኩሪያው
ሂዊ ይሄን ጭካኔ፤ አረመናዊነትና አውሬነት የተሞላበት ጎርናና ድምጽ ስትሰማ ልቧን እቅለሸለሻት....ቀስ ብላ ሥልኩን ከጆሮዋ ላይ አወረደችውና ዘጋችው
"አዎ እራሱ ነው" አለቻቸው...
ሮቤል ጊዜ ሳይወስድበት የመኩሪያውን ስልክ ጠለፈው....
ሚኪ በጉልበቱ ተንበርክኮ አምርሮ አለቀሰ....
"ተረጋጋ ጠንከር በል እናገኛታለን.." እያሉ ሊያጽናኑት መኮሩ..እሱ ግን ለቅሶውን አላቆመም የጥፋተኝነት ስሜት ተሰምቶታል"እንዴት ልረጋጋ እንዴትስ ልጠንክር.. ? በኔ ቸልተኝነትኮ ነው እንዲህ የሆነችው.....እሷ እኔን አምናብኝ እንድደርስላት ደወለችልኝ ግን ስልኬ ዝግ ነው.. .እያንዳንዷ ደቂቃ ሰላሜን ወደሞት እያቀረባት ነው እዩኝ እሥኪ አሁንም እዚህ ነኝ ምንም ላደርግላት አልቻልኩም...ሠላሜ እዛ እየተሰቃየች እኔ መኖር አይገባኝም" ሚኪ እራሱን ከግድግዳው ጋር ያጋጨው ጀመር....
ሮቤልና ሂዊም በእልህ አስጨራሽ ትግል እራሱን እንዳይጎዳ አሥቆሙት...እየደማ ያለውን ጭንቅላቱን በውሃ ካጠቡት በሁዋላ በፋሻ ጠቀለሉለትና ሶፋው ላይ አስተኙት....
"ሚኪ ምን መሆንህ ነው...ያንተን ያህል ባይሆንም እኛምኮ አዝነናል...እራስህን መጉዳት አማራጭ አይሆንም ሠላም ይሄንን የምትፈልግ ይመስልሃል...? ለሰላም ከመቼው በላይ የምታስፈልጋት አሁን ነው...ሠላምን ሳትጎዳ በሠላም ለመመለስ ከፈለክ እኔ የምልህን ታደርጋለህ" አለው ሮቤል በሚኪ የህጻን ድርጊት እጅግ ተበሳጭቶ...
*-*-********
ሰላም ደብዛዋ ከጠፋ 3 ቀን ሆኗታል እነ ሚኪም ኮምፒውተሩ ላይ አፍጥጠው ይነጋባቸዋል በተለይ ሚኪማ እንቅልፍ በአይኑ ዙሮ አያቅም....ሚኪና እንቅልፍ ከተሰነባበቱ ሁለት ቀን ሆኗቸዋል....ነገር ግን የተለወጠ ነገር የለም። የመኩሪያውን ስልክ ጠልፈው 24 ሰአት ቢከታተሉትም ከተራ ወሬ ያለፈ ከሰላም መጥፋት ጋር የተያያዘ ምንም ፍንጭ ሊያገኙ አልቻሉም.......
ሚኪ አሁንም ሳይታክትና ተስፋ ሳይቆርጥ ወንበር ላይ ተቀምጦ ኮምፒውተሩን አትኩሮ ያየዋል ሰላምን በመናፈቅ......እኩለ ሌሊት ሲሆን ሂዊና ሮቤል እንቅልፍ ወዘወዛቸው....ትንሽ እረፍት እናድርግ ብለው ሂዊ አንዱ መኝታ ክፍል ሮቤል ደግሞ ሶፋው ላይ ተጋደሙ።.....
የሌሊቱ አጋማሽ አልፎ 6:30 ላይ ለመኩሪያው ስልክ ተደወለለት....
"ሄሎ.." አለ መኩሪያው ቅርዝዝ ባለ ድምጽ..
"መኩሪያው ወዳጄ....በሰላም ተኝተሀል" ከወዲያኛው የስልክ ጫፍ የተሠማ የቀልድና የስላቅ የሚመስል ድምጽ ነበር......
መኩሪያው ካልጋው ላይ ወረደና ስልኩን ላውድ አድርጎ ማውራት ጀመረ...
"ማነህ...ማን ልበል አላወቅኩህም"
"አታስብ ልጅህን ልትጎበኝ ስትመጣ በደንብ ታውቀኛለህ"
"ልጄ....ሰላሜ የት ናት...? ምንድነው ያደረጋችሁዋት....?"
"አታስብ በጥሩ እየተንከባከብናት ነው ልክ እንደ ቤቷ.....ካካካካ" ሳቀበት
ሚኪ በደስታ ፊቱ ፍክት ብሎና ትኩረቱን ሰብስቦ የስልክ ምልልሱን መከታተል ይዟል
"ትሰሙኛላችሁ ከልጄ ላይ አንድ የጸጉር ዘላላ እንኳን ቢነሳ ስጋችሁን ቆራርጬ ለአሞራ ነው የምሰጠው.."
"አታስብ እኛ የምንፈልገውን ካደረክ ምንም አትሆንም.. እኛ ከሷ ችግር የለብንም ካልተስማማህ ግን ልጅህ ትሞታለች"
"እሱን አታስበው ልጄ አንድ ነገር ብትሆን አሥፈሪ አውሬ ነው የምሆንባችሁ"
"ዛቻውን ተወውና አሁን ኳሱ እኛ ጋር ነው ስለዚህ ወደ ደብረዘይት መስመር መኪናህን ብትነዳው ይሻልሃል።... አዲስ አበባን ለቀህ የደብረዘይትን መንገድ እንደያዝክ 9 ደቂቃ ትነዳለህ ከዛ ፒስታ መገንጠያ ያጋጥምሃል በመገንጠያው ትገባና ትንሽ እንደተጓዝክ ሌላ ሁለት መንታ መንገዶች ያጋጥሙሃል የቀኙን ትተህ በግራ ትታጠፋለህ..ትንሽ እንደነዳህ የሆነ መጋዘን ታገኛለህ...ቦታው ላይ ስትደርስ መኪናውን አቁመህ ውረድ ቀሪውን ለኛ ሰዎች ተወው....ብቻህን ካለምንም ትጥቅ ነገ 3 ሰአት እንድትመጣ..ፓሊስ ወይም ሌላ አካል ይዤ እመጣለሁ ካልክ እመነኝ ይጸጽታሃል..ብል
131 viewsŘéçá Łoveĺý ğãl, 16:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 19:57:55 ሃል ወይም ፓሊሶች ይይዙሃል"
"ሂዊ ተይኝ...አታስቁሚኝ ወደ መኪናው ተመልሰሽ ግቢ" አላት በጣቱ እየጠቆመ
"እመነኝ ሁሉም ጥሩ ይሆናል...ግን በተረጋጋ መንገድ እናድረገው"..
ሚኪ ሊሰማት አልቻለም መንገዱን ቀጠለ....ሂዊ ስሜቷ እንቢ ሲላት እየሮጠች ሄዳ ክንዱን ያዝ አደረገችው.......ወደ እራሷ አዞረችውና ሚኪ ሳያስበው ከንፈሩን በከንፈሯ ገመጠችው።....

ይቀጥላል ....

share

ይ ላ ሉ @officalemutiii
@officalemutiii
@officalemutiii
113 viewsŘéçá Łoveĺý ğãl, 16:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 19:57:55 በቀልና ፍንጥርጣሪው

ክፍል


.
.
.
መኩሪያው በልጁ ሰላም ድንገተኛ የድረስልኝ ጥሪ ተደናግጦ እየበረረ ቢመጣም ረፍዶበታል....
የግቢው ጥበቃዎች እዚህም እዛም ተዘርረዋል ወደ ውስጥ ዘልቆ ሲገባ ሠራተኛዋ ማክዳም ሳሎን ውስጥ እራሷን ስታለች።......
እየተርበተበተ ወደ ሠላም ክፍል አመራ....አዎ ክፍሉ ባዶ ነው....ወደ አልጋው ተጠጋና ልብሶቿን አንሥቶ ጠረኗን በአፍንጫው ማገው....ስቅስቅ ብሎም አለቀሰ.....
"ልጄ አታስቢ ወደ ቤትሽ በሰላም እመልስሻለሁ"....አለና ለማረጋገጥ ወ/ሮ ምእራፍን ሊጎበኛት ሄደ....
ወ/ሮ ምእራፍ አልጋዋ ላይ እንደተኛች ናት....
"እንከፍ ልጅሽ ታግታልሻለች አንቺ እዚህ ካለምንም ሀሳብ ትተኛለሽ" አላትና ሳሎን ወረደ ወዲያውም በጥቅም ወዳጁ ለሆነው ኮማንደር መኮንን ስልክ ደወለለት.....
ሶስቱ ጓደኛሞች ውይይቱን አጧጥፈውታል....እሥካሁንም ብዙ አቅደዋል......
በመሀል እረፍት ለማድረግ ውይይቱን ወደ ጎን አሥቀምጠው መቀላለድና ስለራሳቸው የተወሠነውን ማውራት ጀመሩ።
"ሚኪ ቅድም ያዋራሃት ፍቅረኛህ ናት....?" ሮቤል ነበር ጠያቂው
"አዎ ናት.....ግን አሁን ምን ማሰብ እንዳለብኝ አላውቅም ነገሮች ተዘበራርቀውብኛል"
"ማለት...? ጥሩ ላይ አይደላችሁም...?"
"ነገሩ የከበደ ነው....የመኩሪያው ልጅ ናት"...
ሮቤል እንደተገረመ ያስታውቅበታል
"ብቻ ሚኪ መኩሪያውን ለመጉዳት ቀርበሃት እንዳይሆን.....ልትጠቀምባት ከሆነ ስምምነታችን እዚህ ጋር ያበቃል" አለ ሮቤል...
ሂዊ ጣልቃ ገብታ ስለሆነው ነገር ለሮቤል የተወሰነ ነገረችው...
ማስረዳቱን እንደጨረሰች ውይይታቸውን ቀጠሉ....ልክ ከምሽቱ 3 ሰአት ላይም አቅደው ጨረሱ.....
በእቅዳቸው መሰረት ሂዊ በመኩሪያው የጥቃት ሰለባ ስለሆኑት ሴቶች እንድታጣራና...ልጃገረዶችን የሚያባልግበት ድብቅና ሰዋራ ቤት ካለው እንድትመረምር ተልእኮ ተሰጥቷታል.....ሮቤል ደግሞ እንደ ነጋ ሲቪውን ለድርጅቱ አስገብቶ እንዲቀጠር ወስነዋል።
ሚኪ ለጊዜው ምንም አያደርግም...
ሚኪና ሂዊ ሮቤልን ተሰናብተውት ወደ ፒያሳ ለመሄድ ወደ መኪናቸው አመሩ....የሚኪ መኪና ቀን ከቆመበት አልተነቃነቀም ግን አራቱም ጎማዎቹ ተፈተዋል.....
ሮቤልና አሥገራሚና ድራማዎቹ
መኪናውን አስረስቷቸው እንጂ አውላላ ሜዳ ላይ እስከ ምሽት ድረስ ካለባለቤት የቆመን መኪና ምን እንደሚደርስበት ጠፍቷቸው አይደለም።......
"ኡፍፍፍ ምን አይነት ነገር ነው..."አለች ሂዊ
"አየሽ ነገሮች ሲደራረቡ...እንደዚህ ደክሞን መኪና እንኳን የለንም"...
"እና አሁን ምን ይሻለናል...? እዚሁ ትተኸው ብትሄድ አዳራቸውን አወላልቀው ለቆራሊዮ ነው የሚሸጡልህ.......በቃ ሮቤል ጋር ተመልሰን ጎማ እንጠይቀውና ያበድረና" የሚል ሀሳብ አቀረበችለት
"ይሁን ግን 4 ጎማ ሙሉ የሚኖረው ይመ ስልሻል....?"
"ሃሃሃሃ እሱ እንኴን ጎማና ኑክሌር ቦምብም እራሱ አይጠፋውም"
ካካካካካ ሚኪ በአገላለጿ ሳቀና ወደ ሮቤል ቤት በድጋሚ አመሩ።
የሂዊ ሀሳብ የተሳካ ነበር ከሮቤል ቤት የፈለጉትን አግኝተው በሮቤል አጋዥነት በአንድ ሰአት ውስጥ ገጥመው ጨረሱና ወደ ሰፈራቸው ሄዱ...
ሚኪ ሂዊን ቤቷ አሥገብቷት ወደቤቱ ተመለሰ።....ጃኬቱን ወርወር አድርጎ በድካም የዛለ ሠውነቱን ለማሳረፍ ሶፋው ላይ አረፍ አለ....
በጀርባው ደገፍ አለናም ለሰላም ሊደውልላት የዘጋውን ስልኩን ከፈተው....
ሠላም ደውላለታለች አንድም ቮይስ መልእክት አሥቀምጣለች....
"አይ የኔ ፍቅር...በስርአት ስላላዋራሁዋት ተናዳብኝ ነው የሚሆነው" አለና ቮይ ስ መልእክቱን ከፈተው...
"ሚኪዬ የኔ አለም በጣም እወድሃለሁ ምናልባት ካሁን በሁዋላ ላታየኝ ትችላለህ..የተከናነቡ ሰዎች ሊገሉኝ በጣም ቀርበዋል.. ይሄን የምልህ መኝታ ክፍሌ ተደብቄ ነው.....ሁሌም በልብህ አኑረኝ" ይላል የተቀመጠለት መልእክት
ሚኪ እየተካሄደ ያለውን ነገር ማመን አልቻለም የስልኩን ድምጽ ጨመረና ድጋሚ ጆሮው ላይ አደረገው ግን ምንም የተለወጠ ነግር የለም የሚሰማው የሰላምን በለቅሶ የታጀበ የመ ሰናበቺያ ድምጽ ነው።.....
ሚኪ እየሮጠ ወደ መኪናው ገባና እግረ መንገዱን ሂዊን ከቤት እንድትወጣ ነገራት....
በፍጥነት የቤታቸውን ፒሳታና ሽሩንቁላ መንገድ አልፋ አስፋልት ዳር ጠበቀችው.....
ሚኪም እንደ ጀት እያከነፈው አጠገቧ መጥቶ ቆመ.....ሂዊ ጋቢናውን ከፍታ ገባች....
"እንዴ ሚኪ ምን ሆነህ ነው...? አለችው ሂዊ የተጨነቀ ፊቱን አትኩራ እየተመለከተች...
"ሂዊ ሰላሜን ሊገሏት ነው.."
"ምንድነው የምታወራው እነማን ናቸው የሚገሏት...?"
"ሂዊ አጠይቂኝ ከዚህ በላይ እኔም አላውቅም....መልእክት አሥቀምጣልኝ አዳምጬው ነው"
"ስንት ሰአት ላይ ነው ያስቀመጠችልህ...?"
"1፡30 አከባቢ"
"እሺ ወዴት ነው እየሄድን ያለነው ..?"
"እነ ሰላም ቤት ነዋ..."
"ሚኪ ተረጋጋ....አሁንኮ 5 ሰአት ሊሆን ነው ..."
"ምን ለማለት ፈልገሽ ነው..?"
"ለሁሉም ነገር አርፍደናል እያልኩህ ነው"
"እንዲህ አትበይኝ ሠላሜ ምንም አትሆንም....ታያለሽ ደህና ሁና እናገኛታለን" ጮኸባት
"ሚኪ እሷ ምንም ትሆናለች እያልኩህ አይደለም የኔና የአንተ እዛ መገኘት ህይወታችንን ሊያሳጣን ይችላል.....እቅዳችንም ሊበላሽ ይችላል....ምክንያቱም መኩሪያው አንተ የልጁ ፍቅረኛ እንደሆንክና እኔ ደግሞ የበፊት ቅምጡ እንደነበርኩ ያውቃል ስለዚህ ሁለታችንን አንድ ላይ ቢያየን ምን የሚፈጠር ይመስልሃል" አለችው ለዛ ባለው አነጋገር...
ሚኪ መኪናውን አቆመውና መሪውን ደገፍ ብሎ"እሺ አሁን ምንድነው ያሰብሽው....በምን መልኩ ስለ ሰላሜ ልወቅ....?"አላት ወደ ቀልቡ ተመልሶ
"ያሰብኩት ምን መሰለህ ሮቤልን አብሮን እንዲሄድ እናድርግና እሱ የተፈጠረውን ያጣራልን ማንነቱ ስለማይታወቅ አደጋ አይኖርብንም" አለችው...
ሚኪ ምንም ሳይመልስላት ወደ ኮሌፌ ነዳው.......ሰአቱ ስለመሸ መንገዱ ጭር ብሏል....በመጨረሻው ፍጥነት መኪናውን አከነፈው አየር ላይ የሚንሳፈፉ እሥኪመሥል ድረስ.... እንደደረሱ መኪናውን አቁሞ የሮቤልን የግቢውን መዝጊያ ይደበድቡ ጀመር....
ጋደም ብሎ መጽሀፍ እያነበበ የነበረው ሮቤል ሲጢጥ የሚል የሚኪና ድምጽ ሲሰማ ጆሮውን ወደ ውጪ ቀሰረው....ጭራሽ በሩ ሲቆረቆረ ሽጉጡን ከኮመዲኖው መ ሳቢያ አወጣና በጥንቃቄ ወደ በሩ አመራ.....ድብደባው አየለ...
ሊያጠቃው የመጣ ተሹሎክሉኮ እንጂ በግልጽ እንዲህ በር በሀይል እንደማይመታ ስላወቀ...
ድምጹን ዝቅ አድርጎ "ማነው...?" አለ
"ሮቤል ሚኪ ነኝ ክፈትልኝ.."
ሮቤል ኡፍፍፍፍ ብሎ በረዥሙ ተነፈሰ...
በሩን ከፍቶም አስገባቸው"እናንተ እብዶች ናችሁ እንዴ ምንድነው እንደሰይጣን አሥሬ ውልብ የምትሉብኝ"
"ሮቢ እርዳታህ ያስፈልገናል" አለችው ሂዊ...
ሮቤል የሚኪን ፊት ሲያይ በደህና እንዳልመጡ ገባው"ምነው በሰላም...?" አላቸው
የተከሰተውን መጥፎ ነገር ነግረውት በሚኪ መኪና ወደ ቦሌ ሄዱ....
ከመኩሪያው መኖሪያ ቤት መቶ ሜትር ርቀት ላይ ሰዋራ ቦታ ፈልገው መኪናዋን አቆሟትና ሮቤል የተፈጠረውን ለማወቅ ከሚኪናው ወርዶ በእግሩ ተራመደ....
ሮቤል ከሄደ ግማሽ ሰአት ቢቆጠርም እስካሁን አልተመለሰም...
ሚኪ ከዚህ በላይ መቆየት አልቻለም. ...ቁጭ ብሎ የመጠበቅ ትግስቱ ሲሟጠጥበት ከመኪናው ወረደ....ሂዊም ተከትላው ወርዳ ልታስቆመው ሞከረች....
"እባክህ ሚኪ በእኔ ይሁንብህ አትሂድ....መኩሪያው ወይ ይገል
118 viewsŘéçá Łoveĺý ğãl, 16:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 19:57:55 በቀልና ፍንጥርጣሪው

ክፍል


.
.
ምርጦቼ የቻናሉን ሜምበሮች ለመጨመርና አንባቢዎችን ለመጋበዝ ሲባል የእናንተ እርዳታ ያስፈልገኛል።እያንዳንዱ ሰው ይሄን post ለ5 ሰው ሼር ቢያደርገው 2000 ሜምበር እንገባለን..የሚለጠፉትን ማስታወቂያዎች ቀንሼ በቀን ሁለት ጊዜ አስነብባችሁዋለሁ



ሚኪም በተራው ልቡ በፍርሃት ይመታበት ጀመር..ወዲያው ማካሮፍ ሽጉጡን ከሽንጡ ስር መዥረጥ አድርጎ ሮቤል ላይ ደገነበት።..ኪላሽ የታጠቀው ጎልማሳም እየሮጠ መጥቶ እነ ሚኪ ላይ አነጣጠረባቸው
"ሮቤል እዚህ ጫካ ውስጥ ይዘኸን የመጣኸው ልትገለን ፈልገህ ነው..? ተናገር" አለ ሚኪ የሽጉጡን እጀታ ጠበቅ አድርጎ እየያዘ
ሮቤል ሽጉጥ እንደተደገነበት ሠው ምንም ፍርሃት አይታይበትም..ፊቱ ላይ ድንጋጤም ሆነ የአውሬነት ባህሪ አይታይም..እንዲያውም በሚኪ የተገረመ እስኪመስል ፈገግ ብሏል።
ሮቤል ኪላሽ ያነጣጣረውን ጎልማሳ ሰውዬ መሳሪያውን ዝቅ እንዲያደርግ ነገረው..
በሮቤል እንዲህ ዘና ማለት የተገረመው ሚኪ "ንገረን ልትገለንና ለአራዊቶች ልትሰጠን ነው..?" አለው በድጋሜ
ሮቤል በተረጋጋ መንፈስ "አይ ሚኪ ልገላችሁ ብፈልግኮ ገና ከመጀመሪያው እጨርሳችሁ ነበር..እዚህ ድረስ ምን አለፋኝ ከዋሻው ስር እቀብራችሁ ነበር..ማንም ሊያገኛችሁ አይችልም። ስማ ሚኪ እኔ ገዳይ አይደለሁም" አለው..
ሚኪ አሁን ፍርሃቱና ንዴቱ እየረገበለት ነው።
"ይሄስ መሳሪያ የታጠቀው ሰውዬ ምንድነው..?" አለው በአገጩ እየጠቆመ
"እሱ እዚሁ አከባቢ በግብርና የሚተዳደር ሰው ነው..ቦታውን አብጠርጥሮ ስለሚያውቀው አከባቢውን እንዲቃኝልኝ ቀጥሬው ነው።"
"እንዴት ላምንህ እችላለሁ..?"
"እኔን ከማመን ውጭ አማራጭ የለህም.. መጥታችሁብኝ እንጂ መጥቼባችሁ አይደለም።"
ሚኪ ሽጉጡን ከሮቤል ጭንቅላት ላይ አወረደው..ነገሮችን ሳያገናዝብ ባደረገው ነገር እጅግ አፈረ..ይቅርታ ማለት እንኳን አቅቶት እንደህጻን ልጅ አንገቱን ደፍቶ አይኑን መሬት ላይ ተከለ።
ምን ይፈጠር ይሆን በሚል ጭንቀት ተለጉማ የነበረችው ሂዊ አሁን ወደ እራሷ ተመለሰች..በፍርሃት የተወጠረው አእምሮዋም ረገብ ብሎ ተረጋጋች..ሮቤልን ተጠጋችውና "ይቅርታ አድርግልን ሮቢ አጥፍተናል"አለችው
"ሂዊ ይቅርታ አያስፈልገውም ያጋጥማል..እኔም በናንተ ቦታ ብሆን መጠራጠሬና መደንገጤ አይቀርም.." አላትና የሚኪን ትካሻ ያዝ አደረገው
"ሚኪ አታስብ የተፈጠረውን ሁሉ ሁላችንም መርሳት አለብን..ግን አንድ ነገር የምነግርህ እኔ እንዳመንኳችሁ ዝም ብለህ እመነኝ..ስለኔ የማታውቃቸው ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ ግን የምትጠራጠረኝ ከሆነ እንደቡድን ያቀድነውን ማሳካት አንችልም" አለው..
ሮቤል ከአቶ መገርሳ ጋር አሥተዋውቋቸውና እዚህ አከባቢ ቢመጡ እንደቤተሰብ እንዲንከባከባቸው አጥብቆ ነግሮት ወደ አዲስ አበባ ለመመለስ በዋሻው ውስጥ ጉዞ ጀመሩ..ትንሽ መንገድ እንደተጓዙ ሚኪ "ሰውዬውን ግን ታምነዋለህ..? ለገንዘብ ብሎ ለሌላ አካል አሳልፎ ቢሰጠንስ" ብሎ ጠየቀው
"አይ አይከዳኝም ሠውዬውን ለረጅም ጊዜ አውቀዋለሁ በዚያ ላይ እኛ የከተማ ሰዎች ነን ለቃላችን የማንታመነውና ገንዘብ የሚቀይረን..የገጠሩ ሰውኮ ማህተቡን አጥብቆ የሚይዝ..አምላኩን የሚፈራና ቃሉን የሚያከብር ነው። ቃላቸውን ከሚበሉ የወለዱትን ልጅ ቢክዱ ይሻላቸዋል"

ሸገር እንደደረሱ ሶስቱም መጀመሪ በገቡበት መተላለፊያ ወደ ሮቤል ቤት አመሩ።..እንደ ቡድን ስለሚያደርጉት ነገር ጊዜያዊ እቅድ ለማውጣት ተስማምተው ሂዊና ሚኪ ሶፋው ላይ አረፍ አሉ። ሮቤል ሠውነታቸው እንዲነቃቃ የማሽን ቡና ለማፍላት ወደ ኪችን ገባ ከትንሽ ደቂቃዎች በሁዋላ ይዞ ተመለሰና የተሰላና የበሰለ ሃሳብ እየሰነዘሩ መወያየት ጀመሩ..በመሀል ግን ለሚኪ የተደወለለት ስልክ ውይይታቸውን አቋረጠው..ሰላም ነበረች የደወለችው..አጋሮቹን ይቅርታ ጠይቆ አነሳው
"ሄሎ ሰላሜ"
"ሄሎ ሚኪዬ እንዴት ነህልኝ..?"
"አለሁልሽ..የት ነሽ አሁን..?"
"ምነው ግቢ መስዬህ ልጠልፈኝ ነው..እንዳማረህ ይቅር መኖሪያ ቤቴ ነኝ..ደግሞ ሚኪዬ ናፍቀኸኛል ነገ ግቢ መጥተህ አትወስደኝም..?"
"የኔ ፍቅር እኔም ናፍቀሽኛል በቃ ነገ እመጣለሁ..አሁን ግን ስራ ላይ ነኝ እወድሻለሁ ቻው"ብሎ ስልኩን ዘጋው።
ሂዊ ውስጧ ቅናት አጭሮባት ፊቷ ቅጭም አለ..ውስጧ የሚቀጣጠለው ሰደድ እሳት እንዳይታወቅባት የውሸት ፈገግ ብላ ለመሸፋፈን ሞከረች።ሚኪ ድጋሜ ላለመረበሽ ስልኩን አጥፍቶ ወደ ውይይቱ ተመለሱ።
***
ሰላም ሚኪ እንዲህ አጣድፎ ስልኩን መዝጋቱ አናዷታል
"ደግሞ በዚህ ሰአት የምን ስራ ነው..ከምሽቱ 1:30 ሆኗልኮ" አለችና ከተኛችበት ብድግ ብላ ትራሱን አቅፋ ቁጭ አለች። ማሰላሰሏን ቀጠለች "እረ እንዲያውም የስራ መልቀቂያ ወረቀት አስገብቺያለሁ ብሎኛልኮ..ታዲያ አሁን ምንድነው ስራው..?" ሰላም እራሷ በምትፈጥረው ጥርጣሬና መልስ የሌለው ጥያቄ ቅናት አደረባት
"መጠጥ ቤት ገብቶ ይሆን ወይስ እኔን በሌላ ተካኝ..? ሊሆን አይችልም ከኔ ውጭ ሌላ ሴት ልትኖርህ አትችልም.." አለችና ትራሱን ከእቅፏ አውጥታ ወረወረችውና በእንግልሏ ተኝታ ጣራ ጣራውን እያየች በሀሳብ ነጎደች።
የገባችበት ሀሳብ ግን ምንም ያህል አልቆየም..የሰራተኛቸው የማክዳ ለጆሮ የሚከብድ ጩኸት ከአልጋዋ አሥደንብሮ አወረዳት..እማ ምን ሆነችብኝ ብላ እየተጣደፈች ነጠላ ጫማዋን አጥልቃ ወደ ሳሎን ወረደች..ነገር ግን ያልጠበቀችውን ጨርሶንም ያልገመተችው ነገር አጋጠማት..ማክዳ ወለሉ ላይ ተዘርራለች 5 ሙሉ በሙሉ ጥቁር ሌዘር የለበሱና ማንነታቸው የማይለይ ሰዎች ሳሎኑን ሞልተውታል..
"ሂዱ ተበተኑ..እያንዳንዱን ክፍል ፈትሻችሁ ልጅቷን ይዛችሁዋት ኑ..ፓሊስ ሳይመጣ እንፍጠን"አላቸው አንደኛው በዙሪያው ለከበቡት እሱን መሰል ሰዎች
ሠላም ይሄንን ስትሰማ ህይወቷን ለማትረፍ እግር አውጭኝ ብላ ሮጣ ለመደበቅ ስትሞክር ያደረገችው ነጠላ ጫማ ጣ..ጣ..ጣ እያለ አሳበቀባት። ድምጹን የሰሙት ሰዎቹ አቅጣጫውን ተከትለው ደረጃውን በፍጥነት ወጡ..የቱንም ያህል ለመሰወር ጥረት ብታደርግም ሰዎቹ የትኛው ክፍል እንደገባች አይተዋታል።
ሠላም በሩን ከውሥጥ ቀርቅራ እጆቿ እየተንቀጠቀጡ ሚኪ ላይ ደወለች..የሚኪ ስልክ ዝግ ነው..ደግማ ደወለች
"እኔ ሚኪ ነኝ እባክዎት መልእክት ያስቀምጡ" ከሚለው የቮይስ ድምጽ በቀር ምንም መልስ የለም
እያለቀሰች ያለችበትን ችግርና ምን ያህል እንደምትወደው የሚገልጽ መልክት አስቀምጣለት ስልኩን ዘጋችውና አባቷ ጋር ደወለች..
ሠዎቹ ክፍሏ ደርሰው በሩን ለመክፈት ቁልፉን እየሠረሠሩ ነው..
መኩሪያው ከ3 ጥሪ በሁዋላ ስልኩን አነሳው
"ሄሎ ልጄ"
"አባዬ ድረስልኝ የሆኑ ሰዎች ሊገሉኝ ነው.."አለችው በሹክሹክታ
"ልጄ የት ነሽ..? እነማን ናቸው..?" አላት አፉ እየተሳሰረ
"ቤት ናቸው..አሁን የመኝታ ክፍሌን በሩን ሊሰብሩ እየታገሉ ነው..አባ ድረስልኝ"
በዚህ መሃል በሩ ተበረገደ ሰላምም በድንጋጤ የያዘችውን ስልክ ወደ መሬት ለቀቀችው..አምልጣ ህይወቷን ለማትረፍ እንደማትችል ስለተረዳች ለመፈራገጥ እንኳን ሙከራ አላደረገችም። ሰዎቹም ወደ ውስጥ ዘልቀው እራሷን እንድትስት አደረጓትና መኪና ውስጥ አሥገብተው ግቢውን ለቀው ሄዱ።

ይቀጥላል

ያልኩትን ከተረዳኸኝ ይሄን ፓስት ሼር

ይ ላ ሉ @officalemutiii
@officalemutiii
129 viewsŘéçá Łoveĺý ğãl, 16:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ