Get Mystery Box with random crypto!

በስራ ቦታችሁ ሆነ በተሰማራቹበት ስፍራ ጭንቀት የሚፈጥር ሁኔታ ቢፈጠርባችሁ። ያኔ ተረጋጉና ለውስጣ | 📯 Øfficiãl Ⓒherã📯

በስራ ቦታችሁ ሆነ በተሰማራቹበት ስፍራ ጭንቀት የሚፈጥር ሁኔታ ቢፈጠርባችሁ። ያኔ ተረጋጉና ለውስጣችሁ "እኔ #ደና ነኝ" በሉት።

የምታምኑት ሰው ቢያጭበረብራችሁ። ያኔ ተረጋጉና ለውስጣችሁ "እኔ ደና ነኝ" በሉት።
ይሆናል ብላችሁ የጠበቃችሁት እንዳልጠበቃችሁት ብትንትኑ ሲወጣ። ያኔ ተረጋጉና ለውስጣችሁ "እኔ #ደና ነኝ" በሉት።
የምትወዱትና የሚወዳችሁ ሰው ልባችሁን ሲሰብርባችሁ። ያኔ ተረጋጉና ለውስጣችሁ "እኔ ደና ነኝ" በሉት።
ብቸኝነት ድብርት በድብርት ሲያደርጋችሁ። ያኔ ተረጋጉና ለውስጣችሁ "እኔ ደና ነኝ" በሉት።
በነገሮች ምርጫ ያጣችሁ ቢመስላችሁም። ያኔ ተረጋጉና ለውስጣችሁ "እኔ ደና ነኝ" በሉት።

#ከምንም በላይ በውጪ የሚሆነው ሳይሆን በልባችን የምናስበው ይሆናልና በልባችሁ ጠንክሩ! በልባችሁ ጀግኑ! በልባችሁ መልካም ሁኑ! ለውስጣችሁ የራሳችሁን ጥንካሬ ከነገራችሁት ከውስጣችሁ ያላያችሁት ትልቅ ትልቅነት ይፈጠርና ያልገመታችሁት መልካም ነገር በላያችሁ ላይ ይሆናል።


ለውስጣችሁ አሁን በውጪ እየሆነ ያለባችሁን መልካም ያልሆነ ሁኔታ ደግማችሁ የምትነግሩት ከሆነ ግን፤ህይወታችሁ ወደ ባሰ አዘቅት ውስጥ ይገባል። አእምሯችሁም መፍትሄ ከማመንጨት ይልቅ አሁን ካላችሁበት የባሱ ችግሮችን እያሳያችሁ ጭንቀታችሁን ያባብስባችኋል። ስለነገ መልካም ራእይ እንዳይኖራችሁም እይታችሁን ይዘጋባችኋል።


በችግሮች ውስጥ ሆናችሁ "እኔ ደና ነኝ፣ እኔ አሸናፊ ነኝ፣ እኔ ቆንጆ ነኝ፣ እኔ ጤነኛ ነኝ፣ እኔ ጀግና ነኝ.... " በሉ! ያኔ ሊጥላችሁ የመጣው ፈተና አፍሮ ፊቱን አዙሮ ይሮጣል።
@offical_chera
@offical_chera @offical_chera