"ሕጋዊያን እንደ ሕጉ" ሺ መልካም ብትሰራ ሺ ዝምታ ነው። አንድ ክፋ ስትሰራ ሺህ ጫጫታ ነው። ተራራ የሚያህለው መልካምነት አይታይም ፣ ጉድፍ የምታህል ጉድለትህ ግን ትጎላለች። ስትመሰገን አብረው ያላመሰገኑ ፤ ስትራገም ሰልፋን ይመራሉ። በጎ ስትሆንላቸው ምስጋና በልብ ነው ያሉ ስታስቀይማቸው ግን ርግማን በአዋጅ ነው ይላሉ። ህግ የሌለ ይመስል ፣ በጎ ስትሰራ ድምፁን ያጠፋል ፣ ትንሽ የበደልህ ቀን ግን ፖሊስ ይልክብሃል ፣ ከሳሽ ፣ ምስክር ዐቃቤ ህግ ያሰናዳባሃል። ህጋዊያን እንደ ህጉ ናቸው። መልካም ስትሰራ አይሸልሙህም ባህሪያቸው አይደለምና ፣ ክፋ ስትሰራ ግን ይኮንኑሃል። ህጋዊያን ናቸውና። 215 viewsMercy Mekete, 17:35