Get Mystery Box with random crypto!

ሁለቱም ልጆቼ ይዤ ጎዳና ልወጣ ነዉ !! ቤትሽን ሽጪ ወይዘሮ አሊማ ግራኝ ነዋሪነቷ በወልቂጤ | ethio Nure( ኑሬ ረጋሳ)

ሁለቱም ልጆቼ ይዤ ጎዳና ልወጣ ነዉ !!

ቤትሽን ሽጪ

ወይዘሮ አሊማ ግራኝ ነዋሪነቷ በወልቂጤ ከተማ ሰላምበር ትምህርት ቤት አካባቢ ሲሆን ያለ ወላጅ አባታቸዉ ሁለት ልጆች ታሳድጋለች።

ባለቤቷ ሲሞት የሚኖሩበት ቤት ከፍሎ ያልጨረሰዉ 150 ሺህ ብር እዳ እንደነበረበትና አሁን ደግሞ ይህንንም እዳ ሁለት ቦርቀዉ ያልጨረሱ ትናንሽ ልጆች እያሳደገች ያለችዉ እናት ስራ የሌላትና ማንም የሚረዳት ቤተሰብ ፣ ወገን ስለሌላት እዳዉ ለመክፈል አቅም አጥታለች።

ባለቤቷ ከሞተ ሰባት አመት ሲሆን ሰዉ ቤት ልብስ እያጠበችና ቤት እያጸዳች ልጆቿን ታስተምራለች።

ባለቤቷ ከመሞቱ በፊት ቤቱን የገዛበት 150 ሺህ ብር ዕዳ ቀሪ እንዳለበት ታዉቃለች ይህንንም ዕዳ ለመክፈል አቅም እንደሌላትና የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲረዳት ትማጸናለች።

አበዳሪዎቿ በተለያዩ ጊዜያት እዳዉን አልከፈለችኝም እያሉ ፍርድ ቤት እያመላለሷት እንደሆነም ትናገራለች።

ሁሉም ከተባበረ እነዚህ ታዳጊዎችና ወላጅ እናታቸዉ ጎዳና እንዳይወጡ መታደግ ይቻላልና የምንችለዉ እንደግፋቸዉ።

በተለያዩ ጊዜያት አበዳሪዎች እየመጡ ቤቱን ሽጠሽ ክፈይን ብዙ ጊዜ ጠብቀንሻል እያሉ እያስጨነቋት ነዉ።

ታዳጊ ልጆቿ ነዋል ታጁ እና ፈምሂል ታጁ የእናታቸዉ ስቃይና ፈተና እያዩ በተለያዩ ጊዜ ገንዘቡን ክፈሉ እያሉ ወደ ቤታቸዉ የሚመጣዉ አበዳሪ እያዩ ቤት ሊያስለቅቁን ነዉ እያሉ ያለቅሳሉ።

መጪዉ የአረፋ በአል ይህን ቤተሰብ እንዳይበታተኑና ባሉበት ቤት ተረጋግተዉ ማክበር እንዲችሉ ዕዳቸዉን እንዲከፍሉና ቤቱ ተሽጦባቸዉ ጎዳና እንዳይወጡ እንድረስላቸዉ።

ወላጅ አባታቸዉ በህይወት የሌለዉ ልጆች ይዤ ሜዳ ላይ እንዳልወጣ የምትችሉትን ደግፍኝ በማለት ትጠይቃለችና እንድረስላቸዉ።

መርዳት ለምትፈልጉ

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - 1000281410923

ሂጅራ ባንክ - 100128616000

ስልክ ቁጥር
0913338733 ወይዘሮ አሊማ ግራኝ
0961540464

የሚሰጡ እጆች በፈጣሪ ዘንድ ትልቅ ቦታ አላቸዉ!!!

ኑሬ ረጋሳ

መስጠት ባንችልም ለደጋጎች ሼር እናድርግላቸዉ መረጃዉ