Get Mystery Box with random crypto!

Nuiman Edris Official

የቴሌግራም ቻናል አርማ nuiman_official — Nuiman Edris Official N
የቴሌግራም ቻናል አርማ nuiman_official — Nuiman Edris Official
የሰርጥ አድራሻ: @nuiman_official
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.70K

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-09-26 23:17:32 የወሎዬ ዉበት
(ኑዕማን ኢድሪስ)

ቡና ልጠጣ ከተቀመጥኩበት በረንዳ ላይ የተሰባሰቡ ሰዎች በክርክር ተጠምደዋል። የክርክራቸዉ መነሻ ሁለት ሴቶች በመንገድ ሲያልፉ ተመልክተዋል። ጸጉራ ላይ ሻሽ ጣል ያደረገቸዉ ሴት ዉበቷ የሁሉንም ወንድ ልብ ፈትኗል። አብራት ያለችዉ ሴት ግን ጸጉሯን አንጨባራ፤ በሱሪ ተወጥራ፤ በመነጽር ለመጉላት ብትሞክርም አዲሱ የንግድ ባንክ ህንጻ ስር እንደሚገኝ ሳር ቤት ኩስስ ብላ ታየቻቸዉ።

ሁለቱም ወሎዬ ሆነዉ እንዴት በዉበት ይቺኛዋ በለጠች በማለት ሁሉም የየራሱን ሀሳብ ይሰነዝራል።

እንደኔ ራቅ ብለዉ ዉይይታቸዉን የሚያደምጡ አባት "በወሬያችሁ ገባሁ መሰል ብለዉ..." ንግግራቸዉን ቀጠሉ። ሁሉም ወደሳቸዉ ዙሪዉ ምን እንደሚሉ ለማዳመጥ ትኩረት ሰጧቸዉ። "... ወሎ የዉበት ምንጭ፤ የቆንጆ መፍለቂያ ሀገር ናት። አርጎባዉ፤ ኦሮሞዉ፤ ሶዶማዉ ተደማምሮ ወሎዬ ነዉ። ታዲያ ሴቶቻችን በሄዱበት ሀገር ሁሉ የወንድን ልብ ከፍተዉ እንዲገቡ ዉበትንና ገራገርነትን አብዝቶ አድሏቸዋል። ሴቶች በተሰበሰቡበት ቦታ ላይ ወሎዬዋ ከሁሉም ደምቃና አሸብርቃ ትታያለች። ምክንያቱም ወሎዬ ናታ..." አሉ። እኔን ጨምሮ በበዙሪያችን ያሉ ሰዎች በሽማግሌዉ ሰዉ ንግግር ተስበናል። ማሳረጊያቸዉ ምን ይሆን ብለን ጓጉተናል። "... እና ልጆቼ የወሎ ሴቶች ከሁሉም ይበልጥ ተዉበዉ የመታየታቸዉ ሚስጥር 'ሂጃባቸዉ' ነዉ።..." አሉ። ሁላችንም ተደነቅን። ያላስተዋልነዉ ነገር ነበር።

ዙሪያ ገባዉን ቃኝተዉ እየሰማናቸዉ እንደሆነ ሲያዉቁ ንግግራቸዉን ቀጠሉ "... ሂጃብ ዉበት ነዉ። ጸጉሯ ላይ ሻሿን ጣል ስታደርግ ፀሃዩ ላይ ጨለማን ጥሎበት አለምን በዉበት እንደምታስገርመዉ ጨረቃ ደምቃ ትታያለች። ሃያማኖቷ ደግሞ ክብሯን ይጨምርላታል፤ ቁጥብ ያደርጋታል። እና ልጆቼ የሴቶቻችን ዉበት ሚስጥር ሂጃባቸዉ ነዉ። ይሄን ደግሞ አሁን አብረዉ ካለፉት ሴቶች አረጋግጣችኃል።" ብለዉ ንግግራቸዉን ቋጩ።

Telegram.me/Nuiman_9

Photo - ከዚሁ መንደር
297 views𝑛𝑢𝑖𝑚𝑎𝑛, 20:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-23 21:59:51
ወሎየዋ
(ኑዕማን ኢድሪስ)

አላህዬ አላህዋ
ማርካኛለች ወሎየዋ

ስጠኝና አሳርፈኝ
ሸህዋዉ ነዉ በኢባዳ ያሰነፈኝ
200 views𝑛𝑢𝑖𝑚𝑎𝑛, 18:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-22 21:04:22
ጀቢኝ
ኸሚስ ምሽት 2
(ኑዕማን ኢድሪስ)

በሂጃብ ተዉበሽ
ቡናዉን አፍልተሽ
ምሽቱን አድመቀሽ

ስትይ አወል ጀባ
እንደዉ ሆዴ ባባ

ከቡናዉ  በኃላ አንቺን ብጀቢኝ
ለጀሊሉ ሱጁድ አሁን ባረኩኝ

በይነል ፈኺዘይን ኒዕማዉን ይዘሽ
ሀላሌ አድርጌሽ ጀቢኝ እባክሽ

@Nuiman_9
285 views𝑛𝑢𝑖𝑚𝑎𝑛, 18:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-15 20:40:09
ኸሚስ ምሽት
- ተቀበይ
(ኑዕማን ኢድሪስ)

በሶለዋት ደምቆ
በዚክር አሸብርቆ

ቡናዉን አፍልተሽ
ነዱን አጫጭሰሽ
ስትይ አወል ጀባ

ቀና ብዬ ባይሽ
እስከ'ነ ሂጃብሽ
ከፊቴ ቁመሻል

ምርቃቱ ጠፋኝ
ጀሊሉ በቁድራዉ
ልቤን ጀብቶሻል

@Nuiman_9
497 viewsU, 17:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 08:20:49 ሚስኪኗ ሀያት
ፀሐፊ:- ኑዕማን ኢድሪስ
ተራኪ:- ሙስዓብ ዑመይር
.
የራሴን ጽሁፋ በራሴዉ ዩቱዩብ ቻናል ገብተዉ ይመልከቱ


177 viewsU, 05:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 15:11:28 Watch "ጀግናዉ የኢትዮጵያ ወታደር ረሱልን ሲያወድስ የሚያሳይ ቪድዬ #Neshida #ነሽዳ #ሙአዝ" on YouTube


200 views𝙣𝙪𝙞𝙢𝙖𝙣, 12:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 22:48:43


169 views𝙣𝙪𝙞𝙢𝙖𝙣, 19:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 13:13:07


190 views𝙣𝙪𝙞𝙢𝙖𝙣, 10:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 17:06:36
በጣም ተወዳጅ ነሽዳ ሊንኩን ተጭነዉ ይመልከቱ

434 views𝙣𝙪𝙞𝙢𝙖𝙣, 14:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-06 14:52:50

1.1K views𝙣𝙪𝙞𝙢𝙖𝙣, 11:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ