Get Mystery Box with random crypto!

አስተሳሰቦችና ፍልስፍናዎች @Zephilosophy «ፍቅር ቤቱን የሠራበት ልብ እንዴት የታደለ ነው | ኑ እናንብብ

አስተሳሰቦችና ፍልስፍናዎች
@Zephilosophy

«ፍቅር ቤቱን የሠራበት ልብ እንዴት የታደለ ነው? ምክንያቱም ከዓለም ጭንቀት ሁሉ መዳኛው ፍቅር ነውና። ፍቅር ትዕግስትና ማመዛዘንን ወደ ምንምነት የሚቀይራቸው የነጐድጓድ ኃይል ነው። አፍቃሪ ስለራሱ ደህንነት ማሰብ አያውቅበትም፤ የትችት ተራራ ለእሱ ከገለባ ክምር የቀለለ ነው። እንዲያውም ትችት የፍቅሩን ኃያልነት የሚጨምርለት ጉልበቱ ይሆናል።»

ሱፊስቶች

«ዓለም በሙሉ ዕብድ ነው ይለኛል። በእርግጥም ዕብድ ነኝ። አናንተም ደግሞ ዕብድ ናችሁ። ዓለም በሙሉ ዕብድ ነው። ለመሆኑ ዕብድ ያልሆነስ ማን ነው? ይሁንና እነዚህ ዕብዶች ደግሞ እኔን ዕብድ በማለት ይጠሩኛል። ከእነሱ አንዳንዶቹ ለስማቸውና ለክብራቸው ያበዱ ናቸው። አንዳንዶቹ ገንዘብ በመከተል አብደዋል። ሌሎቹ ደግሞ ሥጋን ውበትን እየተከተሉ ያብዳሉ። እሱ ፈጣሪውን ተከትሎ ያበደ ግን በእርግጥም የተባረከ ነው። እኔ እንዲህ ዓይነቱ ዕብድ ነኝ።»

ባንግ አቫድሁት

"የሰው ልጅ ምኞት ገደብ የለሽ ነው። ምኞት በጥም የተቃጠለ ሰው የሚጠጣው ጨዋማ ውሃ ነው፤ ጨዋማ ውሃ የውሃ ጥምን አለማርካት ብቻ ሳይሆን ጥሙ እየጨመረ እንዲሄድ ማድረጉ የማይቀር ነውና። ስለዚህም የሰው ልጅ የእርካታ ምንጩ ከውስጡ ነው፤ በምኞቱ ግን አለመርካታ ብቻ ሳይሆን ስቃዩም እየጨመረ ይሄዳል። እናም ለምኞትህ ገደብ አበጅለት"

ሃይዲገር

"ስለሦስተኛው የዓለም ጦርነት አላውቅም፧ ስለአራተኛው ግን ልነግራችሁ እችላለሁ አራተኛው የዓለም ጦርነት ብሎ ነገር የለም፤ ምክንያቱም ሦስተኛው ሁሉን ነገር ይጨርስዋልና!"

አልበር አንስታይን

"ሰው የሚያፈቅረውን ነገር ይሆናል። ድንጋይ ካፈቀረ ድንጋይ ይሆናል፤ የሰውን ልጅ ካፈቀረ ደግሞ ሰው ይሆናል፤ ፈጣሪን ካፈቀረ ደግሞ... ከዚህ በላይ እንኳን ማተት የለብኝም... አለበለዚያ በድንጋይ ልትወግሩኝ ትችላላችሁ።"

ኦውግስቲን

"በሰዎች ክፉ ተግባርም ሆነ ምግባር ለመፍረድ ስንነሳ የእኛም ክፉነት እየተገለጠ ይሄዳል። ለማንኛውም የሰው ልጅ የምግባር በሽታ ጠንካራው መድኃኒት ፍቅር ብቻ ነው»

ራማያና

"የሰው ልጅ የፈጣሪውን ማንነት ተረድቶ በእሱ ማንነት በምድር ላይ ለመመላለስና የእሱንም ዘላለማዊነት ለመልበስ ዋስትና የሚሆነው ሃይማኖቱ ሳይሆን የተሰጠውን ተፈጥሮአዊ ብቃት ለመግለጥ በፈጣሪ መንገድ ላይ መገስገስ ብቻ ነው።።"

ሂንዱይዝም

«ራስን አለማወቅ ይጎዳል፤ ራስን አለማወቅ ሕይወትን በሙሉ ትርጉም አልባ ያደርገዋል። ሁሉን ነገር ልታውቁ ብትችሉ እንኳ ራሳችሁን ግን አላወቃችሁም፤ የሚገርመው ግን ከእውቀታችሁ በፊት ልታውቁት የሚገባው ራሳችሁን ነበር።"

ኦሾ

«አብዛኛው የሰው ልጅ የሚከተላቸው እምነቶችና በእምነቱ ውስጥ የሚፈፅማቸው ድርጊቶች መነሻቸው ልማድ ነው። እምነት በዕውቀት መገለጥን ካልያዘ የሚጠይቀውም ሆነ ምላሽ የሚያገኝለት ጥያቄ ስለማይኖር ሌሎች ስለሚያደርጉት ብቻ የሚደረግ ከንቱ ተግባር ሆኖ ይቀራል።»

ዜኖች

"የሰው ልጅ ሊኖር የሚገባው ዛሬን ነው፤ ስለነገ እያሰቡ ዛሬን መኖር ዛሬ ልንጨብጠው የምንችለውን ነገር ለነገ አሳልፎ የመስጠት ተግባር ይሆናል። ብዙዎች እምነታቸውን በነገ ላይ በማንጠልጠላቸው ምክንያት ዛሬ እምነታቸው ሊሰጣቸው የሚችለውን በረከት እያጡት ይገኛሉ። "

ዜኖች

"ቀላል፣ የተዋበ፣ ፀጥታ የሞላበት፣ ተደሳችና የተባረከ ሕይወት መኖር የምትሻ ከሆነ የአእምሮን ስግብግብ ጥያቄዎች ጣላቸውና በምትካቸው የልብህ መልሶች ተካባቸው። የአእምሮ ጠቢብነት ነገሮችን እያወሳሰበ ዕለት ተዕለት ጥያቄን መከመር ነውና የሕይወትህ ጌታ ልብህን አድርገው። "

ኦሾ

"ፍቅር በውስጥህ ቦታን ሲያገኝ የውበት መገለጫው ትሆናለህ። ፍቅር የያዘው ሰው ውበት የሚንፀባረቅበት መስተዋት ነው። ምክንያቱም ውበትም ሆነ ነፀብራቁ መነሻቸው ፍቅር ነውና... የሁለቱም ምንጭ ፍቅር ነው።"

ሱፊስቶች

#Abel
@Zephilosophy
@Zephilosophy