Get Mystery Box with random crypto!

#ከድንጋይ_ፈላጩ_ተማር በስተመጨረሻ የእምቅ ችሎታ ጉብታህን ስታልፍ ሰዎች ስኬትህን የአንድ ቀን | ኑ እናንብብ

#ከድንጋይ_ፈላጩ_ተማር

በስተመጨረሻ የእምቅ ችሎታ ጉብታህን ስታልፍ ሰዎች ስኬትህን የአንድ ቀን ስኬት ብለው ይጠሩታል፡፡ የውጪው ዓለም ሁሉንም የለውጥ ደረጃዎችህን አያይም፡፡ ሰዎች ማየት የሚችሉት ድራማዊ የሆነውን የለውጡን ፍሬ መገለጫ ብቻ ነው። አንተ ግን ለዚህ ያበቁህ ምንም ለውጥ እያሳየህ በማይመስል ሰዓት ሁሉ የሰራሀቸው ጠንካራ ስራዎች መሆናቸውን ታውቃለህ፡፡ በአንድ ነገር ላይ ለመንገስ ትዕግስት የግድ አስፈላጊ ነገር ነው።

ከውጤታማዎቹ የኤን ቢ ኤ ቡድኖች መካከል ተጠቃሽ የሆነው ሳን አንቶኒዮ ስፐርስ ከማህበራዊ ቀራፂው ከጃኮብ ሪስ ወስዶ በተጨዋቾቹ ሎከር ላይ የሰቀለው አንድ ጥቅስ አለ፡፡ ጥቅሱ እንዲህ ይላል፤ ሁሉ ነገር ምንም ለውጥ የማያመጣ በሚመስለኝ ጊዜ ሄጄ የማየው አንድ ድንጋይ ፈላጭ አለ፡፡ ይህ ፈላጭ ድንጋዩን በድንጋይ መፍለጫው መቶ ጊዜ ይመታዋል፡፡ በዚህ ሁሉ ድካም ውስጥ ግን ምንም የመሰንጠቅ ምልክት ድንጋዩ ላይ አይታይም፡፡ በመቶ አንደኛው ምት ግን ድንጋዩ ለሁለት ይሰነጠቃል፡፡ እኔ ግን ድንጋዩን የሰነጠቀችው 101ኛዋ ምት ብቻዋን ሳትሆን መቶ አንዱም ምቶች በአጠቃላይ ተደማምረው እንደሆነ አውቃለሁ፡፡”

ከልማድ ኃይል መጽሐፍ የተወሰደ

@Human_Intelligence
@Human_Intelligence