Get Mystery Box with random crypto!

ነግሬሽ ነበረ ሴት ክብሯን ረስታ ፣ ጭኗን እንዳታምነው ሁሉን ያጣል ብዬ ፣ የሁሉም የሆነው!!! | ኑ እናንብብ

ነግሬሽ ነበረ

ሴት ክብሯን ረስታ ፣ ጭኗን እንዳታምነው
ሁሉን ያጣል ብዬ ፣ የሁሉም የሆነው!!!

ነግሬሽ ነበረ
ውበት ደም ግባትሽ ፣ ሁሉን እንደሚስብ
የወንድ ልጅን ዐይን..
ከተበተነበት ፣ እንደሚሰበስብ
ነግሬሽ ነበረ...
ትንሽ ስትዘነጊኝ ፣ ብዙ እንደማስብ!!!

ነግሬሽ ነበረ... ባትሰሚኝም እንኳ
ሳሙና ነው ብዬ ፣ የቆንጆ ሴት መልኳ
እድፋም ስሜቶችን...
አሽታ ስታነፃ ፣ ያበቃል ታሪኳ!!!

ነግሬሽ ነበረ
ሴት ልጅ ስታማርጥ ፣ ለራሷ ምራጭ ናት
በክብር ነው እንጂ...
በመውለድ አይደለም ፣ የሚኮነው እናት፡፡
ክብረ ቢስ ህይወቶች ፣ ጣፍጠው አይቀጥሉም
የወለዱ ሁሉ እናቶች አይደሉም
ነግሬሽ ነበረ
እናትነት ስሟ
ከክብሯ ነው እንጂ ፣ ከልጇ እንዳልመጣ
ወልዳም ምንም ነች ፣ ሴት ክብሯን ስታጣ።

ነግሬሽ ነበረ...
ሴት ክብሯን ስትጥል ፣ እድሜዋ ይሔዳል
የወንድ ልጅ ቤቱ...
የሴትልጅ ውበት ነው ፣ ካየበት ይለምዳል፡፡

ነግሬሽ ነበረ...
ጭንሽ ሴትነትን ፣ ከቶ እንደማይበልጠው
ቁንጅናም ይረክሳል!
ብቻውን እንዲቀር ፣ ሁሉም ከመረጠው!
ብነግርሽ ብነግርሽ ፣ ባትሰሚኝም ቅሉ
"ሰደበኝ" በማለት ፣ ታወሪያለሽ አሉ
ልክ ነሽ አንዳንዴ
እውነቶች ውሸት ፊት ፣ ስድብ ይመሥላሉ።

ሞኝ ሰው ሲመክሩት
ሞኝ ሰው ሲነግሩት
የቀኑበት መስሎት ፣ በከንቱ ቢታበይ
ግን እነግርሻለሁ!
ነግሪያት ነበር ስል
ቀንቶ ተናገረኝ ፣ ወይም ሰደበኝ በይ።

ግን እነግርሻለሁ
ግን እመክርሻለሁ
ሴት ልጅ ክብሯ ሲጎድል ፣ ውበቷ አይመችም
ሁሉም ይመኟታል ፣ ከአንዱም ልብ የለችም!!!

በላይ በቀለ ወያ እንደፃፈው


@NuEnanbib