Get Mystery Box with random crypto!

,,,,,የታለች,,,,, ሄዋን ወዴት አለች በተፈጥሮ ውበት ኮርታ የደመቀች፣ ፀጉሯ አልበቃ ብሏት | ኑ እናንብብ

,,,,,የታለች,,,,,

ሄዋን ወዴት አለች
በተፈጥሮ ውበት
ኮርታ የደመቀች፣
ፀጉሯ አልበቃ ብሏት
ሂውማን ያልቀጠለች፡፡

አምሮ ለመታየት
በሜካፕ ያለወዛች፣
ጣቶቿን ሞርዳ
ጥፍር ያልሰካካች::

ቅርፃዋን ለማሳመር
በስንፖንጅ ያልተመካች፣
በመሰልጠን ሰበብ
እርቃንዋን ያልወጣች::

ክቡሩን ገላዋንን
በወግ የሸፈነች
ማንነትዋን ሳትክድ
እራሳዋን የሆነች፣
ያቺ ልባም ሄዋን
ንገሩኝ የታለች?!

ሰብለወንጌል

@getem
@NuEnanbib