Get Mystery Box with random crypto!

ኑ በጌታ ደስ ይበለን!🎧🎤..🎸.🎵..

የቴሌግራም ቻናል አርማ nubegetadesyibelen — ኑ በጌታ ደስ ይበለን!🎧🎤..🎸.🎵..
የቴሌግራም ቻናል አርማ nubegetadesyibelen — ኑ በጌታ ደስ ይበለን!🎧🎤..🎸.🎵..
የሰርጥ አድራሻ: @nubegetadesyibelen
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 146
የሰርጥ መግለጫ

እዚህ ቻናል ላይ :-
👉አዳዲስና ዘመን የማይሽራቸዉ ዝማሬዎች 👉አምልኮዎችን(Live Songs)
👉 ስብከቶች፣ የመ.ቅ ጥቅሶችን
👉ልዩ መልዕክት ያላቸውን ፒክቸሮችን ያገኛሉ!
ይ🀄️ላ🀄️ሉን
👉ለ አስታያየት አና ማገልገል ለምትፈልጉ
@Wendi4th
@bibi_son

Ratings & Reviews

4.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-12 22:39:56 የወደድከኝ ጊዜ

ሰማይ የለም ነበር ፣ ገና አልተዘረጋም
ቀን አልተቆጠረም ፣ አልመሸም አልነጋም
ጨረቃ የለችም ፣ በምሽት ላይ ደምቃ
ጸሐይም አታውቅም ፣ ወጥታና ጠልቃ

የወደድከኝ ጊዜ.......
የብሱ ተገላልጦ ፣ ምድር አልተባለም
ውኃ በአንድ ስፍራ ፣ አልተሰበሰበም
ምድር መሽከርከሯን ፣ ገና አልጀመረችም
የሜዳን ቡቃያ ፣ አላበቀለችም

የወደድከኝ ጊዜ.......
ወፎች በሰማይ ላይ ፣ መብረር አልጀመሩም
አራዊቱ ሁሉ ፣ በስም አልተጠሩም
ምድርን ሊያጠጡ ፣ ወንዞች አልፈሰሱም
አሦች በባሕር ውስጥ ፣ አልተንቀሳቀሱም

የመረጥከኝ ጊዜ.......
እኔ እንኳን ራሴ ፣ ገና አልተፈጠርኩም
አንተን አላወ'ኩም ፣ አንተን አልመረጥኩም
ያለነቀፌታ ፣ ያለ እንከን አ'ረከኝ
ህፀፅ የሌለበት ፣ እድፍ አልባ አ'ረከኝ
አለም ሳይፈጠር ፣ ይሄ ሁሉ ሳይሆን
በክርስቶስ መረጥከኝ ፣ በፍቅር እንድሆን

እናማ እንዲህ አልሁህ.......
ሞቴን ልትሞትልኝ ፣ ግድ ያለህ መሞቴ
የዘላለም እረፍት ፣ የሁሌ ሰንበቴ
የሕይወት ቃል ያለህ ፣ ቃል የታጣልህ ቃል
ፍቅር ከሚለው ቃል ፣ ማፍቀርህ ይልቃል

ሄኖክ አሸብር

@Excellent_youth
@Excellent_youth
23 viewsM€ŗ ý, 19:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 14:35:40 ራእይ 1 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁵ እንዲሁም ታማኝ ምስክር፣ ከሙታን በኵርና የምድር ነገሥታት ገዥ ከሆነው ከኢየሱስ ክርስቶስም ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። ለወደደንና ከኀጢአታችንም በደሙ ነጻ ላወጣን፣

⁶ አምላኩንና አባቱን እንድናገለግልም መንግሥትና ካህናት ላደረገን፣ ለእርሱ ክብርና ኀይል ከዘላለም እስከ ዘላለም ይሁ አሜን።

⁷ እነሆ፤ በደመና ይመጣል፤ የወጉት እንኳ ሳይቀሩ፣ ዐይን ሁሉ ያየዋል፤ የምድርም ሕዝቦች ሁሉ ከእርሱ የተነሣ ዋይ ዋይ ይላሉ።
አዎ! ይህ ሁሉ ይሆናል፤ አሜን።

⁸ “ያለውና የነበረው፣ የሚመጣውም፣ ሁሉን ቻይ ጌታ አምላክ፣ አልፋና ዖሜጋ እኔ ነኝ” ይላል።
62 viewsBîbî, 11:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 08:04:30 1ኛ ቆሮንቶስ 15 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁵⁴ #የሚጠፋው_የማይጠፋውን_የሚሞተውም_የማይሞተውን_በሚለብስበት_ጊዜ፣ “#ሞት_በድል_ተዋጠ” ተብሎ የተጻፈው ቃል ይፈጸማል።

⁵⁵ እንዲሁም፣ “ሞት ሆይ፤ ድል መንሣትህ የት አለ? ሞት ሆይ፤ መንደፊያህስ የት አለ?”።

⁵⁶ የሞት መንደፊያ ኀጢአት ነው፤ የኀጢአትም ኀይል ሕግ ነው።

⁵⁷ ነገር ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ድልን ለሚሰጠን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን።

⁵⁸ ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፤ ጸንታችሁ ቁሙ፤ በምንም ነገር አትናወጡ። ለጌታ ሥራ ዘወትር የምትተጉ ሁኑ፤ ምክንያቱም ለጌታ የምትደክሙት በከንቱ እንዳልሆነ ታውቃላችሁ።
88 viewsBîbî, 05:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-24 19:42:41 “እናንተም በመጨረሻው ዘመን ሊገለጥ የተዘጋጀው ድነት እስኪመጣ ድረስ በእምነት አማካይነት በእግዚአብሔር ኀይል ተጠብቃችኋል።”
— 1ኛ ጴጥሮስ 1፥5 (አዲሱ መ.ት)
96 viewsBîbî, 16:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-21 22:33:59 የውሃ ጥም ሲይዘን ቦዶ የነበረውን ብርጭቆ በውሃ እንደምንሞላ ከዛም ጥማችንን እንደምናረካ፤

#የብጭቆው በውሃ መሞላት የአንተ የውሃ ጥም ነው።
#የመርካትህም ምስጢር መጠማትህ ነው።

ለጥምህና ለራብህ እርካታ የሚዮንህ አንተ የተጠማሀውና የተራብከው እራሱ ነው ነገር ነው ሚሆነው፤ ከዛውጭ ከሆነ ማስታገሻ ቢሆን እንጂ መቼም እርካታ አይሆንም።

#ትረካ ዘንድ እንደምትጠማ እንዲሁ እግዚአብሔርን የመፈለግ ጥማትና ረሀብ ሲኖረን እንረካ ዘንድ እግዚአብሔር እራሱን ይገልጥልናል፤ የሚያረካህ የተጠማሀው ነገር እንደሆነ እንዲሁ እግዚአብሔርን እርሱን ተጠምተሀልና ጌታ እግዚአብሔር #ለጥምህ_እርካታ_ሊሆን_እራሱን_ይገልጣል።

#ጥማትህ_እግዚአብሔር፤
እርካታህ_እራሱ_እግዚአብሔር።


በሰማያት ላይ የተቀመጥከው
ልቤን ማደሪያ ዙፋንህ ያረከው
እንዳተ ሚሆን ሚያክልህ የለም
ያውና ሕያው ለዘለዓለም
ያውና ሕያው ለዘለዓለም
117 viewsBîbî, 19:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-10 21:10:58 “ምንጊዜም በጌታ ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜ እላለሁ ደስ ይበላችሁ።”

“ምንጊዜም በጌታ ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜ እላለሁ ደስ ይበላችሁ።”

“ምንጊዜም በጌታ ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜ እላለሁ ደስ ይበላችሁ።”

“ምንጊዜም በጌታ ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜ እላለሁ ደስ ይበላችሁ።”

“ምንጊዜም በጌታ ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜ እላለሁ ደስ ይበላችሁ።”

“ምንጊዜም በጌታ ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜ እላለሁ ደስ ይበላችሁ።”
— ፊልጵስዩስ 4፥4 (አዲሱ መ.ት)



https://t.me/Nubegetadesyibelen
https://t.me/Nubegetadesyibelen
134 viewsBîbî, 18:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 12:13:19
የሚያድነዉን እውነት መውደድ፤ ማክበርና መታዘዝ ይሁንልን!


Join
@Nubegetadesyibelen
123 viewsŴęŋđĺ Ťŷpíŋğ..., 09:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-30 21:50:58 #የኢየሱስ_ቅድምና ( #2 )

በአገልጋይ ብርሃኑ ታምራት

ጌታ ኢየሱስ በሥጋ የተገለጠው ከጊዜ በኋላ ከድንግል ማርያም ነው።ይሄ ግን ለመገለጥ ሥጋን መዋሃድን እንጂ ጅማሬን አያሳይም።ኢየሱስ አልፋ ነው። #የመጣውም_ከአለበት_ወደ_አለበት_እንጂ_ከአለበት_ወዳልነበረበት_አይደለም።እንዲህ ተብሎ እንደተፃፈ፦

ዮሐንስ 1
¯¯¯¯¯¯⁹ ለሰው ሁሉ የሚያበራው እውነተኛው ብርሃን #ወደ_ዓለም_ይመጣ_ነበር።
¹⁰ #በዓለም_ነበረ፥ #ዓለሙም_በእርሱ_ሆነ፥ #ዓለሙም_አላወቀውም።

#ወደ_ዓለም_በሥጋ_የመጣው_ኢየሱስ_በዓለም_ውስጥ_የነበረው_ነው። #የነበረው_መጣ።ያልታየው በሥጋ ተገለጠ።ዓለምን የፈጠረውም እርሱ ነው።በዓለምም ነበረ።ዓለም እንዲያየውና የማዳን ሥራውን ለመፈፀምም በሥጋ ተገለጠ።

በሥጋ ተገልጦ መመላለሱን፤ከሴት ተወልዶ የሰው ልጅ መባሉን ያዩ ሕልውናውን በሥጋ ከተገለጠበት ጊዜ ጀምረው እንዳይቆጥሩት "በመጀመሪያው ቃል ነበር…ቃልም ሥጋ ሆነ" በማለት የኢየሱስ ክርስቶስን ቅድምና አሰምቶ ዮሐንስ ተናገረ።

ያመንበት ኢየሱስ አልፋ ነው።ለፍጥረት መጀመሪያን የሰጠ መጀመሪያ የለሽ ቀዳማዊ እርሱ ነው።መጨረሻ የሌለው ዖሜጋም እርሱ ነው።ለፍጥረት ፍፃሜን ይሰጣል።እርሱ ግን ፍፃሜ የለውም።

በለበሰው ሥጋ ዘመን ቢቆጠርለትም በመለኮታዊ ማንነቱ መጀመሪያም መጨረሻም የለውም።
እንዲህ ተብሎ እንደተፃፈ፦
ዮሐንስ 8
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁵⁷ አይሁድም፦ ገና አምሳ ዓመት ያልሆነህ አብርሃምን አይተሃልን? አሉት።
⁵⁸ #ኢየሱስም፦ #እውነት_እውነት_እላችኋለሁ፥ #አብርሃም_ሳይወለድ_እኔ_አለሁ አላቸው።

ደግሞም ባለ ራእዩ ዮሐንስን እንዲህ አለው፦
ራእይ 1
¯¯¯¯¯¯¹⁷ ባየሁትም ጊዜ እንደ ሞተ ሰው ሆኜ ከእግሩ በታች ወደቅሁ። ቀኝ እጁንም ጫነብኝ እንዲህም አለኝ፦ አትፍራ፤ #ፊተኛውና_መጨረሻው_ሕያውም_እኔ_ነኝ፥
¹⁸ ሞቼም ነበርሁ እነሆም፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ፥ የሞትና የሲኦልም መክፈቻ አለኝ።

የኢየሱስ ሕልውና(መኖር) ዓለም ከተፈጠረ ዘመን ከተቆጠረ በኋላ ሳይሆን ዓለም ሳይፈጠር ዘመን ሳይቆጠር ነው።
ዓለም ሳይፈጠር ለኖረ፤ዓለምንና በዓለምን ያለውን ለራሱ ለፈጠረ ለጌታ ኢየሱስ ክብር ይሁን።አሜን።።

16/09/2014 የጌታ ዓመት
65 viewsBîbî, 18:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-30 21:50:57 #የኢየሱስ_ቅድምና

በአገልጋይ ብርሃኑ ታምራት

የኢየሱስ ሕልውና የጀመረው በድንግል ማርያም ማኅፀን አይደለም። #ኢየሱስ_መጀመሪያ_ነው_እንጂ_መጀመሪያ_የለውም።ጊዜን የፈጠረ እርሱ ነውና ዘመን አይቆጠርለትም።

ዮሐንስ ወንጌሉን ሲጀምር የሚሰብከው ኢየሱስ ዓለም ከመፈጠሩ በፊት እንደነበር በመናገር ይጀምራል።

"በመጀመሪያው ቃል ነበር" በማለት በመጀመሪያ ያለው ጊዜ የመለኮትን ቅድምና ለመናገር ነው።በሥጋ መገለጥ ከዘመን ኋላ የተከናወነ ሲሆን የኢየሱስ ሕልውና ግን ከዘመን ዘመናት በፊት ዘመን የሚባል ቆጠራ ሳይኖር፤ዓለማት ገና ሳይፈጠሩ ነው።

#ኢየሱስ #ቃል_የተባለው_በሁለት_ምክንያት_ነው።

#አንደኛ፦ የመሆን(የኲነት) ስሙ ነው።ማለትም ለአብ ቃሉ ነው።አብ የሚናገረው በኢየሱስ ቃልነት አማካኝነት ነው።በአጭሩ ኢየሱስ የአብ ቋንቋው ነው።የሰው ሁሉ ቃል ዝርው(በአየር ተጭኖ ወደ ጆሮ የሚደርስ ከዛም የሚበተን) ሲሆን ኢየሱስ ግን ለአብ አካል ያለው ቃሉ ነው።እንዲህ ተብሎ እንደተፃፈ፦
“በደምም የተረጨ ልብስ ተጐናጽፎአል፥ #ስሙም #የእግዚአብሔር_ቃል ተብሎአል።”
— ራእይ 19፥13

#ሁለተኛው፦ ቃል የተባለው የአብ መገለጥ ስለሆነ ነው።አብን ያየው ማንም የለም።ኢየሱስ ግን አብን ገለጠው፥ተረከው፥አብራራው።ስለዚህ በልብ ያለ ሀሳብ በቃል ሲነገር እንደሚገለጥ እንዲሁ ኢየሱስ የአብ መገለጥ ነው።ኢየሱስ የአብ መልክ፥የባሕርዩና የክብሩም መንፀባረቅ ነው።እንዲህ ተብሎ እንደተፃፈ፦

ዕብራውያን 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¹ ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በብዙ ዓይነትና በብዙ ጎዳና ለአባቶቻችን በነቢያት ተናግሮ፥² ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት #በልጁ_በዚህ_ዘመን_መጨረሻ_ለእኛ_ተናገረን፤³ #እርሱም #የክብሩ_መንጸባረቅና #የባሕርዩ_ምሳሌ_ሆኖ፥ ሁሉን በስልጣኑ ቃል እየደገፈ፥ ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ፤

ስለዚህ ኢየሱስ የአብ ቃሉ ነው።አንድም አብ የሚናገርበት፥አንድም አብ የተገለጠበት ነውና።

ይቀጥላል………

15/09/2014 የጌታ ዓመት
50 viewsBîbî, 18:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-27 00:05:31
1ኛ ቆሮንቶስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁶ ወንድሞች ሆይ፥ መጠራታችሁን ተመልከቱ፤ እንደ ሰው ጥበብ ጥበበኞች የሆኑ ብዙዎች፥ ኀያላን የሆኑ ብዙዎች፥ ባላባቶች የሆኑ ብዙዎች አልተጠሩም።
²⁷ ነገር ግን እግዚአብሔር ጥበበኞችን እንዲያሳፍር የዓለምን ሞኝ ነገር መረጠ፤ ብርቱንም ነገር እንዲያሳፍር እግዚአብሔር የዓለምን ደካማ ነገር መረጠ፤
²⁸ እግዚአብሔርም የሆነውን ነገር እንዲያጠፋ የዓለምን ምናምንቴ ነገር የተናቀውንም ነገር ያልሆነውንም ነገር መረጠ፥
@Nubegetadesyibelen
97 viewsŴęŋđĺ Ťŷpíŋğ..., 21:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ