Get Mystery Box with random crypto!

Nolawi ኖላዊ

የቴሌግራም ቻናል አርማ nolawii — Nolawi ኖላዊ N
የቴሌግራም ቻናል አርማ nolawii — Nolawi ኖላዊ
የሰርጥ አድራሻ: @nolawii
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5.52K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ቻናል ኦርቶዶክሳዊ መንፈሳዊ ትምህርቶች የሚተላለፉበት ነው። እግዚአብሔር አገልግሎቱን ያስፋ!
0911699907 ዲያቆን አሸናፊ መኮንን

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-30 18:23:01 ምክር ለሰሚው 28 – Telegraph
https://telegra.ph/%E1%88%9D%E1%8A%AD%E1%88%AD-%E1%88%88%E1%88%B0%E1%88%9A%E1%8B%8D-28-08-30
363 views15:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 18:01:52 ምክር ለሰሚው /28

ወዳጄ ሆይ !

ቤትህ መሰወሪያህ ፣ ቤትህ ከድካም ማረፊያህ ፣ ቤትህ እንግዳ መቀበያህ ፣ ቤትህ ገመና ሸፋኝህ ናት ።

“ቤቴ ፣ ቤቴ ገመና ከታቼ ፣
የቤት ገመና መክተት ምንድነው ምሥጢሩ ?
ወደ ጓዳ ገብተው ዱቄትስ ቢቅሙ”

እንዲሉ ቤትህን ጽዱ ፣ ሰላማዊና ተናፋቂ አድርጋት ። ከሰዎች ትልቅ ቤት ያንተ ትንሽ ቤት ያንተ ናት ። ቤትህ እውነተኛ ማረፊያህና መደበቂያህ የምትሆነው ከሥራህ ስፍራ የራቀች ስትሆን ነው ። ሰው ቤቱ ሲታወክ ወደ ሥራ በመሄድ አየር ይቀይራል ። የሥራው ስፍራ ሲከፋ ወደ ቤቱ ሂዶ ያርፋል ። እንደ ገና ዳቦ ከላይና ከታች እሳት እንዳይነድብህ ቤትህን ልዩ ግዛትህ አድርጋት ።

ወዳጄ ሆይ !

ሰውን ልብስ ፣ ቤት ፣ ትዳር ፣ የንስሐ አባት ፣ ልጅ ፣ ወገኑ ይሸፍነዋል ። ዘመን ሲከፋ ልብስ ይቀደዳል ፣ ክብርም ይገፈፋል ። የተራቆቱለት ትዳርም በአደባባይ ያዋርዳል ። ንስሐ አባትም ምሥጢርን ያወጣል ። ልጅም ጠቋሚ ይሆናል ። ወገንም አሳልፎ ይሰጣል ። ሰባራ ዘመን በጸሎትና በእንባ ይታለፋልና ተግተህ ጸልይ ።

ወዳጄ ሆይ !

እግዚአብሔር ብዙ የማዳኛ መንገዶች አሉት ። በማጣትም ከመጥፋት ፣ በሕመምም ከሞት ፣ በእስራትም ከርኵሰት ይጠብቃል ። ለአንዳንዱ ማጣቱ ነፍሱን ማትረፊያ ፣ ለሌላው ሕመሙ ከሞት መዳኛ ፣ ለቀረው እስር ቤቱ ገዳም ይሆንለታል ። ሞት ወዳጆችህን ሲወስድብህ አንተንም እየታከከህ ነውና ኑሮህን በጥንቃቄ አድርግ ። ሞትህ ሞት እንዳይሆን የበደለህን ክሰህ ፣ የቀማኸውን መልሰህ በሰላም ዕረፍ ። በሰላም ማረፍ በምርቃት ሳይሆን በተግባር የሚገኝ ነው ።

ወዳጄ ሆይ !

የሁሉም ሰው ኑሮ ቢለያይም የነፍስ ዋጋ ግን እኩል ነው ። የነፍሳቸውን ሀብት እውቀትን ለሰጡህ መምህራን ፣ ነፍሳቸውን ለመሥዋዕትነት ለሚሰጡ የአገር ጠባቂዎች ክብር ይኑርህ ። ነጻ አእምሮ የንጹሕ ኑሮ ውጤት ነው ። መልእክትህን መስማት ከቻልህ እግዚአብሔር ዛሬም ይናገራል ። የተቀደሰ ኑሮ ዓለምን ያስንቃል ። ባሕርይህን ሳይሆን ጠባይህን ለውጥ ። ጾታህን መለወጥ አትችልም ፣ መጥፎ ጠባይህን ግን መለወጥ ትችላለህ ። የሥጋት ዘመን ሲመጣ እንቅልፍ እንዳበዛህ ምልክት ነው ።

ወዳጄ ሆይ !

ወዳንተ የመጣው ወንጌል በቀላሉ ሳይሆን በዋጋ ነው ። ወዳንተ የመጡ ወዳጆችም ብዙ መሥዋዕትነት ከፍለዋል ። ለዛሬ ማንነትህ ማንነታቸውን ያጡ አሉ ። አገር እንዲኖርህ አፈር የሆኑልህ አያሌዎች ናቸው ።

ወዳጄ ሆይ !

ቤተሰብ ሳለህ ሌጣ ፣ ሀብት ሳለህ ድሀ ፣ ወገን ሳለህ ብቸኛ ፣ ነጻነት ሳለህ ባሪያ ፣ አልጋ ሳለህ እንቅልፍ አልባ የሚያደርግህ ሰላም ማጣት ነውና ለሰላም ዋጋ ክፈል ። ስለ ጤናህ ለማመስገን እስክትታመም አትጠብቅ ።

ምክር ለሰሚው 28
ዲያቆን አሸናፊ መኰንን
ነሐሴ 24 ቀን 2014 ዓ.ም.
401 viewsedited  15:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 08:09:03 የታመቀ ስሜት /2

የታመቀ ስሜት መነሻዎች

1- የአስተዳደግ ሁኔታ

እናትን ወይም አባትን አሊያም ሙሉ ወላጅን በማጣት ያደጉ ልጆች የታመቀ ስሜት አላቸው ። ዕለት ዕለት ይህን ይመስሉ ይሆን ? እያሉ የወላጆቻቸውን ሥዕል ሲስሉ ያለማቋረጥ በውስጣቸው ያወራሉ ። ያንን ስሜት ገልጦ መናገር አሳዳጊዎቻቸውን የሚያስቀይም ስለሚመስላቸው ዝም ይላሉ ። በአገራችን ያለ አስተዳደግ መናገርን እንደ ብልግና የሚቆጥር በመሆኑ እንደ ፍግ እሳት ውስጥ ውስጡን እየነደድን እንድናልቅ አድርጎናል ። የአገራችን አስተዳደርም መናገርን የሚፈቅደው ሲሰክሩና ሲያብዱ ብቻ በመሆኑ የታመቀ ስሜት የእኛ መገለጫ ሁኗል ። ማኅበራዊ ሚዲያዎች ሲመጡ ነገራችን ዕርቃኑን የወጣው ተደብቀን ማውራት ስለቻልን ነው ። ይህ ሁሉ ገመና ለምን አደባባይ ተሰጣ ? ስንል የታመቀ ስሜት በተገቢው መንገድ ካልተነፈሰ የሚያጥለቀልቅ ጎርፍ ስላለው ነው ።

2- ያልወጣ ኀዘን

ወዳጆችን በሞት በማጣት የሚመጡ ኀዘኖች አሉ ። አንዳንድ ሰዎች አታልቅሱ ተብለው በመከልከላቸው ፣ ሌሎች ሃይማኖተኛ ሰው አያለቅስም ብለው በማሰባቸው ፣ የቀሩት ዘመናዊነት መስሏው በጥቁር ቲሸርትና ኮፊያ ልቅሶውን እንደ በዓል በማሳለፋቸው ውስጣቸው ኀዘን ይሰነቀራል ። ከሰው ጋር ማልቀስ ኀዘንን ያወጣል ። ከሰው ጋር ጠንካራ መስለው ሰው ሲሄድ ብቻቸውን የታመቀ ስሜት ውስጥ የሚገቡ ብዙዎች ናቸው ። በአገራችን ያለው የተለያየ የልቅሶ ባሕል ኀዘንን የሚያወጣ ነው ። ኀዘን ካልወጣ ጭንቀት እየሆነ ይመጣል ።

3- ጉዳት

ሰው ሁኖ በሰው ያልተጎዳ ሰው ማግኘት ከባድ ነው ። ከቅርብ ዘመናት ወዲህ በአገራችን መጎዳዳት የዕለት ሥራ ሁኗል ። የእኔ ህልውና ያለው በእገሌ መጥፋት ውስጥ ነው በሚል ሰይጣናዊ አስተሳሰብ ውስጥ የገባን ይመስላል ። በሰዎች የተጎዱ ሁሉን ሰው በመሸሻቸው የታመቀ ስሜት ውስጥ ይገባሉ ።

4- ብቻዬን ነኝ ብሎ ማሰብ

የሚሰማኝ ስሜት ፣ የሚሰማኝ እኔን ብቻ ነው ብሎ ማሰብ የታመቀ ስሜት ይወልዳል ። እንደ እኔ የሚሰማው ግን እልፍ ነው ። እንኳን አንድ ዓይነት መከራና መረጃ ባለበት ዘመን የሚኖሩ ይቅርና የዛሬ ሦስት ሺህ ዓመት በፊት የነበረው ሰው ከእኔ ጋር ተመሳሳይ ስሜት አለው ። ያ ባይሆን አንድ እውነት የዘመናት ፈዋሽ አይሆንም ነበር ።

5- ምሥጢር ሲባክን

አምነን የነገርነውን ምሥጢራችንን ሸቀጥ አድርጎ በአደባባይ ሲቸረችረው ፣ ይቅርታችን እንደ ውርደት ሲቆጠርብን የታመቀ ስሜት ውስጥ እንገባለን ። የታመቀ ስሜት ጨካኝ ፣ መራራ ፣ ኀዘነተኛ ፣ ብስጩ ፣ ተበቃይ ፣ ተጠራጣሪ ያደርጋል ። ከታመቀ ስሜት ለመዳን የሚሆነው ነገር ሲሆን የነበረ መሆኑን ማሰብ ይገባል ። አዲስ ሰው እንጂ አዲስ መከራ የለም ። በይቅርታ ያለፈውን ዘመን ፋይል መዝጋት ፣ ለሚመጣው መጠንቀቅ መፍትሔ ነው ። ከሁሉ በላይ ቀጥሎ ያሉት ሁለት ነገሮች አስፈላጊ ናቸው ። የመጀመሪያው እንደ እኛ የሚሰማውን ሰው ማግኘት ሲሆን ሁለተኛው በሕይወት ትግላችን ውስጥ አልፎ ድልን ያስቀመጠልንን ክርስቶስ ጌታችንን ማሰብ ነው ።

አቤቱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ፍጽምትና ጽንዕት በምትሆን ባንተ ሰላም አስበን !

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

ዲያቆን አሸናፊ መኰንን
ነሐሴ 23 ቀን 2014 ዓ.ም.
765 viewsedited  05:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 11:41:37 2014-12-01 ለአገሩም እዘኑለት

በ#ዲያቆን #አሸናፊ #መኮንን የተዘጋጀ ስብከት

አሁን በቴሌግራም ቻናል ይለቀቃል ። ይከታተሉ

የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ትምህርቶችና ስብከቶች ለመከታተል ከሥር የተቀመጡትን ገጾች ይመልከቱ፡-

https://t.me/Nolawii

https://t.me/nolawisebketoch

https://www.facebook.co m/ashenafi.mekonnen.357





www.ashenafimekonen.com
874 views08:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 11:39:41 ለአገሩም እዘንለት

ዲያቆን አሸናፊ መኮንን
820 viewsedited  08:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 11:47:15 የታመቀ ስሜት – Telegraph
https://telegra.ph/የታመቀ-ስሜት-08-27
1.0K views08:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 11:37:34 የታመቀ ስሜት

ልክ እንደ ተወጠረ ቍስል ፣ እንዳልተበጣ እብጠት ፣ የቆሸሸው ነገር እንዳልፈሰሰ ውጥረት ፣ መራመድ እንደሚከለክል ንፍፊት የታመቀ ስሜትም እንዲሁ ነው ። እየተራመዱ ድንገት ጉዞ እንደሚያስቆም ፣ ሰላም እየተወራ በመሐል አስጩኾ እንደሚያስደነግጥ እባጭ የታመቀ ስሜትም እንዲሁ የሕይወትን ጉዞ ይገታል ። የጀመሩትን ነገር ላለመጨረስ ምክንያት ይሆናል ። ራስን በትክክለኛነት ስሜት እየሞላ ሰው ሁሉ ጥፋተኛ ነው ያሰኛል ። በልብ ኀዘንን ፣ በዓይን እንባን ይሞላል ። ለማልቀስ ሰዋራ ቦታን ይፈልጋል ። የታመቀ ስሜት ይወጥራል ። ለመቆም ለመቀመጥ ፣ ለመኖር ለመሞትም መንታ አሳብ ላይ ያውላል ። የታመቀ ስሜት ሕመም አለው ። ፍቅርም ሆነ ጥላቻም ሲታመቅ ሁለቱም እኩል ሕመም አለው ። ጉዳትም ሆነ እልልታ ሲታፈን ሁለቱም ጭንቀት ያመጣል ። ጸሎትና ምስጋና ለልቅሶና ለእልልታ ዘመን የተዘጋጁ ማስተንፈሻዎች ናቸው ። ኀዘንም ደስታም ሁለቱም አጋር ፣ ተባባሪ-ወዳጅ ይሻሉ ። የታመቀ ስሜት እብጠቱ ለሰው ባይታይም ለባለቤቱ ግን የተራራ ያህል ይሰማዋል ። ውስጡን የመረዘው ፣ ሊወገድ ሲገባው አብሮት ያለው ክፉ ስሜት የነፍስ ሲቃ ውስጥ ይከተዋል ። ማንም በሌለበት ከራሱ ጋር እንዲያወራ ያደርገዋል ።

በክፉ አስተዳደግ ፣ በባሕል ተጽእኖ ፣ ድንበሩን አልፎ ሰውን በሚያጠቃ ማኅበረሰብ መካከል ማሳለፍ ፣ በአጉል የሕይወት ምርጫ ፣ ማንም ሰው ያለሁበትን ሁኔታ ሊፈርድ እንጂ ሊያውቅልኝ አይችልም የሚል አስተሳሰብ የታመቀ ስሜት ይመጣል ። የታመቀ ስሜት ከልጅነት እስከ ወጣትነት ፣ ከወጣትነት እስከ ሽምግልና እንደ-ታፈነ ሊኖር ይችላል ። ዕድሜውን የሚያሳጥረው የዓለምን እውነታ መረዳት ነው ። የታመቀ ስሜት የምንወደውን ነገር እያሰብን ፣ ከማንወደው ጋር እንድንኖር የሚያደርግ ነው ። ለምሳሌ፡- በታመቀው ስሜት ፍቅራቸው ከእገሌ ጋር ነው ። አሁን ግን በትዳር የሚኖሩት ያንን ሰው እያሰቡ ከሌላ ሰው ጋር ነው ። አንዳንዴ ከልባችን ሳንሆን መንገዱን በትክክል እንሻገራለን ። ባልነቃ አእምሮ ተግባራችንን እናከናውናለን ። በዚያ በታመቀ ስሜት ጡዘት ውስጥ ሁነው ሌላ ኑሮ የሚመሠርቱ ፣ በአሳብ ከሌላ ጋር በተግባር ደግሞ ከሌላ ጋር የሚኖሩ አሉ ።

የታመቀ ስሜት እያመሳሰለ መኖር ይወዳል ። የሚወደውን ሰው በሞትና በሌላም ነገር ስላጣ ያንን ወዳጅ የሚመስል ሰው ሲያገኝ ያንን ሰው በነጻ ይወደዋል ። የሄደው ሰው የጎዳው ቢሆን እንኳ ለዚያ ሰው የነበረውን የቀደመ ፍቅር እያሰበ ሌላ ሞክሼውን ሲያገኝ ይወደዋል ። ልጄን ይመስላል ተብለው በነጻ የሚወደዱ ሰዎች እንዳሉ ማለት ነው ።

ካለ መናገርና የሚመስልን ሰው ካለ ማግኘት የተነሣ የታመቀ ስሜት ዕድሜው እየረዘመ ይመጣል ። ለመንፈሳዊ አባት ወይም ለሥነ ልቡና አማካሪ በተገቢው መንገድ መተንፈስ ከውስጥ የነበረው አዋኪ ነገር የሚወጣበት መንገድ ነው ። ያንን ለማድረግ ያልተመቸው ደግሞ በጸሎትና በእንባ በእግዚአብሔር ፊት መናዘዝና ማልቀስ ትልቅ መፍትሔ ነው ። ከሁሉ በላይ በዚያ ስሜት ውስጥ የሚያልፍን ሰው ማግኘት ልብን ይፈውሳል ። ስሜቴን የሚረዳልኝ ሰው አገኘሁ ማለት ነፍስን ከሞት መንገድ ይመልሳል ። ጌታችን ከኃጢአት በቀር የእኛን የሕይወት ትግል በፈቃዱ የተቀበለው ፣ የሰው ልብ “እንደ እኔ የተፈተነ ነው” በማለት የስሜት አጋሩን በማግኘት ፈውስ ስለሚያገኝም ነው ። እርሱ ስሜታችንንም ሊያድን ወደ ምድር መጥቷል ። የከበረው ሐዋርያ፡- “ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እንደ እኛ የተፈተነ ነው እንጂ፥ በድካማችን ሊራራልን የማይችል ሊቀ ካህናት የለንም” ብሏል ። ዕብ. 4፡15።

ችግራችንን እንዲያርቅ እንለምነዋለን እንጂ ችግራችን እንዲገባው አናስረዳውም ። እርሱ ሁሉንም ያውቀዋል ። የታመቀ ስሜት ውስጥ የሚያልፉ ሰዎች የሚፈርድባቸውን ፣ የሚያጣጥላቸውን ሰው በፍጹም አይፈልጉም ። እጸልይልሃለሁ የሚላቸውን ሳይሆን የሚያዳምጣቸውንና በእግር ጫማቸው ውስጥ እግሩን ከትቶ የሚረዳቸው ሰው ይፈልጋሉ ። የታመቀ ስሜት ያላቸው ሰዎች ከትዳር አጋራቸው ፣ ከቅርብ ዘመዳቸው ፣ ከወላጆቻቸው ይልቅ ያሉበትን ሁኔታ ያወቀላቸውን መንገደኛ በጣም ሊወዱና እንደ ንስሐ አባታቸው ሊያዩት ይችላሉ ። የታመቀ ስሜት የተለያዩ መነሻዎች አሉት ።

ይቀጥላል

ዲያቆን አሸናፊ መኰንን
ነሐሴ 21 ቀን 2014 ዓ.ም.
1.0K views08:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 07:14:53
ኢየሱስ ናዝራዊ
በዲያቆን አሸናፊ መኮንን
ተራኪ ኤፍሬም ዘፈለገ ግዮን
1.1K views04:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 11:38:17 ኢየሱስ ናዝራዊ – Telegraph
https://telegra.ph/ኢየሱስ-ናዝራዊ-08-25
1.2K views08:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 11:31:14 ኢየሱስ ናዝራዊ

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአብሮ አደጎቹና ዘመዶቹ ተራ ሕልም ያለው ተደርጎ ይታያል ። ፖለቲከኞች ለወንበራቸው የሚያሰጋ የዙፋን አደጋ አድርገው ቆጥረውታል ። የሃይማኖት አባቶችም በትክክል አገልግለው የሚያገኙትን እንጀራ በግብዝነት ተውኔት ከሕዝቡ ለማግኘት ፈልገዋል ፣ በዚህም ኢየሱስን የጥቅማቸው ተጋፊ ብለው በመፈረጅ ከቅናታቸው ጥልቀት የተነሣ ለሞት ከጅለውታል ። ደቀ መዛሙርቱም የተጨቆነ ኑሮ መኖር ሰልችቷቸው ነበርና የዳዊትን መንግሥት አስመላሽ አድርገው ገምተውታል ። ባለጠጎችም የሀብት ተቀናቃኝና የምቾት እንቅፋት ብለው ሰይመውታል ። ማኅበረሰቡም ሰው የማይመርጥ ዘማዊና ቀራጭ ወዳድ አድርጎ ሥሎታል ። ኢየሱስ ጌታችን ለብዙዎች ጥያቄ ላመኑበት ግን መልስ ነው ።

ዲያቆን አሸናፊ መኮንን
ነሐሴ 19 ቀን 2014 ዓ.ም.
1.1K viewsedited  08:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ