Get Mystery Box with random crypto!

ከዚህ በፊት የቅዱስ ጊዎርጊስ ቢራ መወገዝ እንደሚገባ ፅፈንላቹ ነበር። አሁን ደሞ ቅዱስ ዮሃንስ ቢ | ኖህ ኢትዮጵያ

ከዚህ በፊት የቅዱስ ጊዎርጊስ ቢራ መወገዝ እንደሚገባ ፅፈንላቹ ነበር። አሁን ደሞ ቅዱስ ዮሃንስ ቢራን ይዘው መጥተዋል። በአሜሪካ አንድ የሀበሻ ሬስቶራንት ውስጥ ለገበያ የቀረበው ይህ ቢራ በቀጥታ የቅዱስ ዮሃንስን በረከት ከሀገራችን ሊያሳጣ የሚችልና ለመቅሰፍትም የሚያደርስ ነው።

የሰማዕታት ስዕል በኦርቶዶክስ ሀይማኖት ትልቅ ትልቅ ስፍራ ያለው ነገር ነው። እንኳን ቢራ ላይ ሊታተምና በየመንገዱ ሊጣል ቀርቶ ትንሽ የቆሸሸ ስፍራም አይቀመጥም። እጅግ ከባድ የሆኑ ነገሮችን እያቀለልን በማለፋችን ነው አሁን ለደረስንበት ውድቀት የደረሰነው። ውድቀታችንን ብቻ ከማየት ባለፈ የውድቀታችንን ምንጮች ፈልገን ማድረቅ ስንችል ነው ከችግሮቻችን ወጥተን ወደ ቀደምት ልዕልናችን የምንመለሰው።

ለሀገራችን ችግሮቻችን አንዱ ምንጭ የኢትዮጵያን ባለውለታ የሰማዕቱ ቅዱስ ጊዎርጊስን ስዕለ አድኖ በዚህ ደረጃ አርክሰን ከቆሻሻ ጋር መጣላችን ነው። ያለፈው ትውልድ የሰራውን ስህተቶች አዲሱ ትውልድ በንቃት እያረመ ካልሄደ በስተቀር መቀመቅ ነው ተያይዘን የምኖርደው።

ይህን ጽሁፍ ያነበበ ለነፍሱ ይወስን!

ቢያንስ እኛ ቢራውን ባለመጠቀምና ሌሎችን በማንቃት ግዴታችንን እንወጣ!