Get Mystery Box with random crypto!

♥̷_̷የ̷ፍ̷ቅ̷ር̷_̷ግ̷ጥ̷ም̷♥̷

የቴሌግራም ቻናል አርማ nizretm — ♥̷_̷የ̷ፍ̷ቅ̷ር̷_̷ግ̷ጥ̷ም̷♥̷
የቴሌግራም ቻናል አርማ nizretm — ♥̷_̷የ̷ፍ̷ቅ̷ር̷_̷ግ̷ጥ̷ም̷♥̷
የሰርጥ አድራሻ: @nizretm
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 14.20K
የሰርጥ መግለጫ

መሳጭ መሳጭ ግጥሞች
አቅራቢ @Muba88

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2021-09-17 22:51:20 .......#የዘመኑ_ሰዎች

በአርቲፊሻል ውበት ግራ እየተጋቡ
በልብ ሳይገናኙ ባሳብ ሳይግባቡ
በቃላት ጋጋታ ውስጡን ሳያጣጥም
በአፍ ላይ ፍቅር ብቻ ከንፈር የሚገጥም
በስሜት ሚነዳ እልፍ ሰው ሲበዛ
ከሚጋባው ይልቅ የሚፋታው በዛ።

╔═══❖• •❖═══╗
@Nizretm
╚═══❖• •❖═══╝

4 any comment
@Muba88
❥❥________⚘_______❥❥
29.6K viewsedited  19:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-03-03 16:53:20 ምኖረው ለነፍሷ ምትገለኝ ለነፍሱ፣
ሚታገላት ልቤ ሚያሸንፋት ኪሱ፣
የምትከሰኝ እሷ የሚዳኘን እሱ፣
አለመገጣጠም ግጥም ነው በራሱ፡፡

በላይ በቀለ ወያ

Share & join @Nizretm
51.8K views13:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-27 16:43:24 ............አየሽ ?

ይሄንን ምኞት ነው
ይሄንን እሳት ነው
የፍቅርሽ ማዕበል
ድራሹን ያጠፋው
በፍቅርሽ ወተት ነው
እንስሳነት ከስሞ
ሠው መሆን የፋፋው
ይሄን ጉድ ምኞት ነው
ፍቅርሽ ያከሸፈው
ሚሊዮን ብልግና
እልፍ መሻት ገሎ
ውስጤ የገዘፈው
........አየሽ......?

አሌክስ አብርሀም

@Nizretm
50.3K views13:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-20 17:45:30 ስስምሽ ስላየሁ
ትላንትና በህልሜ
ዛሬን ቶሎ ተኛሁ
ልስምሽ ደግሜ
ታድያ ምን ያረጋል
የህልሜ ደራሲ
አትታደል ቢለኝ
ህልሜን ገለባብጦ
ሲስሙሽ አሳየኝ!!!

በረከት በላይነህ

@Nizretm
52.4K viewsedited  14:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-30 15:28:19 #ኤልዳን_ለኢትዮጵያ

{የፍቅር ጠንቋይ}
°°°°°°°°°°°°°°°°°

(አፍቃሪና ጠንቋይ ለራሱ አያውቅም)

እኔ ማለት
ስላንች እያሰብኩ መኖርን የምመኝ
ለራሴ የማላውቅ የፍቅር ጠንቋይ ነኝ
:
ምግብ ቀርቦ
ለመመገብ እጄን ብዘረጋም
ያንችን መጉረስ
ሳላረጋግጥ ወደ አፌ አላስጠጋም
አንች ካልበላሽ መብላት አያምረኝም
ፆሜን እንኳ ብውል ምንም ቅር አይለኝም
በአንች መብላትነው ልቤ የሚረካ
በአንች መጥገብ ነው ሆዴ የሚፈካ
እኔ ለእኔ አልልም
በአንች መኖር ነው ህይወቴ ሚሳካ
በቃ እኔ ማለት
ካለመብላቴ ይልቅ መብላትሽ ሚያኖረኝ
ለራሴ የማላውቅ የፍቅር ጠንቋይ ነኝ
:
አልጋ ላይ ተኝቼ
ለማንቀላፋት እጅግ ብመኝም
ያንችን መተኛት
ሳላረጋግጥ እንቅልፍ አይወስደኝም
አንች ካልተኛሽ እንቅልፍ ለምኔ
ሳልተኛ ቢነጋም አይደንቀኝም እኔ
አንች ስትተኚ ነው መንፈሴ የሚያርፈው
አንች ስትተኚ ነው ህይወቴ ሚታደሰው
እኔ ለእኔ አልልም
በአንች ህልም ነው መኖር ምፈልገው
በቃ እኔ ማለት
በመተኛትሽ ውስጥ እንቅልፌን የማገኝ
ራሴን ማላስቀድም የፍቅር ጠንቋይ ነኝ
:
ከፊትሽ ቆሜ
ፍቅርን… ከገፅሽ ብቃኝም
ያንችን ድምፅ
ካልሰማሁ የኖርኩ አይመስለኝም
አንችን ሳልሰማ ከምል ኑሪያለሁ
ጆሮ ባይኖረኝ በእጥፍ እመርጣለሁ
አንች ስትናገሪ ነው ምትለመልም ነፍሴ
አንች ስትናገሪ ነው ሚሰማኝ ውዳሴ
እኔ ለእኔ አልልም
በአንች ቃል እኖራለሁ ቢቆረጥም ምላሴ
በቃ እኔ ማለት
የፍቅር ቃላትሽ ህይወት የሚሰጠኝ
መናገር ማልሻ የፍቅር ጠንቋይ ነኝ

ዳንኤል ከበደ


"SHARE" @Nizretm
50.5K views12:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-29 15:12:25 ____ የምዕዳን ጀምበር ____
.......
አንቺ ሁኚ ÷ ደማም ፣
እኔ ልሁን÷ አመዳም ፣
በፍቅርሽ ነው እንጂ ÷
በቃልሽ አልደማም ።
...............

@Muba88
@Nizretm
45.3K viewsedited  12:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-27 16:49:22 እኔ ወድሻለሁ

በካፊያ ዝናብ ተኝቶ እንደማለም፣
በተስኪያን ስሞ ደሞ እንደመሳለም፣

እኔ ወድሻለሁ
ተጠምቶ እንደመርካት ተርቦ እንደመጥገብ፣
ነጠላ አጣፍቶ
ጧፍ በእጅ ይዞ የመዘመር አጀብ፣

በዚህ ሁሉ መውደድ እኔ ስውተረተር፣
ያንቺ ጠብ አይልም
በአንደበት ብቻ ሁሌ እንደምሰማው ፖለቲካ ቀመር፣

ቢሆንም ግን ዳሩ እኔ ወድሻለሁ፣
እንዳገሬ ገንዘብ
ትቀየሪ እንደሆን እጠብቅሻለሁ፡፡

@Muba88

╔═══❖• •❖═══╗
@Nizretm
╚═══❖• •❖═══╝
❥❥ ⚘ ❥❥
45.5K views13:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-17 16:51:43 ​​ውሸት ነው

ፍቅሬ እንዳንዴ አመሌን የማጣው
በንፁ ጨዋታሽ የምነጫነጨው
በጥርስሽ ብርሀን ፊታን የማጠቁረው
ምነው ሆዴ ስትይ ብወድሽ የምለው
እውነት እንዳይመስልሽ አይደለም ውሸት ነው

ደግሞም አንዳንድ ቀን
እኔ አንቺ አብረን ሆነን
የምለይሽ በሰመመን።
ከሰመመን መልሰሽኝ
ምንው ሆዴ ስትይኝ
ሀሳብ የከተተኝ
ፍቅርሽ ነው ያልኩትኝ
እውነት ይሁን ውሸት እኔንም አልገባኝ
ሌላም በሌላ ቀን አዱኛ ስተርፈን
አድባር ሲቀርበን ፍቅር በልተን
ፍቅር ሰርተን እንዳበቃን
ታፈቅረኛለህ ስትይኝ ከእኔ በላይ ያልኩትኝ
በእውኔ አይሆንም በህልሜ መሰለኝ
ደግሞም ሌላ ጊዜ
ከሀገር ምድር ተገልለን
እኔ ባንቺ አንቺ በእኔ ተጠልለን
ምሽት ደርሶ ሲለያየን
ጀንበር ዘቀዘቀችች መለየት ሊሆን ነው
ነግቶ እስከማይሽ ናፍቆት ብዙ ነው
ብዬ ያወራሁሽ እኔ ልሙት ብዬሽ
እውነት እውነት ስልሽ
እውነት እንዳይመስልሽ
ውሸት ነው ልንገርሽ
በፈጠረሽ አምላክ ይሄን ሁሉ እውነት
አሁን የነገርኩሽ እራሱ ውሸቱን እውነት
እንዳይመስልሽ እውነት ግን አለሜ
ውሸት ይመስልሻል አንቺን ባላፈቅር
ይሄ ሁሉ ይወራል ውሸቴን ነው ተብሎስ
ከወደዱት ሌላ ለጠላት ይፃፋል
እውነቱን ልንገርሽ ሊፃፍም ይችላል
እውነት ነው ብሎ ማታለል ይቀላል
እኔ ግን ልንገርሽ
እውነት ነው ስልሽ
እውነት እንዳይመስልሽ
ውሸት እንዳይመስልሽ....

➲ከኤፍሬም ስዩም
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን

✦ የምንም ግዜ ተወዳጅ የሆነው
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
አዘጋጅ፦ @Nizretm

@Muba88
45.1K views13:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-08 06:45:54 #ፍቅሬን_ተረጀልኝ

ልቤ ላይ ያሰርኩት የዝምታ ማተብ
በሀቅ የታሰረ የእምነቴ ገደብ
ፈሪ ነህ ተብየ በሀሰት ስሰደብ
በቃላቶች ጅረት እውነቴ ሲታጠብ
:
አደዩ ልብሽን በቃላት ባልቀስመው
ጠላት ምቀኛሽን በነገር ባልነድፈው
ቃሌ ባያረካሽ ውስጥሽን ባይነካው
ዝምታየ ጥልቅ ነው ማንም ያተረዳው
:
የቃላት ጥርቅም የሀገሬ ስብጥር
የዓንቀፅ ጋጋታ የድርሰቶች ክምር
ፍቅርን ላያፀና በቃል ለሚሰበር
ዝምታ ሀቅ ነው ምንም የማይበገር
:
ልብሽን ባገኘው በቃላት ደልየ
የሞተ አስነስቼ ያለውን ገድየ
ልብሽ ላይ ከምሰፍር ውስጤን አታልየ
መኖር ይሻለኛል እራሴን በድየ
:
ግን ልብሽ ጆሮ ሁኖ ውስጤን አድምጠሽው
የዝምታ ገዳሜን ቆርበሽ ጎብኝተሽው
የልቤ ኪዳኑን በልብሽ ከትበሽው
ፍቅሬ ላይ ኮብልይ ሀቄን ተረድተሽው






@Muba88


"SHARE" @Nizretm
ይሄም ላንቺ ነዉ የተፃፈዉ #s
45.9K viewsedited  03:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-07 16:49:55 *ሁለት ዓለም*



አንቺን እስካወኩሽ እስከዛች ቅፅበት፣
ብቻዬን ለመኖር ነበረ ያሰብኩት፣

ፍቅርን አላለምድም ከእንግዲህ ለልቤ፣
ሰው አላምንም ከቶ ሞት ቢሆን ቀለቤ፣

ብዬ ወስኛለሁ፣
እካገኝሽ ድርስ እንዲ ነኝ አውቃለሁ፣

ያለፍኩት ስንክሳር፣
ሰው አምኖ መጎዳት
ቁስሉን ለማከም ብቻዬን ስጣጣር፣
ላላፈቅር ማልኩኝ ድጋሜ ብፈጠር፣

ብታዪ ያን ሰሞን፣
ለኔም እግዳ ነው እንዴት እንደምሆን፣

በደል እየመጣ የእንባ ቋቴን ወገቶ፣
ክህደት እያመመኝ መራር እውነት ግቶ፣
ነበር ያገኘሽኝ፣
ከፍቅር ስጣላ ፍቅር ያሳየሽኝ፣

ታዲያ ምን ያደርጋል፣
የኔ ልብ ሲድን ያንቺ ያገረሻል፣

ለካስ አንቺም ኖረሽ የፍቅር ታማሚ፣
ድንገት ተገጣጠምን
ፍቅርን ስጀምረው አንቺ ስትፈፅሚ፡፡

@Muba88

share @Nizretm
43.1K viewsedited  13:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ