Get Mystery Box with random crypto!

#ለአንች# #ይብላኝልሽ# : ለአንች ይብላኝ እንጅ እኔን ለገፋሽኝ ከልቤ ስወድሽ በአፍ ቃል ለወደድ | ♥̷_̷የ̷ፍ̷ቅ̷ር̷_̷ግ̷ጥ̷ም̷♥̷

#ለአንች# #ይብላኝልሽ#
:
ለአንች ይብላኝ እንጅ እኔን ለገፋሽኝ
ከልቤ ስወድሽ በአፍ ቃል ለወደድሽኝ
በሹፈት አንደበት ማሬ ውድ ላልሽኝ
የአፍሽን መዝጊያ ቁልፍ የልቤ ነው በለሽ
እውነት በሚመስሉ ቃላቶች ሸንግለሽ
ከልብሽ በለለ በተፈጥሮ ቆዳ በከንፈርሽ ስመሽ
ልብሽን ከሌላ አካል ከእኔ ትተሽ






ግን ግድ የለም ይነጋል መቸም መሽቶ አይቀር
ጨለማን ያጠቃል እውነትና ፍቅር
አይ ያንች ነገር
ያን ሁሉ ማንነት ጨርሽ ስሰጥሽ
ማነም ከለለበት ልብ ከፍቸ ሳስገባሽ
አንች የኔ እናቴ የሂወት ምስጢሬ ብየ በነገርኩሽ
እያመመኝ እንኳ ያንን ነገር ሁሉ ለአንች በሆንኩልሽ?





ፍቅር ማለትኮ ነው የእግዜር ስጦታ
ፍ-ፁም እውነታንን በጀርባው ያዘለ
ቅ-ንነትን መርህ አርጎ የታደለ
ር-ዝራዥ ውሸት ከውስጡ የለለ
ግን አንች
የተስፋ መንገዴን በሬንን ዘግተሽ
አይዞህ ባይ ከለለው ከጫካው ጥለሽ
ምን ባደርግሽ ይሆን እንዲህ የጨከንሽ???






ኝ?
መውደዴ ነው ስህተት ወይስ ልብ መስጠት
ነው ሁሌም ሰርክለት ስምሽንን መጥራት?
ነው ወይስ ደግሞ መክፈሌ ነው መስዋት??
በይ እንጅ መልሽ

በቃ ይሄ ነው መልስሽ ያራቀሽ ምክንያት?
ለአንዴ ላትመለሽ ያራቀሽ እኔ ቤት?
ስትገርሚ
ትሰሚ ከሆነ ልንርሽ አንድ እውነት?
ሞልቶ አልተፈጠረም ማንኛውም ፍጥረት
ለምን እንዲህ አልከኝ ብለሽ ከጠየቅሽ
ሙሉ አድርጎ አንችን ከፈጠረሽ
ነገ ማሰብ ቀርቶ እሡን ትረሻለሽ
ሰለዚህ
ሰው ሁኖ ተፈጥር መች እንከን ይጠፋል
ድከመት ደግነትም አብሮት ይኖራል
ግን ከመራቅ ይልቅ ሌላ ከመፈለግ
አይቻልሽም ወይ እኔንን ሰው ማድረግ?
እረ ግን
እኔ በአንች አልፈርድም በቃ ትቸዋለሁ
ከላይ ከመግቢያየ ሁሉን ብየዋለሁ
ግድ የለም ይነጋል ነገን አየዋለሁ
ሰለንፁህ ፍቅርሽ አመሠግናለሁii


ገጣሚ ልጅ ፋሲል የጎንደር ልጅ
@Gebrieln19211227
መታሠቢያነቱ ለአንች ለ(H

SHARE AND JOIN @Nizretm

Any comment @Muba88