Get Mystery Box with random crypto!

​​​​​​​​​​​​▓▓▓▓▓▓▓ ግጥM ▓▓▓▓▓▓▓ ➲ ​​​​ኧረ የማን ልሁን | ♥̷_̷የ̷ፍ̷ቅ̷ር̷_̷ግ̷ጥ̷ም̷♥̷

​​​​​​​​​​​​▓▓▓▓▓▓▓ ግጥM ▓▓▓▓▓▓▓


➲ ​​​​ኧረ የማን ልሁን

ከለታት ባንድ ቀን እየኖርኩ እያለ
መጣልኝ ሠውየው ወደድኩሽ እያለ
ብዙ ቀንም ሳይቆይ ተመልሶ ደሞ
ጠላሁሽ ሊለኝ ነው? ልቤን አሳምሞ

ከለታት ሁለት ቀን እየኖርኩ እያለ
ሌላኛው መጣልኝ አፈቀርኩሽ አለ

ሁለቱን እያሰብኩ ብዙም ሳልቆይ ሳለሁ
ከለታት ሦስት ቀን እየኖርኩ እያለሁ
አንደኛው ተነስቶ አበድኩልሽ አለኝ
ኧረ አሁንስ በዙ የማን ልሁን አልኩኝ
ሁሉም ለኔ ለኔ ሲንገበገቡልኝ
የራሴ መሆንን እራሴ ተመኘሁኝ

ለመወሰን ከብዶኝ ባለሀብት ቦታ
አራተኛው መጣ በሀብቱ ሊረታ
ማን ሊሰማው ከቶ ሀብቱን ቢያስጎበኘኝ
እስኪ ይፈልገኛ እኔም ግን ስሆን ሞኝ

ለአምስተኛ እንኳን ቦታ አልሰጥም ብዬ
በውሀ ውስጥ አልዋኝ ሆኜ እንደዳክዬ
ወይ አልሰቀልም ሆኜ እንደ ፓፓዬ

ሀብታሙ ሀብቶቹን ደሀው ንፁህ ፍቅሩን እያወዳደሩ
በልቤ ዙፋን ውስጥ በፍቅር እንዲኖሩ
ዛሬ ከኔ ጋ ናት ዛሬ ከኔ ጋራ እየተፎካከሩ
እኔን ወደኋላ ትተውኝ በረሩ

ግን .............
ከሀብታሙ ብኖር ሀብቱ አማለለኝ
ግን ደሞ እንደገና ደሀው ፍቅሩ ያዘኝ

የሚወደኝን ሠው ገፍቼ ገፍቼ
የምወደውን ሠው ስከተል አብዝቼ
ኋላ እንዳይፀፅተኝ ሁሉንም አጥቼ

ሜሮን ገነነ


━━━━━━✦✗✦━━━━━━━


Share&join @Nizretm

➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢