Get Mystery Box with random crypto!

የመንግስት ሀይሎች በመርሐቤቴ ጥቃት እየፈፀሙ ነው ንሥር ብሮድካስት | NiSiR Int. Broadcasting Co. (Official Telegram Channel)

የመንግስት ሀይሎች በመርሐቤቴ ጥቃት እየፈፀሙ ነው

ንሥር ብሮድካስት
ሰኔ 5/2015

የመንግስት ታጣቂዎች በመርሀቤቴ ጥቃት እየፈፀሙ ሲሆን ትላንት ሰኔ 4 ቀን 20115 ዓ.ም በዓለም ከተማ የ2ኛ ደረጃ መምህር የሆነው ስለሺ ስዩምን የፋሽስቱ ኃይሎች በአደባባይ በዱላ እየደበደቡ ወስደው አስረውታል።

በሌላ በኩል ደግሞ የጤና ጥበቃ ጽ/ቤት የጥበቃ አባል የሆነው አቶ በነበሩ እና ስሙን ማወቅ ያልተቻለ ወጣት ሰክረው ሲያሽከረክሩ በነበሩ የአገዛዙ ወታደራዊ ሾፌሮች ተገጭተዋል ተብሏል።

ልዩ ስሙ ሰታቲት የሚባል የመኖሪያ መንደር ሰኔ 4 ቀን 2015 ዓ.ም ከምሽቱ 4:30 ሁለት ወጣቶች በአገዛዙ ወታደሮች በጥይት ተደብደበው ሆስፒታል ገብተዋል።

የከተማው የሚሊሻ ኦፕሬሽን መሪ የአገዛዙ ወታደሮች ከተማው ውስጥ ከመግባታቸው በፊት እኔ ፋኖ ነኝ ብሎ ተመሳስሎ ሲሰልሉ የነበረ ሲሆን የወታደሮቹን መግባት ተከትሎ ትክክለኛ ማንነታቸውን አደባባይ አውጥተው የሴቶችን ቦርሳ ሳይቀር እፈትሻለሁ በሚል ሌብነት መጀመራቸውን ጋዜጠኛ ሙሉጌታ አንበርብር መረጃውን አጋርቷል።

ወቅታዊ ፤ ትኩስ እና የተሟላ መረጃዎችን ለማግኘት
Youtube: https://www.youtube.com/@nisir/videos

FaceBook Page 1 :    https://www.facebook.com/Nisirbroadcast

FaceBook Page 2:  https://www.facebook.com/Nisirmereja      

Telegram:    https://t.me/nisirbroadcasting

Website: https://nisirbroadcasting.com

Twitter:   https://twitter.com/NISIRInternati1

Instagram:  https://www.instagram.com/nisirbroadcast/
ንሥር ብሮድካስትን በወዳጅነት ይከታተሉን።