Get Mystery Box with random crypto!

ከ፩ ዐማራ ፋኖ የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ ሰኔ 2/2015  ኢትዮጵያ የብዙ ብሔር ብሔረሰቦች ውብ | NiSiR Int. Broadcasting Co. (Official Telegram Channel)

ከ፩ ዐማራ ፋኖ የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ
ሰኔ 2/2015

 ኢትዮጵያ የብዙ ብሔር ብሔረሰቦች ውብ ባህላት እና የእምነት ብዝኻነት የነበራት ከመሆኗም በላይ ሁሉም ተቻችለው፣ ተፈቃቅደውና በፈርሃ አምላክ ተዋደው የሚኖርባት የነበረች መሆኗን ሁሉም በኩራት ሲተርከው የኖረ መሆኑ ይታወቃል።
ይሁን እንጂ ሃገራችን ኢትዮጵያ ስሪቷ ፀንታ የኖረችው በሁሉም ኢትዮጵያውያን ክቡር ተጋድሎና ሰማዕትነት መሆኑን ለማስታወስ ብዙ የውጪ ወረራዎችን ያከሸፉበት ብሎም አሳፍረውና አዋርደው የመለሷቸው ታሪካዊ ጠላቶቻችን ህያው ምስክሮቻችን ናቸው።

ታሪካዊ እና ሀገራዊ የውጪ ጠላቶቻችን በወረራና በጦርነት ያልተሳካላቸውን የማንበርከክ፣ ሀገራዊና ስነ ልቦናዊ ውቅራችንን ለመፈታተን የመረጡት መንገድ "የሀገሩን ሰርዶ በሀገሩ በሬ" የሚለውን ብሒል ሲሆን፦ በተለያዩ ጊዚያትም ሀገር  በቀል ባንዳዎችን በመመልመል፣ በመደገፍ፣ በማሰልጠን፣ ብሎም ለሀገራዊ በትረ ስልጣን በማብቃት የኖረውን እና ፅኑውን የሀገር ፍቅር ስሜቶቻችንን ሲፈታተኑ መቆየታቸው ማሳያው  ዘርፈ ብዙ ቢሆንም አሁናዊ የምንመለከታቸው ነባራዊ ሁኔታች ህያው ምስክራችን ናቸው! አስተርጋሚም እያሻውም::


ይባስ ብሎም በስመ መንግስት  የመንግስት ስም ያለው ስብስብ ከፕሪቶሪያው ስምምነት ማግስት ዐማራ ክልልን ህግና ስርዐት አልባ በማስመሰል፣ ክልሉንና መላው የዐማራ ህዝብን በማዳከም ሴራ ተቀኝቶ በጦርነት ; በማፈናቀል; በግድያ; በአፈና እና እስር የአማራን ህዝብና ክልል ላለፍት ዐመታት በፍዳና ሰቆቃ እንዲቀጥል አድርጋል::

በክልሉ ውስጥና ከክልሉ ውጪ ያሉ የንፁኻን ዜጎች በደል፣ ስደት መፈናቀል፣ የጅምላ ፍጅትና መንግስታዊ ሽብር በመፈጸም ላይ መሆኑ የአደባባይ ሚስጥር ቢሆንም ምንም ዓይነት የመገናኛ ብዙኻን ሽፋን እንዳያገኝ እያደረገ ያለበት ሁኔታ እብሪቱንና ማናለብኝነቱን ያስመሰከረበት ሁኔታን ታዝበናል:: ይባስ ብሎም ከሚያዚያ/ 2015 ዓ.ም ጀምሮ እየወሰደ ባለው በስመ 'ህግ ማስከበር' ስም ሀገሪቱ ያላትን ውስን የሰለጠነ የሠው ሃይል፣ ቁሳዊ ሃብት; ተቋማዊ መዋቅር እንድታጣ እያደረጋት ነው:: የነቁ እና ህዝብን የሚያነቁ አማራወችን አፍኖ በመሰወር፣ ኢ ሰብኣዊ ድርጊት በመፈፀም ትክክለኛውን የህዝብን ጥያቄዎችን ለማፈንና ዝም ለማስባል እየሰራ እንደሆነ በግልጽ ታይቷል። ይህ እብሪተኛ መንግስት ትግላችንን ለማፈንና ለማዳከም የወሰደው የሃይል እርምጃ እኛን ከማዳከም ይልቅ እያጠናከረን፤ የበተነን ሲመስለው ደግሞ በተሻለ አስተሳሰብ እያሰባሰበን እንደሆነ ወራት ያስቆጠረው ትግል ምስክራችን ነው:: የአማራ ትግል ደረጃውን በማሻሻል ህዝባዊ ከመደረጉም በላይ በንፁሓንና ሀገር ወዳድ ብሔር ብሔረሰቦችም ዘንድ ለምን እንዲሉ በማድረጉ የማዕከላዊ መንግስቱን ቀጣይነት ጥያቄ ውስጥ አስገብቶታል።

ከዚህም ጋር በተያያዘ 'መንግስት ነኝ' ባዩ የወንበዴዎች ስብስብ "ካፈርኩ አይመልሰኝ" በሚል የወራዶች ሀሳብ የሀይል ጥቃቱን በማጠናከር በንጹሓን ዜጎች፣ በእምነት ተቋማትና ምንም ዓይነት ዐላማ እና ተሳትፎ በሌላቸው የገዳማት ላይ እየፈጸመው ያለው እኩይና ዘግናኝ ተግባርን ከክልሉ ነዋሪዎችም ባሻገር በ'መንግስት' ይደግፉኛል በሚላቸው ስብስቦቹም ጭምር እየተወገዘ መሆኑን ታዝበናል።በታላቁ ገዳም ደብረ ኤልያስ እና አንዋረ መስጊድ ላይ ያደረሰው ጥቃት ማሳያ ነው ።

ስለሆነም፦
፩ኛ/ ውድ የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት; እንቁ የተቋሙ ወታደራዊ መኮንኖችና ኢትዮጵያዊ ስሜቱ ያላችሁ ሓላፊዎች አሁን ላይ ኢትዮጵያ የገጠማት ሁለንተናዊ ችግር መነሻው ፖለቲካዊ መሆኑን ታውቃላችሁ፤
የእናንተ ተቀዳሚው ተግባራችሁም ሀገርን ከውጪ ወራሪ መከላከልና የመላው ኢትዮጵያውያንን ሠላምና ደህንነትን ከማረጋገጥ በመለስ በወረዳና በጎጥ ደረጃ ከሚገኙ ወጣቶች ጋር ግብግብ ስትገጥሙ ላስተዋለ የትልቁን ሀገራዊ ተቋምነት ትዝብት ውስጥ ጥሎታል፤ አልፎ ተርፎም ታላቁን የሀገር መከላከያ ተቋሙን ተራ የፓርቲና የግለሰብ ፖለቲከኞች መጠቀሚያ አስመስሏችሗል። እናም እየተሰራባችሁ ያለውን ፖለቲካዊ ሸፍጥና ሴራን በውል በመረዳት ወደ ታላቁ እና ሀገራዊ ተልኳችሁ ዘንድ በማተኮር የጀመራችሁትን የመንደር ሚሊሻና የቀበሌ ፖሊስ ተግባራችሁን ለሚመለከታቸው ባለድርሻዎች በመተው ከታሪካዊ ስህተታችሁ እንድትታቀቡ እንጠይቃለን! በተጨማሪም ህዝብ ላይ ከመተኮስ ይልቅ ባለውለታ ህዝብን ከችግርና ወረራ በመታደግ ተግባራችሁ ላይ በማተኮር ከፍታችሁን አስጠብቁ።

፪ኛ/ በየአካባቢያችሁ የምትገኙ የፀጥታ መዋቅር አባላት በፖለቲካዊ ፍላጎት የተበላሸውን ዘመቻ በመቀልበስና በመጠቆም፤ በመምራት፤ በተኩስ በመግጠም በጋራ የምንከፍለውን አላስፈላጊ ውድሙትን በማቆም ታሪካዊ ግዴታችሁን እንድትወጡ እያሳወቅን ከዚህ እኩይና ፀረ ግብ ከሆነው ድርጊታችሁ እማትቆጠቡ ከሆነ ግን ለሚደርስባችሁ ማንኛውም ዓይነት ማህበራዊም ይሁን ሠዋዊ ኪሳራ ሓላፊነቱን እንደምትወስዱ ልናሳስባችሁ እንወዳለን።

፫/ ወቅቱ አመቸን፤ ጊዜ ዘመመባቸው ብላችሁ ከፍ ሲልም እነሱ እስካሉ ድረስ የ'እኛ ህልውና' አደጋ ላይ እንወድቃለን በሚል ሰንካላ ፍርሃት የ'ፋኖ' አባላትን፣ አስተባባሪዎችን፣ ባለ ሀብቶችን እና ማህበረሰብ አንቂዎችን በስመ "ህግ ማስከበር" ስም እያደረሳችሁብን  ያለውን ማሳደድ በአፋጣኝ አቁሙ፤ አስቁሙም!
ለመከላከያ ባልተገባ መልኩ ስምሪት ከመስጠት እንድትቆጠቡ ጥሪያችንን እያስተላለፍን፤ ከዚህ በሗላ ግን በሚደርስብን ማናቸውም ዓይነት  ጥቃትና በደል እዳውን እንደምታወራርዱት ልናረጋግጥላችሁ እንወዳለን።

፬ኛ/ ውድ የዐማራ ክልል ማህበረሰብና መላው ኢትዮጵያን አሁን ላይ እየደረሰብን ላለው መሳደድ፣ መገደል፣ መታሰር; ታፍኖ መሰወር እና እንደ ህዝብ መጥፋት የታወጀውን በማውገዝ ለገጠሙን ችግሮች በጋራ በመጋፈጥ እና ለአለም ማህበርሰብ በማሳወቅ ከጎናችን እንድትሰለፉ ጥሪያችንን እናቀረባለን ።

 ፭ ኛ / ታላቁ እስክንድር የመሰረተውን የአማራ ህዝባዊ ግንባር የምንቀበል እና በጋራ የምንታገል መሆኑን እየገለፅን ታላቁ መሪያችን ላይ የታቀደውን ሴራ በጋራ እንታገለዋለን ይህንንም የግብረሶደም መንግስት እናሰወግዛለን።

፮ ኛ አርበኛ ዘመነ ካሴ እንኳን ከማይገባህ ወህኒ ቤት በሰላም ወጣህ እያልን ወደፊት አንተን ይዘን የአማራን እና የኢትዮጲያን ጠላቶች እናሸንፋቸዋለን።

በመጨረሻም መላው የአማራ ወጣት ሁልህም በመክሊትህ ታግለህ እራስህን ነፃ ለማድረግ በሰፈርህ ባለው የፋኖ አደረጃጀት ተቀላቀል:: ይህ ካልሆነ በባረነት እንኳን የምትኖረባት ሃገር አትኖረህም ።



ድል ለአማራ ህዝብ
ድል ለኢትዮጲያ
ድል ለፋኖ
አንድነት ሃይል ነው !!!
ሠኔ/ 02/2015 ዓ . ም.