Get Mystery Box with random crypto!

'የፋኖ ጽንፈኛ የለም፤ የብልፅግና ካድሬ እንጅ' ብለሃል የተባለዉ መኮንን አየለ 'በሁከትና ብጥብጥ | NiSiR Int. Broadcasting Co. (Official Telegram Channel)

"የፋኖ ጽንፈኛ የለም፤ የብልፅግና ካድሬ እንጅ" ብለሃል የተባለዉ መኮንን አየለ "በሁከትና ብጥብጥ" ክስ ፍርድ ቤት ቀረበ

         ንሥር ብሮድካስት
        ግንቦት 9/2015

በአዲስ አበባ ከተማ አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 05 ልዩ ቦታዉ ገዳም ሰፈር ነዋሪ የሆነው እና ቀደም ሲል የመከላከያ ሠራዊት አባል የነበረዉ መኮንን አየለ "ፋኖ ጽንፈኛ አይደለም፤ የብልፅግና ካድሬ እንጅ" የሚል ንግግር አድርገሃል በሚል በሁከትና ብጥብጥ ክስ ተከሶ በአሁኑ ሰዓት በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በእስር ላይ ይገኛል።

መኮንን አየለ በአማራነቱ የግፉ እስረኛ  ሲሆን ፍርድ ቤት በ5 ሺህ ብር ዋስትና እንዲወጣ ውሳኔ ቢሰጥም፤ ፖሊስ "በሚያዚያ ወር 2015 ዓ.ም በአ.አ ከተማ አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 5 ልዩ ቦታው ገዳም ሰፈር እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በመንቀሳቀስ በአ.አ ከተማ ውስጥ ሁከትና ብጥብጥ ለማስነሳት በማሰብ "የፋኖ ጽንፈኛ የለም፤ የብልጽግና ካድሬ እንጂ" በማለት በድረ ገጽ የሚቀሰቅስ፣ መንግስት በአማራ ክልል ከልዩ ኃይል አደረጃጀት ጋር በተያያዘ ሀሰተኛ የሆነ መረጃ በማሰራጨት፣ ብሄርን ከብሄር ሁከት ቀስቃሽ የሆኑ መልዕክቶች ለማስተላለፍ እና በከተማው አደረጃጀት በመፍጠር  ሁከትና ብጥብጥ እንዲፈፀም ከጽንፈኞች ጋር ሲንቀሳቀስ እንደነበር መረጃ ደርሶናል በሚል ይግባኝ ጠይቆበት በእስር ላይ እንዲሚገኝ ታውቋል።

ወቅታዊ ፤ ትኩስ እና የተሟላ መረጃዎችን ለማግኘት
Youtube: https://www.youtube.com/@nisir/videos

FaceBook Page 1 :    https://www.facebook.com/Nisirbroadcast

FaceBook Page 2:  https://www.facebook.com/Nisirmereja      

Telegram:    https://t.me/nisirbroadcasting

Website: https://nisirbroadcasting.com

Twitter:   https://twitter.com/NISIRInternati1

Instagram:  https://www.instagram.com/nisirbroadcast/
ንሥር ብሮድካስትን በወዳጅነት ይከታተሉን።