ችሎት ዜና
ፍ/ቤቱ ፖሊስ በጋዜጠኞቹ ላይ የጠየቀውን ተጨማሪ 14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ፈቀደ
ንሥር ብሮድካስት
ግንቦት 4/2015
ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው እና ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ አስፋው ዛሬ ግንቦት 4 ቀን 2015 ዓ.ም ከረፋዱ 4:00 ላይ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት ቀርበው ነበር::
ጋዜጠኞቹ በሁከትና ብጥብጥ ተጠርጥረዋል በሚል ቀደም ሲል አራዳ ፍርድ ቤት ቀርበው በዋስ እንዲወጡ ተወስኖላቸው የነበረ ሲሆን የፌደራል ፖሊስ ውሳኔውን በመተው በሌላ "በሽብር" ጠርጥሬያቸዋለሁ በሚል ነው ወደልደታ ፍርድ ቤት ያዛወራቸው::
ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበው በጠበቆቻቸው በኩል ጥፋተኛ አለመሆናቸውንና ህጉ ከሚፈቅደው ውጭ ጋዜጠኞቹ በቅድመ እስር እየተጉላሉ መሆኑን ተከራክረዋል::
በዋስ ወተው ጉዳያቸውን በውጭ እንዲከራከሩም ጠይቀው ነበር::
ይሁንና ፍርድ ቤቱ መርማሪ ፖሊስ የጠየቀውን የ14 ቀን ቀጠሮ ፈቅዷል ሲል ጋዜጠኛ አራጋው ሲሳይ አጋርቷል።
ወቅታዊ ፤ ትኩስ እና የተሟላ መረጃዎችን ለማግኘት
Youtube: https://www.youtube.com/@nisir/videos
FaceBook Page 1 : https://www.facebook.com/Nisirbroadcast
FaceBook Page 2: https://www.facebook.com/Nisirmereja
Telegram: https://t.me/nisirbroadcasting
Website: https://nisirbroadcasting.com
Twitter: https://twitter.com/NISIRInternati1
Instagram: https://www.instagram.com/nisirbroadcast/
ንሥር ብሮድካስትን በወዳጅነት ይከታተሉን።